Get Mystery Box with random crypto!

'ህይዎት በፈረቃ ናትና ታገስ ' ምድራዊ ህይዎት ተፈጥሮዋ ፈረቃ ነው።ፍፁም ተድላና ፍፁም ችጋር | 🇪🇹ኢትዮ-News መረጃ

"ህይዎት በፈረቃ ናትና ታገስ "

ምድራዊ ህይዎት ተፈጥሮዋ ፈረቃ ነው።ፍፁም ተድላና ፍፁም ችጋር የሚባል ነገር የለም።

ደስታና ሀዘን፣ረሃብና ጥጋብ፣ህይዎትና ሞት፣ብርሃንና ፅልመት፣ትዳርና ፍቺ፣ጤና እና ህመም፣ልፋትና እረፍት፣ጦርነትና ሰላም፣ትርፍና ኪሳራ፣ክረምትና በጋ፣መውደቅና መነሳት፣ዕውቀትና ድድብና፣ሁከትና ፀጥታ፣ችኮላና እርጋታ፣..........የዚች አለም የፈረቃ ገፆች ናቸው።

ትናንት ድሃ የነበሩ አገሮች ዛሬ በሃብታቸው አለምን እየገዙት ነው።ተሰብረው የነበሩት ተጠግነው መራመድ ችለዋል።የተጣሉት ታርቀው ወዳጅ ሆነዋል።የተናቁ የነበሩት ዛሬ አለም እየሰገደላቸው ነው።መካኖች ልጅ ወልደው ስመዋል፣ሃያላን ተሰባብረው ጎዳና ላይ ወድቀዋል፣.............

ዋናው ነገር ሁለቱንም ፈረቃዎች በትዕግስትና በጥበብ ማስተናገድ ነው።የክረምቱ ወጀብ ተገልጦ የበጋው ፀሃይ እንደሚበሰረው ሁሉ ዛሬ ያለንበት የችግር ዶፍ አባርቶ የብልፅግናችንን ፀደይ የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይደለም።

ዛሬ ላይ ጠላት ቢበዛም ነገ መበተኑ አይቀሬ ነው።የዛሬው መጥፎ ገጠመኝ ለነገው ብሩህ ተስፉ ቦታውን ለቆ መሄዱ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ግደታ ነው።ዛሬ በጥጋብ የፈነጩብን ነገ እንደማያፍሩ ዋስትና የላቸውም።

የዛሬ መከረኛ ሌሊቶች በነገ የማለዳ ጮራዎች ተገፈው ያነቡ አይኖች ይታበሳሉ።ያስቸገሩን ኮረብታዎች ሁሉ በተባበረ ክንዳችን ይደረመሳሉ።የወጋን ቡዳ ማርከሻውን ሲያገኝ ይረክሳል።ሊፈጀን ያሰፈሰፈው ባቀጣጠለው እሳቱ ተቃጥሎ አመድ ሆኖ ይበናል።

ሰውና ትዕግስት አብሮ አደግ ናቸው።ከስልጣን ያወረዱትን፣ከማህበራዊ መስተጋብሩ ያገቱትን፣በኢኮኖሚ ማዕቀብ አሳምመው የቀጡትን፣በቀዬው ባይታወር ያደረጉትን ሁሉ በትዕግስት ትቷቸው እያለፈ ዛሬ ላይ ደርሷል።


ዛሬና ትናንት ፍፁም አንድ አይደሉም።ፀንፈኝነት፣አግላይነት፣ደሴትነቴ፣ከፋፋይነት፣ስግብግብነት፣በኪነት መግዘፍ፣ቤት ዘግቶ መብላት፣ወዘተ የፍፃሜ ጊዚያቸውን ሊያገኙ የመጨረሻው ትራክ ላይ ደርሰናል።የሚጠበቅብን ሁነቶችን በትዕግስት፣በጥበብና በስራ አጅቦ ማስተናገድ ብቻ ነው።"ቀን አለና ቀና ብለህ ተራመድ "እንዲሉ በዛሬው የችግር ናዳ አንገትህን ደፍተህ ከመራመድ ይልቅ የነገውን የተስፋ ጮራ እያማተርክ ቀና ብለህ ተራመድ።

እናም አብሽሩ!ሁሉም ለበጎ ነው!እርጎ ካልተገፋ ቂቤ አይወጣውም።እንጨት ካልጨሰ አይነዲም።ሻይ ካልተማሰለ ጣዕሙ አይታወቅም።በእርግጥም ከችግር በኋላ ድሎት አለና አይዞን!ነገ የእኛ አንገት ቀጥ ብሎ የግፈኞች አንገት መሰበሩ አይቀሬ ነው።


https://t.me/ethiomereja0