Get Mystery Box with random crypto!

PAPIO BELETE 💚💛❤️

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopap — PAPIO BELETE 💚💛❤️ P
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopap — PAPIO BELETE 💚💛❤️
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopap
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 977
የሰርጥ መግለጫ

ጠቢብ አባት ልጁን "ልጄ ሰው ሁን!" ብሎ ሲመክረው ከሚታየን ሰውነት ባሻገር "ሰው" የመሆን ህላዌ እንዳለ ያመለክታል፡፡
ሰው ፡ "ሰው" መሆን ካልቻለ ፡ ሌሎች ሰዎችን ሊያፈቅር አይችልም፡፡
ሰው ፡ "ሰው" መሆን ካልቻለ ፡ ከሌሎች ሰዎች ጋር በሰላም መኖር አይችልም፡
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE0xkdzIDE_qjfy9cA
@TMan

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-30 22:18:04 https://www.instagram.com/tv/CgmQi2sovDK/?igshid=MDJmNzVkMjY=
225 views19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 22:45:58
https://youtube.com/channel/UCaYlFgQMYiYdltwhfRw682g?sub_confirmation=1
221 views19:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 22:14:57 https://youtube.com/channel/UCaYlFgQMYiYdltwhfRw682g?sub_confirmation=1
1.0K views19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-17 17:06:55

520 views14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-26 21:17:07
935 views18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-26 21:16:51 የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት 11ኛ ትውልድ የነበሩት #ብጹዕ_አቡነ_ዲዮስቆሮስ (አባ ወልደ ትንሳይ ግዛው)
አቡነ ዲዮስቆሮስ በጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት የትውልድ ቦታ #ኢቲሳ ጽላልሽ በመጋቢት 24 1911 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ብጹእነታቸው በተወለዱበት ኢቲሳ ተክለ ሃይማኖት የድቁናን ትምህርት ተከታትለው ከግብጻዊው ጳጳስ አቡነ ቄርሎስ ድቁናን ተቀብለው በመናገሻ ጸዋትወ ዜማን፣ በደብረ ማርቆስ ቅኔን፣ በቆላ እስጢፋኖስና ዲማ ጊዮርጊስ ትርጓሜን ተምረው ወደ ትውልድ ስፍራቸው ተመልሰው መምህር በላይ ከተባሉ ሊቅ ዘንድ በመቀመጥ ትምህርታቸውን እያጠናከሩ ሳለ የፋሺሽት ኢጣልያ ጦር ኢትዮጲያን በመውረሩ ትምህርታቸውን አቋርጠው አርበኞችን በመቀላቀል ለ4 አመታት ከታገሉ በኋላ በጣልያን ጦር ለአንድ አመት በምርኮ ቆዩ፡፡

በዚህ ወቅት ብጹዕነታቸው ኢትዮጵያ ከጣሊያን ነጻ ከወጣች በምንኩስና እግዚአብሔርን ለማገልገል ቃል ገቡ፡፡ በቃላቸው መሰረት ኢትዮጵያ ነጻ እንደወጣች ወደ ደብረ ሊባኖስ በማቅናት ነሐሴ 24 1933 ምንኩስናን፣ መጋቢት 24 1934 ደግሞ ቅስናን ተቀበሉ፡፡ ከዚህ በኋላ በአዲስ አበባ ለ6 አመታት አገልግለው በ1940 መጋቢት 24 ቁምስናን በመቀበል በአዲስ አበባ፣ ሐረር፣ ድሬዳዋ፣ ኡጋዴንና አካባቢው በእልቅናና በመምህርነት አገለገሉ፡፡
ከዚህ በኋላ ብርሃን ሆነው ወዳበሩባት ወሊሶ ሊቀ ካህናት ሆነው መስከረም 1 1945 ተጓዙ፡፡ ቀጥለውም ግንቦት 30 1970 ከብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ማእረገ ጵጵስናን በመቀበል የደቡብ ምዕራብ ሸዋና ጨቦና ጉራጌ ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ተሾሙ፡፡

