Get Mystery Box with random crypto!

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በወሩ መጨረሻ መሰጠት ለሚጀምረው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማ | Ethiopia 24

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በወሩ መጨረሻ መሰጠት ለሚጀምረው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችን ለመቀበል በሙሉ አቅሙ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን ከ36 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ፈተናውን ለመስጠት ዝግጅቶችን እያደረገ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው በዋናው ግቢ፣ በቡሬ እና በጤና ካምፓስ ተፈታኝ ተማሪዎችን ለመቀበል ላለፉት ሁለት ሳምንታት የተለያዩ ኮሚቴዎች በማዋቀር ቅድመ ዝግጅት ሲያደረግ መቆየቱን የተቋሙ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ይኼይስ አረጉ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ከዋናው እና ቡሬ ካምፓስ 539 ፈታኝ፣ 36 አንባቢ እና 17 ቆጣሪ ተመልምለው የስም ዝርዝራቸው ለትምህርት ሚኒስቴር መላካቸውን ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎች ወደ ተቋሙ ሲሄዱ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና ብርድ ልብስ መያዝ እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24