የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤ ልዑካን ቡድን ከኢትዮጵያ ሙስሊም ኮሚኒቲ ጋር በዶሐ ውይይት እያደረገ ነው ። ግንቦት /3/2015 የጠቅላይ ምክር ቤቱ ልዑካን በዶሐ ከሚኖሩ የኢትዮጵያን ኮሚኒቲ ወገኖቹ ጋር ከሚያደርገባቸው ዘረፈብዙ ውይይቶች በተጨማሪ የኮሚኒቱ አባላት ለጠቅላይ ምከር ቤቱ የተለያዩ ጥያቄዎችን አነሰተዋል- ከእነዚህ ውሰጥ -የኢትዮጲያ መስሊሞች የሃይማኖታቸው መገለጫ በሆነው ሒጃብ ጉዳይ በጉራጌ ክልል በጉንችሬ ከተማ የሚደረገው መገፋት ዘላቂ ወጥነት ባለው መንገድ መፍትሄዉ ምንድን ነው? -የሙስሊሞቸ ቀልብ ማረፊያ የሆነው እና የአላህ ቤት መስጅዶች ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየፈረሰ በመሆኑ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ተጨባጭ መፍትሄ ማምጣት ለምን ቸገረው? -በውጪ አገር የምንኖር ሙስሊም ወገኖቻቹህ በማህበራዊ ኑሮቸን ውስጥ የኒካህ ሰርተፍኬት ለማግኘት የቃዲ ችግረ አለብን -በሰኮላ ሽፕ ዙሪያ ያለባቸውን ችግር አንስተዋል -በሃይማኖታችን አትለያዩ አንድነት የጥንካሬያችሁ መገለጫ ነው ፤የሙስሊም ጌጡ ህብረቱ ነው የሚል ኢስላማዊ አሰተምህሮት ቢኖርም በየኮሚኒቱ ችግር ሆኖ ቆይቷል ይህ ችግር በዚህ ለውጥ ዘመን ሊለወጥ ይገባል -በእዚህ የኮሚነቲ ውይይት ላይ የአወሊያ ትምህርት ጉዳይ በስፋት ተነሰቷል -በኳታር የመጅሊስ ቅርጫፍ አንዲከፈትም ጠይቀዋል በ ኮሚነቲ ውይይት ላይ በርካታ ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን፣ የልዑካን ቡድኑ ምላሽ እንደደረሰን የምንገልፅ ይሆናል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤ ልዑካን ቡድን ከእዚህ የኮሚኒቲ ውይይት በኋላ በቀጠዩ ቀናት ወደ አገር ቤት ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል። 3.8K viewsedited 17:59