በወሊሶ አገልግሎታቸውን በጀመሩባት የቤተሳይዳ ማርያም ቤ/ክ ከ10 ሚሊዮን በላይ ለሆኑና ከተለያዩ ዓለማት ይመጡ ለነበሩ ህሙማን ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው የፈውስ ጸጋ ይፈውሱ ነበረ። አዕዛብን ሳይቀር በጥምቀት ዳግም እንዲወለዱ ያደረጉ ታላቅ ሐዋሪያም ናቸው።
ብጹዕነታቸው ለወጣቶች ከፍተኛ ፍቅር ነበራቸው፡፡ ወጣቶች በወቅቱ በነበረው መንግስታዊ የኮሚኒዝም ፍልስፍና ተወስደው እንዳይጠፉ በቤተ ክርስቲያን ፍቅር ተተክለው እንዲቀሩ ይለፉ ነበር፡፡ እንዳሁኑ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጊቢ ጉባኤያት ባለተዘረጉበት በዛ ዘመን እርሳቸው ጋር መጥተው ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ቁጥር ከፍተኛ ነበር፡፡ ከ70 በላይ ድሃ እና ወላጆቻቸው የሞቱባቸውን ሕጻናት በማሳደግ ለቁም ነገር እና ለወግ ለማእረግ አብቅተዋል፡፡

የብጹዕነታቸው ትህትና ከፍተኛ በመሆኑ ለፈውስም ሆነ ለቃለ ወንጌል ወደእርሳቸው የሚመጡ ምእመናን እጃቸውን ይስሙ ነበር "አዳኙ አምላክ ነው የኔን እጅ ለመሳለም አትሩጡ። እኔ አዳኝ ብሆን #አንድ_ዐይኔን_አበራ_ነበር። ይልቁን እናትና ልጁን አመስግኑ። መባውን ከሳጥኑ አኑሩ፥ የሳጥናኤልን ቃል አትስሙ። በማለት እጃቸውን ለመሳም እንዳይጋፉ ይከለክሉ ነበር፡፡
አስገራሚው የብጹዕነታቸው የሕይወት ክፍል ደግሞ የጸሎት ህይወታቸው ነበር፡፡ ሁልጊዜም በፊቷ ቆመው የሚለምኑባት ሥዕለ ማርያም ነበረቻቸው። በአንድ ወቅት በሰጡት ቃለ መጠይቅ ሕሙማን ሳይፈወሱላቸው ሲቀሩ በሥዕሏ ፊት ቆመው "ምነው እመ ብርሃን፥ ተይ አታሳፍሪኝ" ብለው ሲጸልዩ ሕሙማን ይፈዋሱላቸው እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ሀይለ ስላሴ ለአገልግሎት ይረዳቸዋል ብለው የሸለሙዋቸውን ላንድ ክሮዘር መኪና ነበራቸው ይህቺን መኪና በማሽከርከር ላይ ሳሉ ተገልብጣ ከሞት በተረፉ ሰዓት ይህች ስዕል ደረታቸው ላይ ተገኝታለች፡፡ ሥዕሏ በአሁኑ ወቅት በሰበታ ቤተ ደናግል ገዳም የመድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ስትገኝ በየወሩ በሃያ ሰባት ቤተ ክርስቲያኑ ስለሚከፈት ትታያለች፡፡ ብጹዕነታቸው ብዙ ቋንቋ መናገር ባይችሉም፥ ከተለያዩ ዓለማት የመጣውን ሁሉ - የኳታሩን ፕሬዝዳንት ልጅ ጭምር - በቋንቋቸው ያናግሩ ነበር።

