Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው በ10ሺ ሜትር ድል አልቀናትም * **** እየተካሄደ ባለው በ18ኛው የኦሪገ | 💚💛❤️ ዮቶራዊያን💚💛❤️

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው በ10ሺ ሜትር ድል አልቀናትም
* ****
እየተካሄደ ባለው በ18ኛው የኦሪገኑ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ውድድር ፍጻሜን ተጠብቀው የነበሩት ኢትዮጵያዊያን ድል አልቀናቸውም፡፡
ኡጋንዳ በጆሽዋ ቺፕቴጌ ወርቁን 27፡27.43 በሆነ ጊዜ ወስዳለች፡፡ኬንያ በስታኒሊ ዋይታካ የብር ሜዳሊያውን ስታገኝ፣ ኡጋንዳ በውድድሩ በጃኮፕ ኪፕሊሞ ነሃስ በማግኘት የውድድሩን የበላይነት ወስዳለች፡፡
አትሌት ሰለሞን ባረጋ ውድድሩን በአምስተኛነት ሲያጠናቅቅ በሪሁ አረጋዊ ደግሞ 7ኛ ደረጃን ይዞ ጨርሷል፡፡ታደሰ ወርቁ በበኩሉ 14 ደረጃ ላይ ሆኖ ውድድሩን አጠናቋል፡፡
በዛሬው ውድድር በርቀቱ በኢትዮጵያዊያን በኩል የቡድን ስራ ጎልቶ አልታየም፡፡አትሌት ሰለሞን ባረጋ ሜዳሊያ ውስጥ ለመግባት ከፍተኛ ትግል ቢያደርግም ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