#ሴቷ ማዲህ
አንዲት ሴት ኩበት እየለቀመች መንዙማውን እንዲህ እያለች ታንጎራጉራለች
አወየው ነቢ ፣ አወየው ነቢ
ሙሀመድ ነቢ ሰላም አለይክ እየለች ስትመድህ
#ጌታው ሰይድ *ጫሌ ሰሞት ብድግ አሉና ማነች ይቺ የሴት ማዲህ ዝም በይ በሏት አሉ። እርሷም ሰማችና እንዲህ አለች።
እኛ አርግዘነዎት: እኛ ወልደነዎት
አኛ አጥብተነዎት
ቃልቻ ዝም በል ነቢ የኛ ነዎት ፣አለች።
ጫሌም አረገኝ ወደየት ወሰደችው አሉና ወንድን ወንድ ሲመድኽው ነው ሚያምረው ብለን እንጂ ሌላ አይደለም አሏት። እሷም
ወንድነት ሲጠቀም: ሴትነት ሲጎዳ
እንገናኛለን አረደል በይዷ ሜዳ አለቻቸው።
እሳቸውም አረ በኸለቀሽ አረ እንደዛ አይደለም የዛሬን አፉ በይኝ ብለው ዱስቱር አሉ።
#የሴቶች ሀድራ ስትሰሙ ሁሉ ለምትንጫጩ አደብ ብለናል
Ethio Mewlid
https://t.me/ethiomewild