በንጉሱ ዘመን አፄ ኃይለ ሥላሴን ደፈረው ከሚናገሩ ከሚገስጹ አበው አንዱ ናቸው ንጉሱም አባታችንን እንደ አይን ብሌን የሚያዩአቸውና የሚያከብሩዋቸው ነበሩ።
በደርግ ዘመን ወታደሩ ወጣቶች ሊረሸን በተነሳ ግዜ አባታችን መሀል በመግባት መጀመርያ እኔን ገላችሁ ወጣቱን ጨርሱ በማለት ብዙዎችን ከሞት ታድገዋል። የግድያው መሪ ነገ አንተን እዚሁ እደፋሀለው ብሎ በመዛት ይሄዳል አባ ወልደ ትንሳኤል ሙዋቹን አምላክ ያውቃል ብለው ወደ በዓታቸው ያመራሉ በማግስቱ ያ ወታደር እዛው እዛተበት ቦታ መኪናው ተገልብጦ ሞቶዋል። በሰው ሞት ባንደሰትም የአምላክን ፍርድ እናደንቃለን።

እምነትን ከምግባር፣ ክብርን ከትህትና፣ የፈውስ ጸጋን ከትንቢት ስጦታ በአንድ የያዙት የወሊሶው ብርሃን አቡነ ዲዮስቆሮስ (አባ ወልደትንሣይ) በዛሬዋ ቀን ጥር 18 1991 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተውናል። ከባንክ ደብተራቸው የተገኘው ስድስት ብር ብቻ ነበር። ስርዓተ ቀብራቸውም የወቅቱ ቅዱስ ፓትሪያሪክ አቡነ ጳውሎስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በተገኙበት በመሰረቷት ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡

#በረከታቸው_ይድረሰን

ምንጭ፡- ዜና ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፥ ዌኪፔዲያ የመረጃ ቋት፥ የመልአከ ሰላም አባ ገ/ሚካኤል፥ ሸገር ኤፍ ኤም ከፕ/ር መስፍን ጋር ካወጉት።
810 views18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-28 19:29:28 #ጊጎ (GIGO) የሚለውን ምህፃረ-ቃል የሚጠቀሙት የኮምፒውተር ባለሙያዎች ናቸው፡፡ ጊጎ ሲተነተን (garbaga in garbage out) በአማርኛ “ቆሻሻ ከገባ ቆሻሻ ይወጣል” ማለት ነው፡፡ የኮምፒውተር ባለሙያዎች ይህን ቃል የሚጠቀሙት ስለኮምፒውተር አለመሳሳት ሲያስረዱን ነው፡፡ “ኮምፒውተር አይሳሳትም ከተሳሳተም እኛ ተጠቃሚዎቹ የተሳሳተ ትእዛዝ በመስጠታችን የተነሳ ነው ሊሳሳት የቻለው” እንደ ለማለት ነው፡፡ የሰው ልጅ የሰራው ኮምፒውተር ካልተሳሳተ የሰው ልጅ ስለምን ሊሳሳት ቻለ ? የሚለውን ጥያቄ እንደ አንድ ትልቅ አጀንዳ የራሳችንን መላምት ልንሰጥበት እንችላለን። ታላቁ የስነልቦና ሊቅ #ሲግመንድ_ፍሩድ “child is the father of man” ( ልጁ የሰውየው አባት ነው) ማለት ነው ሲል አባባ ተስፋዬ ደግሞ “የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች” እንደሚሉት መሆኑ ነው፡፡ “የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች” ሲባል ቁም ነገሩ የአበባው መልክ ሳይሆን ፍሬው ላይ ነው፡፡ ፍሬው ለነገም ዘር ዛሬም የልፋት ውጤት ነው።

የገባ ነው የሚወጣው፤ የተተከለ ነው የሚፀድቀው፤ የተንከባከቡት ነው የሚያፈራው፤ የተዘራ ነው የሚበቀለው፡፡ ስለዚህ አዘራራችን በልኩ እና ቀና ቀናውን መልካሙን ዘር መሆን አለበት፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ዘራችን ከመከነ፤ እንክርዳድ ከበቀለበት፤ ከጠወለገ ተጠያቂው ፍሬው ሳይሆን አዝመራውን ያዘመረ፤ ፍሬውን ኮትኩቶ ያበቀለው ነው፡፡ እኛ የልጆቻችን ገበሬዎች ነን እነሱ ደግሞ ፍሬዎቻችን፡፡ ምርቱን የፈለገ ሰው ሌት ተቀን ሳያርፍ አረሙን ያርማል፤ ውሀ ያጠጣል፤ አዝመራውን ያዘምራል፤ ጎተራውን ይጠብቃል፡፡

