Get Mystery Box with random crypto!

#AU የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓትን የሰላም ንግግር በተመለከተ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊ | 🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

#AU

የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓትን የሰላም ንግግር በተመለከተ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት መግለጫ አውጥተዋል።

በመግለጫው ምን አሉ ?

- የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት #ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት የተገናኙበት የሰላም ንግግር ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ተጀምሯል።

- በሰላም ንግግሩ ላይ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (IGAD)
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ፣ የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች በታዛቢነት እየተሳተፉ ነው።

- ደቡብ አፍሪካ የሰላም ንግግሩን ለማስተናገድ ፍቃደኛ ስለሆነች ለሀገሪቱ መንግስት እና ለፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፖሳ ምስጋና አቅርበዋል።

- ሙሳ ፋኪ ማሀመት የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የኢትዮጵያን ጥቅም ባስጠበቀ ሁኔታ ሰላምን ለማስፈን እና ለግጭቱ ዘላቂ ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲገኝ ለማስረግ ባሳዩት ቁርጠኝነት ይበልጥ እንደተበረታቱ ገልፀዋል።

- የአፍሪካ ህብረት " የሰላም ንግግር " ተሳታፊ ወገኖች ኢትዮጵያ፤ በኢትዮጵያውያን ባለቤትነት እና በአፍሪካ ህብረት መሪነት ሰላም እንዲሰፍን ፣ የተረጋጋችና አንድነቷ የተጠበቀ እንድትሆን ህብረቱ ድጋፉን እንደሚቀጥል ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።

https://t.me/ethiomereja0