Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲን አስመልክቶ በሰራው ዘገባ ላይ እርማትና ተጨማሪ ማብራሪያ ሰ | Ethiopia 24

አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲን አስመልክቶ በሰራው ዘገባ ላይ እርማትና ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥቷል። ዩኒቨርሲቲውንና አንባቢያኑንም ይቅርታ ጠይቋል።

አዲስ ማለዳ በቅጽ 4 ቁጥር 203 መስከረም 14/2015 እትሟ ‹በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ዲግሪ በ20 ሺሕ ብር እየተሸጠ መሆኑ ተነገረ።› በሚል ርዕስ የፊት ገጽ ዜና ይዛ መውጣቱ ይታወሳል።

አዲስ ማለዳ ባወጣዉ ሰፊ ማብራሪያ ፤ ይህንን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲው በዜናው ላይ ቅሬታ እንዳለው ለጋዜጣዋ ዝግጅት ክፍል አሳውቋል ብሏል። ቅሬታው በዋናነት ‹ዜናው ሚዛናዊ አይደለም› የሚል ነበር። አዲስ ማለዳ ዘገባውን ሚዛናዊ ለማድረግ ተቋሙ በድረ-ገፁ ላይ ባስቀመጠው ስልኮች ላይ በተደጋጋሚ በመደወል የሚመለከታቸውን የሥራ ኃላፊዎች ለማነጋገር ጥረት አድርገናል ብሏል።

ነገር ግን ይህ ሙከራ እንዳልተሳካ በዜናው ላይ ገልጸናል ብሏል። በማብራሪያዉ ፤ ምንም እንኳን ዜናውን ለአንባብያን ለማድረስ በሚታወቅ የሚዲያ አሠራር ምክንያት የጊዜ እጥረት የነበረብን ቢሆንም፣ የተቋሙን አመራሮች ለማግኘት ተጨማሪ ጊዜ ወስደን በጉዳዩ ላያ ያላቸውን አስተያየት ማካተት ተገቢ እንደነበር እናምናለን ፤ ይህን ሳናደርግ ዜናውን ለአንባቢያን በማቅረባችን ዩኒቨርሲቲውንም፣ አንባቢያንንም ይቅርታ እንጠይቃለን ሲል አዲስማለዳ ጋዜጣ አስታውቋል።

በተጨማሪም፣ ጉዳዩ በዜናው ርዕስ ላይ እንደተገለጸው ዩኒቨርሲቲው አውቆ፣ ተቋሙ በዘረጋው ሥርዓት በኩል እውቅና ተሰጥቶት ትምርህታቸውን በተቋሙ የትምህርት ክፍሎች ውስጥ ገብተው ላልተማሩ ሰዎች 20 ሺሕ ብር ስለከፈሉ ብቻ ዲግሪ እየተሰጣቸው እንደሆነ የሚመስል አንድምታ ዜናው እንደፈጠረ ተረድተናል ያለ ሲሆን ነገር ግን በምርመራችን እንዳረጋገጥነው ይህ ስህተት ነው ብሏል።

ዩኒቨርሲቲው ይፋዊ በሆነ መንገድ ሳያውቀውና እውቅና ሳይሰጠው በተቋሙ ሥም የሚዘጋጁ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን አንዳንድ ሰዎች 20 ሺሕ ብር በመክፈል እያሠሩ መሆኑን አዲስ ማለዳ በምርመራዋ አረጋግጣለች። የዜናችን ርዕስ ከዘገባው መሠረታዊ ጭብጥ በወጣ መልኩ ዩኒቨርሲቲው በ20 ሺሕ ብር ዲግሪ እየሸጠ እንደሆነ አንድምታ በሚፈጥር መልኩ መሠራቱ ስህተት ነዉ ብሏል።  አዲስማለዳ በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣዉ ማብራሪያ ዩኒቨርሲቲውንም ሆነ አንባቢያንንም ይቅርታ እንጠይቃለን ብሏል።

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24