ድሮ ልጆች ሲያጠፉ፤ ስርአት ሲጎድላቸው “እናንተ አሳዳጊ የበደላችሁ!” ይባላል፡፡ ዘንድሮስ ምንድነው የሚባለው? ፌስቡክ የበደላችሁ፤ ዲሽ ያንጋደዳችሁ፤ ሆሊውድ ያጣመማችሁ ነው የሚባለው፡፡ ድሮ ጥሩ ቤተሰብ ባይኖር እንኳ መልካም መካሪ ጎረቤት አይጠፋም፡፡ ጉርብትናው በኑሮ ሩጫ ስለጠፋ ልጆቻችን ቴሌቪዥንና ሞባይላቸው እያንጋደደ ያሳድግልን ጀመር፡፡
ዛሬ በብልሹ ምግባር እራስ ወዳድ የሆኑት ልጆቻችን ትናንት ለእነሱ የትኛውንም መስዋእትነት ከፍለን ስላላስተማርናቸው፣ ስላላሳደግናቸው ነው፡፡ ዛሬ ማንንም አንውቀስ፡፡ ምክንያቱም ጥፋቱ የኛው ነው፤ ጊጎ ነው፡፡

ኮንትራት ተፈራርመው የተጋቡት ልጆቻችን እንደ አባቶቻቸው በየሰፈሩ ቅምጥ ላለማስቀመጥ ሊሆን ይችላል፡፡ እስኪብርቶ በመጨበቻቸው ሰአት ጠርሙስ መጨበጥ የተማሩት እኮ ትናንት በጆግ ጠላ አምጡ ብለን ስንልካቸው ነው፡፡ ጫት የለመዱት ያኔ እኛ እየቃምን ልጆቻችን ቡና ሲያፈሉልን በማጨሻው ላይ እጣኑን ሲያደርጉልን ነው፡፡ እውቀት በደንብ ያልጨበጡ ተማሪዎች ጥፋቱ ከእነሱ ወይስ ካስተማሪው ?
ሰው የዘራውን ነው የሚያጭደው ይባላል፡፡ ሚዲያዎቻችን የተዘራው እንደሚበቅል ረስተውታል፡፡ የሬዲዮ ፕሮግራሞቻችን ጠባም መሸም ኳስ ኳስ ብቻ ነው፡፡ ለምን ? ሲባሉ “ሰው ኳስ ይወዳል” ነው መልሱ፡፡ ሰው የሚሰማውን ነው የሚወደውም የሚፈልገውም፡፡ የኳስ ዘር እየዘራን እንዴት የስነጽሑፍ፣ የባህል፣ የ ታሪክ የሀገር እውቀት ያለው ትውልድ ከየት ነው የሚያብበው፡፡

በየሚዲያው ላይ “ከሁለት እና ከሦስት በላይ ፍቅረኛ ያላችሁ፤ ከትዳር በፊት ወሲብ መፈፀም ምን ይጠቅማል፤ ጫት ለጥናት ያለው ጥቅም፤ በትዳር ላይ የማገጣችሁ ተሞክሮአችሁን አካፍሉን” እያልን ክብር የማይገባውን፤ እውቅና ሊሰጠው የማይገባውን ጉዳይ እውቅና እየሰጠን፤ እንዴት ብለን ነው እሴት አክባሪ፤ ታሪኩን አዋቂ እና ታሪክ ሰሪ ትውልድ የምንፈጥረው ??
አውቀንም ሆነ ሳናውቅ የምንናገረው፤ የምንፅፈው ጽሑፍ፤ በሚዲያ የምናስተላልፈው የምናደርገው ድርጊት ሰዎች ላይ የሚያመጣው ተፅእኖ ከፍተኛ ነው፡፡ ጊዜ፣ ሁኔታ፣ ቦታ፣ ስለፈቀደልን የፈለግነውን ነገር እንደፈለግን መወርወር የለብንም፡፡ መልካሙን እንዝራ መልካሙን መልሰን እናጭዳለን፡፡
.
ቃልኪዳን ሀይሉ
.
713 views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-07 22:58:56
በዚህ ምስል አትገረም። የደኸየ ኪስ እንጅ የደኸየ ስነልቦና የለንም። የቆሸሸ ልብስ እንጅ የቆሸሸ አዕምሮ የለንም። የቀጠነ ሰውነት እንጅ መከራ የማይችል አጥንት አልተሸከምንም። ህዝብን እንደ ህዝብ አገርን እንደ አገር የሚያከብር አስተሳሰብ እንጅ በሀያል ናቸው ተራ ፕሮፓጋንዳ የሚሸነፍ ወንድነት አልሰራብንም። ሰዎቹ ኩሩ ነን። በማንም ጎረቤቶቻችን ላይ የማንንም ክብር እና ሉአላዊነት ደፍረን እምነቱን ለይተን፣ ቋንቋውን መርጠን ጥቃትና ወረራ ፈፀመን አናቅም። አክብረን የተከበርን ህዝቦች ነን።

