Get Mystery Box with random crypto!

የክለባችን ቅድመ ውድድር ዝግጅት በሐዋሳ! የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ዋናው ቡድን በሐዋሳ ሴ | ኢትዮጵያ ቡና የሸገር አርማ

የክለባችን ቅድመ ውድድር ዝግጅት በሐዋሳ!

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ዋናው ቡድን በሐዋሳ ሴንትራል ሆቴል መቀመጫውን አድርጎ ከነሐሴ 1/2014 ዓ.ም ጀምሮ የቅድመ-ውድድር ዝግጅቱን በማድረግ ላይ ይገኛል።

ቡድኑ በዋናው አሰልጣኝ #ተመስገን_ዳና እየተመራ ከእሁድ በስተቀር በቀን ሁለት ጊዜ በሐዋሳ ግብርና ዩኒቨርስቲ የመለማመጃ ሜዳ ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል።

አዳዲስ ካስፈረምናቸው ተጫዋቾች እና ከተስፋው ቡድን ለመታየት ቡድኑን ከተቀላቀሉት በተጨማሪ ከተለያዩ ክለቦች ለሙከራ የመጡ ተጫዋቾችን አሰልጣኙ እየተመለከቱ ሲሆን፤ ወደ ቡድኑ የሚቀላቅሉትን ተጫዋቾችን ለመለየት ይረዳ ዘንድ ዛሬ ቡድኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሁለት በመክፈል ግጥሚያ አድርገዋል።

በቀጣይ የፊታችን ሰኞ የወዳጅነት ጨዋታ ከሌላ ክለብ ጋር አድርገው ሙሉ ለሙሉ ቡድናቸውን ያሳውቃሉ።

ቡድኑ የተለያዩ ባለሙያዎችን እያስመጣ ስልጠናዎችን ለመስጠት በያዘው ዕቅድ መሰረት ዛሬ ለሁሉም የቡድኑ አባላት በስነ-ምግብ ባለሙያ ስልጠና የሚሰጣቸው ሲሆን ፤ በቅርቡም የስፖርት ሳይኮሎጂ ስልጠናም የሚሰጣቸው ይሆናል።

በቀጣይ በቡድኑ ዙሪያ የሚኖሩ መረጃዎችን ይዘንላችሁ የምንቀርብ ይሆናል።