Get Mystery Box with random crypto!

#ነጻ_የስልጠና_ዕድል የ2ኛ ደረጃ ትምህርታችሁን ላጠናቀቃችሁ ተማሪዎች የተዘጋጀ ነጻ የስልጠና ፕ | Ethio_E_learning_Center

#ነጻ_የስልጠና_ዕድል

የ2ኛ ደረጃ ትምህርታችሁን ላጠናቀቃችሁ ተማሪዎች የተዘጋጀ ነጻ የስልጠና ፕሮግራም፦

ስልጠናው በ2013 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርታችሁን አጠናቃችሁ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለምትገቡ የህይወት ክህሎታችሁን ለማዳበር የተዘጋጀ ነው።

ስልጠናው ልምድ እና ሙያዊ እውቀት ባላቸው አሰላጣኞች የሚሰጥ ነው፡፡

ክቡር ኮሌጅ ከደስታን ኮሚዩኒኬሽን እና ከአፍሪካ ቢዝነስ ሰኩልስ አሶሴሽን ጋር በመተባበር ስልጠናውን አዘጋጅተውታል።

ሰልጣኞች በመረጡት የኮርስ አይነት ከአንድ ሳምንት እስከ ሦሥት ሳምንት ድረስ በስልጠና ላይ የሚቆዩ ይሆናል።

ስልጠናውን ወስደው ለሚያጠናቅቁ ተማሪዎች ሰርተፍኬት የሚሰጥ ሲሆን ንቁ ተሳትፎ ላደረጉ የተመረጡ ተማሪዎች ነጻ የከፍተኛ ትምህርት ዕድል (Scholarship) ተመቻችቷል፡፡

እስከ ሚያዚያ 27/2014 ዓ.ም ድረስ የ2014 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት ኮፒ በመያዝ በአካል በመቅረብ መመዝገብ ይቻላል፡፡

የሚሰጡ ስልጠናዎች፦

በአመራር ክህሎት
ፕሮግራሚንግ
የስሜት ብልህነት (EQ)
ሮቦቲክስ
ፕረዘንቴሽን ክህሎት
የመግባባት ክህሎት
ፐርሰናል ብራንዲንግ
ግራፊክስ ዲዛይን
ጊዜ አጠቃቀም
መሰረታዊ ሊኑክስ እውቀት
ዌብ ዴቨሎፕመንት
የሥራ ፈጣሪነት አስተሳሰብ

0113698558
0904848586

Join
@ethiolearn
@ethiolearn_bot
Contact
@Ethio_E_learning_center_Bot
━━━━━✧❂✧━━━━