Get Mystery Box with random crypto!

አጂብ ! ልብ የሚያንኳኳ...! ‹‹አላህ ሆይ ከጥቂቶቹ ባሪያዎችክ አድርገኝ›› ___ _ በአንድ ወ | Ethio Nashida🎼🎤🎧ኢትዮ ነሺዳ

አጂብ ! ልብ የሚያንኳኳ...!
‹‹አላህ ሆይ ከጥቂቶቹ ባሪያዎችክ አድርገኝ››
___ _
በአንድ ወቅት ዑመረል ፋሩቅ ረዲየላሁ ዐንሁ በአንድ የንግድ
ስፍራ እያለፈ ሳለ አንድ ነጋዴ.. ‹‹አላህ ሆይ ከጥቂቶቹ ባሪያዎችክ
አድርገኝ›› ብሎ ዱዐ ሲያደርግ ይሰማዋል።
ዑመርም:- ‹‹ ይሄን ዱዐ ከየት ነው ያገኘከው?›› ብሎ
ይጠይቀዋል
ነጋዴውም:- ‹‹ አላህ በቁርዓኑ ከባሮቼ በጣም አመስጋኞቹም
ጥቂቶች ናቸው›› ይላል አለው ።
ዑመርም እራሱን ወቅሶ አለቀሰ እንዲህም አለ:- ‹‹ ዑመር
ሆይ ካንተ በላይ ሕዝቦችክ ዓዋቂዎች ናቸው››
‹‹ ያ አላህ ከጥቂቶቹ ባሪያዎችክ አድርገኝ›› ብሎ እሱም ዱዐ
አደረገ ።
_)_)_)_)_)_)
አንዳንድ ጊዜ ሰዎችን አንድ መጥፎ ተግባር እንዲያቆሙት
ሲመከሩ.. ‹‹ እኔ ብቻ አይደለሁም ይሄ ሁሉ ሰው እንዴት
ይሳሳታል ፣ ብዙሃኑ እኮ እንዲ ያደርጋል›› ሲሉ ይደመጣል ።
አላህ በቁርዓኑ ስለ ብዙሃኑ ሲነግረን እንዲህ ይላል :-
ብዙሃኑ ...!
- አያውቁም (7:187)
- አያመሰግኑም (2:243)
- አያምኑም (11:17)
- አመፀኞች ናቸው (5:59)
- ይስታሉ (6:111)
- እውነቱን አያውቁም (21:24)
- እንቢተኞች ናቸው (21:24)
- አይሰሙም (8:21)
ስለዚህም አላህ እንዳለው ከጥቂቶቹ ሁን !
(( ከባሮቼ በጣም አመስጋኞቹም ጥቂቶች ናቸው )) (34:13)
(( ጥቂቶች እንጂ ከርሱ ጋር አላመኑም )) (11:40)
(( በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ሲሆኑ ፤ ከፊተኞቹ ብዙ
ጭፍሮች ናቸው ፤ ከኋለኞቹም ጥቂቶች ናቸው)) (56:12-14)
ኢብነል ቀዪም ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ:-
‹‹የሃቅ መንገድን ያዝ ፤ አብረውህ ባሉት ጥቂት ሰዎች ቁጥር
ማነስ ብቸኝነት አይሰማክ ፤ የውሸትን መንገድ ተጠንቀቅ ፤ ጠፊ
በሆነው ብዛት አትታለል››
_ _
አላህ ከጥቂቶቹ ባሪያዎቹ ያድርገን

SHARE SHARE :-jOIN

@Islamicpost2399 @Islamicpost2399