2021-02-13 20:12:54
ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው!
የካቲት 06/2013
የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው፡፡
ከነዚህ መካካል
#ወለጋ
የወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 3ሺህ 398 ተማሪዎችን ዛሬ በወለጋ ስታዲየም አስመርቋል።
ዩኒቨርሲቲው ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል የመጀመሪያ ዲግሪ 3 ሺህ 13፣ በሁለተኛ ዲግሪ 344፣ በህክምና ዶክትሬት 40 እና የአካዳሚክ ዶክተር በአጠቃላይ 3 ሺህ 398 ናቸው።
#ቀብሪ_ደሀር
ቀብሪ ደሀር ዩኒቨርሲቲም የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ እና ሌሎች የክልልል እና የፌዴራል የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 612 ተማሪዎቹን አስመርቋል፡፡
#አዲግራት
የአዲግራት ዩንቨርሲቲም ለስምንተኛ ጊዜ 2ሺህ 576 ተማሪዎችን ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል፡፡
ዩንቨርሲቲው በትይግራይ ክልል በተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ጉዳት ስለደረሰበት ተማሪዎች ቀሪ ትምህርታቸውን በመቐለ ዩንቨርሲቲ እንዲያጠቅቁ ተደርጎ ዛሬ እየተመረቁ ነው፡፡
በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ሁርካቶ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል::
#መቀሌ
በሌላ በኩል በቅርቡ ተማሪዎችን አስመርቆ የነበረው መቐለ ዩኒቨርሲቲ ቀሪ 608 ተማሪዎችን በሁለተኛ ዙር እያስመረቀ ይገኛል::
#አርሲ
አርሲ ዩኒቨርስቲ በመጀመሪያ ዙር ያሰለጠናቸውን የህክምና ስፔሻሊስት ሀኪሞችን እያስመረቀ ነው!
አርሲ ዩኒቨርስቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመጀመሪያ ዙር በአራት የትምህርት ክፍል ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 23 የህክምና ስፔሻሊስት ሀኪሞችን እያስመረቀ ነው።
ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል 22ቱ ወንዶች እና 1 ሴት ሲሆኑ፣ በቀዶ ጥገና፣ በውስጥ ደዌ፣ የህፃናት ህክምና እና የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊቲ ዘርፍ ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆናቸው ተገልጿል።
በምረቃ መርኃ-ግብሩ ላይ የዩኒቨርሲቲው የሴኔት አባላት፣ የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዎች፣ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
#ኮተቤ
የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ፣ ተከታታይ እንዲሁም በማታ የትምህርት ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን 2ሺህ 39 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።
በዛሬው እለት ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል 2ሺህ 39ኙ ወንዶች ሲሆኑ 1ሺህ 29ኙ ደግሞ ሴቶች ናቸው፡፡
በምረቃ ስነስርአቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምሩቃኑ በሰለጠኑበት ዘርፍ ለሀገር የሚጠቅም ስራ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሀነ ጠና በበኩላቸው ተመራቂ ተማሪዎች የተመረቁት በቀለም ትምህርት በቻ ሳይሆን በአንድነትም በመሆኑ ህብረብሄራዊነትን የማስጠበቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
ብቁ ዜጋን በማምረት የእውቀት ፋና ወጊ የሆኑ መምህራንን በማፍራት አንጋፋ ስም ያለው ዩኒቨርሲቲው እስካሁን ከ80 ሺ በላይ ተማሪዎችን ማስመረቁ ተገልጿል።
#ጅማ
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው
የጅማ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ የትምህርት መርኃግብር ያሰለጠናቸውን 4ሺህ 328 ተማሪዎች በቅድመ እና ድህረ ምረቃ እያስመረቀ ነው፡፡
ከተመራቂዎቹ መካከል 2ሺህ 707 ወንድ እንዲሁም 1ሺህ 621 ሴት ተማሪዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
1993 ዓ.ም ላይ የተመሰረተው የጅማ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት 20 ዓመታት በርካታ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተደድር ሽመልስ አብዲሳ እና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መዓዛ አሸናፊን ጨምሮ በርካታ የክብር እንግዶች ተገኝተዋል፡
#via ENA/WALITA/EBC/FBC
#Purpose ETHIO MEREJA NEWS
@ethiomereja1 ሼር
67 views17:12