Get Mystery Box with random crypto!

በሸዋሮቢት ከተማ ከዛሬ ጀምሮ የሚተገበሩ የሰዓት ገደብ እላፊና ሌሎች ክልከላዎች ታወጁ ሐሙስ ጥር | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

በሸዋሮቢት ከተማ ከዛሬ ጀምሮ የሚተገበሩ የሰዓት ገደብ እላፊና ሌሎች ክልከላዎች ታወጁ

ሐሙስ ጥር 25 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት ከዛሬ ጥር 25/2015 ጀምሮ የሚተገበር የስዓት ገደብ እላፊና ሌሎች ክልከላዎች ማውጣቱን አስታውቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ ከአገር መከላከያ ሰራዊት፣ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከአማራ ልዩ ሀይል እና ከከተማው የፀጥታ መዋቅር የተውጣጣ መሆኑ ተገልጿል፡፡

እንደ ኮማንድ ፖስቱ ገለጻ ከሆነ፤ በቀጠናው የተፈጠረውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል በርካታ የሰላምና የጸጥታ ሥራዎች ለመስራት ያስችል ዘንድ የፀጥታ መዋቅሩ በተለይም ደግሞ አከባቢውን የተቆጣጠረው የአገር መከላከያ ሰራዊት ለሥራ ምቹነት ሲባል የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት የሚከተሉትን ክልከላዎች ማስቀመጡን አስታውቋል፡፡

ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ ካወጣቸው የሰዓት ገደብና ክልከላዎች መካከል ፡-

1ኛ. ባጃጅ እና ሞተር ሳይክል ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑን፣

2ኛ. በመንግስት እውቅና ወይም ፍቃድ ያልተሰጠው ስብስባ ማድረግ፣ ግጭት መቀስቀስ እና በማህበራዊ ሚዲያ ህዝብን ወደ ሁከት የሚያጋልጡ ምስሎችን እና ድምጾችንና ጹሁፎችን ማሰራጨት በጥብቅ የተከለከለ ነው፣

3ኛ. አገልግሎት ሰጪና ንግድ ተቋማት እንዲሁም የሰው እንቅስቃሴ ከምሽቱ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ የተከለከለ መሆኑ፣

4ኛ. ሲቪል ሆኖ የተለያዩ የፀጥታ መዋቅር ማለትም የአማራ ልዩ ሀይል፣ የአገር መከላከያ እና የፌደራል ፖሊስ አልባሳት መልበስ የተከለከለ ነው፣

5ኛ. በሰርግና ሌሎችን ሁነቶችን ምክንያት በማድረግ ርችትና ተቀጣጣይ ነገሮችን መተኮስ የተከለከለ መሆኑ፣

6ኛ. ከተፈቀደለት የፀጥታ መዋቅር ውጪ በከተማው ዘጠኙም ቀበሌዎች የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑን ኮማንድ ፖስቱ ገልጿል።

እነዚህን ድንጋጌዎችና ክልከላዎችን በማክበርና በማስከበር እንዲሁም በኮማንድ ፖስቱ አማካኝነት የሚሰሩ የሰላምና የጸጥታ ሥራዎችን ውጤታማ እንዲሆኑ እና የቀጠናው ሰላም ዘላዊነት እንዲረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ሲል ኮማንድ ፖስቱ ባወጣው መግለጫው አሳስቧል፡፡