Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ ቴሌኮም ግብርን በቴሌ ብር ለመክፈል የሚያስችል አሰራርን ይፋ አደረገ ኢትዮ ቴሌኮም ገ | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

ኢትዮ ቴሌኮም ግብርን በቴሌ ብር ለመክፈል የሚያስችል አሰራርን ይፋ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም ገንዘብን በቀላል ፣ፈጣን ፣ ምቹ እና አስተማማኝ በሆነ መልኩ ግብርን በቴሌ ብር ለመክፈል የሚያስችል ስምምነት ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በዛሬው እለት ተፈራርሟል ።ደንበኞች ግብርን መክፈል የሚችሉበት የተለያየ መተግበሪያዎች መኖራቸው ተጠቁሟል።

ከነዚህም ውስጥ የቴሌ ብር የደንበኛ መተግበሪያ፣ የደንበኞች መተግበሪያን፣ እንዲሁም *127# በመጠቀም የብሄራዊ ባንክ ህግን በማክበር ግብርን መክፈል እንደሚቻል ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል ።ግብር ከፋዮች ኢ ታክስ ሲስተምን መጠቀም የሚችሉበት አሰራር ሲሆን የአጋርነት ስምምነቱ ለገቢዎች ሚኒስቴር የገቢ ግብርን እና የግል ሰራተኞች የጡረታ መዋጮ ፣ የፌደራል ታክስ ክፍያዎችን በወቅቱ ለመሰብሰብ እና ለማሳለጥ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገልጿል ።

ቴሌ ብር አገልግሎት እስካሁን 28.2 ሚሊዮን ደንበኞችን ማፍራት የቻለ ሲሆን ፣112 ዋና ወኪሎች ፣ ከ98 ሺህ በላይ ወኪሎችን እና ከ25 ሺህ በላይ ነጋዴዎችን ማፍራት ችሏል።በቀጣይም ጊዜያት ኢትዮ ቴሌ ኮም ከሌሎች ተቋማት ጋር በመተባባር የክፍያ ስርዓትን በቴሌ ብር የሚተገብርበት አሰራር በማመቻቸት ደንበኞችን የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራም የኢትዮ ቴሌ ኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ገልጸዋል ።