Get Mystery Box with random crypto!

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በተያዘው ወር መጨረሻ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት እያደረገ | Ethiopia 24

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በተያዘው ወር መጨረሻ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ከ34 ሺህ 200 በላይ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል።

ዩኒቨርሲቲው በሁለት ዙር ለሚሰጠው ፈተና አራት የመፈተኛ ቦታዎችን ማዘጋጀቱን አሳውቋል።

በደሴ በዋናው ግቢ እና በመምህራን ኮሌጅ እንድሁም በኮምቦልቻ በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቱ እና በኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ፈተናውን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የመፈተኛ፣ የምግብ እና የመኝታ ክፍል አገልግሎቶች ዝግጅት እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል።

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24