Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች  #ዩኒፎርም ለብሶ የመገኘት ግዴታ  አለባቸው ፦ የአ | Ethiopia 24

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች  #ዩኒፎርም ለብሶ የመገኘት ግዴታ  አለባቸው ፦ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

ዘንድሮ ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለጸ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ፈተናውን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤ ኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ፌደራል ቴክኒክና እልጠና ኢንስቲትዩት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገልጻል፡፡

በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውንና ፈተናውም ከመስከረም 30 ጀምሮ በቅድሚያ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ተፈትነው ሲጨርሱ የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ቀጥለው እንደሚፈተኑ የተገለጸ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የምግብና የመኝታ አገልግሎቶችን በየተቋማቱ እንደሚያገኙም ተጠቁማል፡፡

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24