Get Mystery Box with random crypto!

#ትንሳኤ እንኳን አደረሳችሁ ! ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የኢትዬጲያካስቲንግ ፊልም ፖሮ | 🇪🇹Ethiopia Casting Film production

#ትንሳኤ

እንኳን አደረሳችሁ !

ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የኢትዬጲያካስቲንግ ፊልም ፖሮዳክሽን አባላት በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።

በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

በዓሉን ስናከብር ፤ የተቸገሩ ወገኖቻንን አለንላችሁ በማለት ፣ የወደቁትን በማንሳት ፣ በሀዘን ላይ ያሉ ወገኖችን በማፅናናት፣ ከክፉ ድርጊትና ሀሳብ ርቀን ሊሆን ይገባል።

በተጨማሪም ፤ በዓሉን በሰላም እጦት ፣ በግጭት ፣ በጥቃት፣ በድርቅ ክፉኛ የተጎዱ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በገዛ ቄያቸው ከሞቀው ቤታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የወደቁትን ፤ በፀሃይና ዝናብ የሚንከራተቱትን ፤ የሚወዱትን ተነጥቀው በጥልቅ ሀዘን ላይ የሚገኙትን ፣ ታመው በየሆስፒታሉ የተኙትን ፣ በየሰው ሀገር በስደት ስቃያቸውን እያዩ ያሉ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በግልም ፤ በሀገርም ላለብን ችግር ሁሉ አምላክ መፍትሄ እንዲያበጅልን እየተማፀንን እንድናሳልፍ አደራ እንላለን።

የሰላም፣ የመተሳሰብና የበረከት በዓል ያድርግልን !
ፈጣሪ ሀገራችን ሰላም ያድርግልን !

መልካም በዓል !
EthiopiaCasting Film Production