Get Mystery Box with random crypto!

በጉንችሬ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ አንዲደረግ ልዑኩ አሳሰበ ። ሚያዚያ 21/15 በኢትዮጵያ የእ | "ኡማ ቲቪ " Tv

በጉንችሬ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ አንዲደረግ ልዑኩ አሳሰበ ።

ሚያዚያ 21/15

በኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መሪነት በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጉራጌ ዞን እነሞር ወረዳ ጉንችሬ ከተማ አሰተዳደር በሙስሊም ተማሪዎች ከኒቃብ አለባበስ ጋር ተያይዞ የተነሳ የቆየ ችግር በዘላቂነት ከሚመለከታቸው ጋር ተነጋግሮ ለመፍታት ልዑካን ቡድን ልኳል።

በተለያዩ ጊዜያት በአካባቢው በተከሰው ችግር ምክንያት ቅሬታዎችና አቤቱታዎችን መነሻ በማድረግ ሶስት አባላት ያሉት ልዑኩ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ከሚመለከታቸው የቢሮ ኃላፊዎችወደ ቦታው ለመሄድ መንግስት አስፈላጊውን ሁኔታዎች እንዲያመቻችና ከክልሉ የሃይማኖት ተቋማት አባቶች ጋር ለሁለት ቀናት ጥልቅ ውይይት አድርጓል ።

በተደረገው ውይይት መሠረት ችግሩ የነቃብ አለባበስ ብቻ ሳይሆን ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ይዘት ያለውና በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው የሠላም ችግር በሰዎች ና በንብረት ላይ ሰፊ ጉዳት በማስከተሉ ችግሩን በዘላቂነት መፈታት እንዳለበት ቡድኑ ተገንዝቧል።

በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ተፈጥሮ የነበረውን የሠላም ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት ሁሉ አቀፍ ሕዝባዊ ውይይት ማድረጉ አስፈላጊ በመሆኑ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ና የክልሉ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካል ጋር በመነጋገር በቀጣይ ሳምንታት በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ እንዲያዘጋጁ ከልዑካን ቡድኑ ጋር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።