ማንም ይሁን የትም ሰው በመሆኑ ብቻ እናከብራለን። ለዚች አለም ስግብግብ የሆነ አመለካከት የለንም። ሆዳችን አሸንፎን ችግራችንን በክብራችን ተደራድረንበት አናቅም። ጥቁር አድርጎ ሲሰራን በመፅሀፍ ቅዱስ ክብር ያላት አገር ተብሎ ስማችንን
ከትቦ ሲያስቀምጥልን ፣ በታላቁ ነብየ (መሀመድ ) ሰአወ ..ሀበሾችን ካልነኳችሁ አትንኩ ብለው የተናገሩልን ሚስጠረኛ ህዝቦች ነን። በታሪካችን እማንም ላይ ዘለን ገብተን የማንም ክብር አልነካንም። ክብራችንን ገፍተው የነኩንን ወራሪና ተላላኪ ባንዳና ቅኝ ገዢዎችን ግን አዋርደን መመለስ እንችልበታለን።
681 views19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-11 19:30:59 https://youtube.com/channel/UCaYlFgQMYiYdltwhfRw682g
905 views16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-29 22:04:40
መስቀልን በጉራጌ አዲስ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን Tourism Ethiopia የምስራች ይለናል። የጥያ ትክል ድንጋይ መገኛ፣ የበርካታ የባህል እሴቶች መፍረቂያ፣ የጥንታዊ ገዳማትና አድባራት እንዲሁም መስጊዶች መገኛ የሆነው ጉራጌ መስቀልና ሌሎች መስህቦች በቱሪስቶች እንዲጎበኙ እና ለማህበረሰቡ የገቢ ምንጭ ለማድረግ የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ ይገኛል።

ሰሞኑን ከተለየዩ ሀገራት የመጡ የውጭ ሀገር ዜጎች በጉራጌ በምሁር አክሊል በመገኘት "ራይድ ዘሪፍት የተሠኘ የብስክሌት ውድድር ፕሮግራምና በመስቀል በዓል ስርዓት ላይ ተሳትፎ አድርገዋል። ቱሪስቶቹ በዋቤ ወንዝ ላይ የጀልባ ላይ ቀዘፋ፣ በሐዋርያት ተራራማ አካባቢ የብስክሌት (Mountain bike tour) ጉዞም አድርገዋል፡፡ ዳይናስቲ ኢትዮጵያ፣ ተስፋ ቱር እና ሰሜን ኢኮ ሳይክሊንግ ቱር አስጎብኝ ድርጅቶች ከቱሪዝም ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ይህ የቱሪስቶቹ ቆይታ በቆቀር ቀበሌ በተለያዩ ቤተሰቦች በመገኘት በጉራጌ ማኅበረሰብ ዘንድ በታላቅ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ስርዓት በሚከበረው የመስቀል በዓል ስርዓት ላይ ተሳትፈዋል፡፡
.
via...ግሩም
1.1K views19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