Get Mystery Box with random crypto!

Ethio_E_learning_Center

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiolearn — Ethio_E_learning_Center E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiolearn — Ethio_E_learning_Center
የሰርጥ አድራሻ: @ethiolearn
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.10K
የሰርጥ መግለጫ

https://t.me/ SVSIDQoTv92qjcjA

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-04-29 08:26:25
#ነጻ_የስልጠና_ዕድል

የ2ኛ ደረጃ ትምህርታችሁን ላጠናቀቃችሁ ተማሪዎች የተዘጋጀ ነጻ የስልጠና ፕሮግራም፦

ስልጠናው በ2013 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርታችሁን አጠናቃችሁ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለምትገቡ የህይወት ክህሎታችሁን ለማዳበር የተዘጋጀ ነው።

ስልጠናው ልምድ እና ሙያዊ እውቀት ባላቸው አሰላጣኞች የሚሰጥ ነው፡፡

ክቡር ኮሌጅ ከደስታን ኮሚዩኒኬሽን እና ከአፍሪካ ቢዝነስ ሰኩልስ አሶሴሽን ጋር በመተባበር ስልጠናውን አዘጋጅተውታል።

ሰልጣኞች በመረጡት የኮርስ አይነት ከአንድ ሳምንት እስከ ሦሥት ሳምንት ድረስ በስልጠና ላይ የሚቆዩ ይሆናል።

ስልጠናውን ወስደው ለሚያጠናቅቁ ተማሪዎች ሰርተፍኬት የሚሰጥ ሲሆን ንቁ ተሳትፎ ላደረጉ የተመረጡ ተማሪዎች ነጻ የከፍተኛ ትምህርት ዕድል (Scholarship) ተመቻችቷል፡፡

እስከ ሚያዚያ 27/2014 ዓ.ም ድረስ የ2014 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት ኮፒ በመያዝ በአካል በመቅረብ መመዝገብ ይቻላል፡፡

የሚሰጡ ስልጠናዎች፦

በአመራር ክህሎት
ፕሮግራሚንግ
የስሜት ብልህነት (EQ)
ሮቦቲክስ
ፕረዘንቴሽን ክህሎት
የመግባባት ክህሎት
ፐርሰናል ብራንዲንግ
ግራፊክስ ዲዛይን
ጊዜ አጠቃቀም
መሰረታዊ ሊኑክስ እውቀት
ዌብ ዴቨሎፕመንት
የሥራ ፈጣሪነት አስተሳሰብ

0113698558
0904848586

Join
@ethiolearn
@ethiolearn_bot
Contact
@Ethio_E_learning_center_Bot
━━━━━✧❂✧━━━━
4.5K viewsedited  05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 08:25:20 ሰበር ዜና

የ ዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ተደርግዋል

የ 2013 12ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ተደርግዋል

ዩኒቨርሲቲ ምደባው ለማየት
Telegram bot
@moestudentbot

Google link
https://result.ethernet.edu.et

 Join
@ethiolearn
@ethiolearn_bot
Contact
@Ethio_E_learning_center_Bot
━━━━━✧❂✧━━━━
4.5K views05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-19 20:54:30
#Update

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ፤ ከክልሉ ተጨማሪ ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ የተወሰነላቸው 4339 ተማሪዎች በምን አግባብ እና በምን ሂደት እንደሚመረጡ አሳውቋል።

4,339 ተማሪዎች 50 ፐርሰንት እና ከዛ በላይ ካመጡ ከክልሉ ሁሉም ዞኖች መካከል በውጤታቸው ቅደም ተከተል ይመረጣሉ ብሏል።

ይህ በዚህ እንዳለ ሌሎች 50 ፐርሰንት እና በላይ ውጤት አምጥተው ወደ ዩኒቨርስቲዎች መግባት ያልቻሉት ደግሞ በክልሉ መምህራን ኮሌጆቾ " በመደበኛው የዲግሪ ኘሮግራም " የመምህርነት ስልጠና እንዲጀምሩ ሰፋ ያለ ቁጥር ለመቀበል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ቢሮው አሳውቋል።

ሌላው የመግቢያ ነጥብ ያላመጡ ተማሪዎች በመደበኛ ተማሪነት በድጋሜ ፈተና ይወስዳሉ የተባለው ሁሉንም የክልሉን ተማሪዎች የሚያካትት ሲሆን ይህም በልዩ ሁኔታ ለአማራ ክልል ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ወደ ዩኒቨርስቲዎች ሆነ ወደ መምህራን ኮሌጆቾ መግባት ያልቻሉት ተማሪዎች በቂ ዝግጅት አድርገው መፈተን እንዲችሉ የ2014 ዓም የ12ኛ ክፍል የፈተና ጊዜ እንዲራዘም ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል።

ትምህርት ሚኒስቴርም ቢሮው ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ከመስከረም 2015 ዓ/ም በፊት ፈተናው እንደማይሰጥ ትላንት መወሰኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

የክልሉ ተማሪዎች የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 20 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት ጊዚያት ሊሰጥ እንደሚችል አውቀው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ቢሮው አሳስቧል።

መረጃውን ይፋ ያደረጉት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ማተብ ታፈረ ናቸው።
Join
@ethiolearn
@ethiolearn_bot
Contact
@Ethio_E_learning_center_Bot
5.2K views17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-19 05:19:54
ተነስ ጥረትህን ቀጥል!

እየደበረህም ቢሆን በጠዋት ስትነሳ፣ ስፖርት ስትሰራ፣ ቁጭ ብለህ ስታነብ፣ አዲስ ትምህርት ስትማር፣ ቋንቋህን ስታሻሽል ወይ አዲስ ክህሎት ስትለማመድ ገንዘብህን፣ ጊዜህን እና ጉልበትህን ልታወጣ ትችላለህ፤ ግን ባወከው እውቀት ልክ ዋጋህ እያደገ ነው።

ይሄን ማድረግ ቀላል አይደለም፤ ቀላል ቢሆንማ ሁሉም ያደርገው ነበር። በህይወት ብዙ ውጤት መሰብሰብ ካሰብክ ግን ብዙ መዝራት አለብህ፤ ለዛነው አሁን ተነስተህ ጥረትህን የምትቀጥለው። ዳይ ተነስ!
3.7K views02:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 11:32:48 #NewsAlert

ትምህርት ሚኒስቴር ፥ በጦርነት እና በግጭት ውስጥ ሆነው ተፈትነዋል ተብለው የተለዩ እና የ12ኛ ክፍል የማለፊያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በዚህ ዓመት በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እንደ መደበኛ ተማሪ ሆነው መፈተን እንደሚችሉ አስታወቀ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር፣ ሁሉም ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በጋራ መግለጫ እየሰጡ እንደሚገኙ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

Join
@ethiolearn
3.6K views08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 11:59:01
የ2013 ዓ/ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ሂደት ላይ የቀረቡ ቅሬታዎችን እንዲያጣራ ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተላከው ኮሚቴ ምንድነው ያለው ?

የ2013 የትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት አስመልክቶ የአማራ ክልል ትምህርት ባቀረባቸው ቅሬታዎች ላይ የተደረሰበት ሂደት ኮሚቴው ለህዝብ አሳውቋል።

በዚህም መሰረት ፤ በጦርነት አውድ ውስጥ ቆይተው ፈተና እንዲወስዱ የተደረጉ በክልሉ የሁሉም ዞን ተማሪዎች በውጤታቸው ላይ የተለየ ተፅዕኖ የተፈጠረ መሆኑ እና ጉዳዩ በልዩ ሁኔታ መታየት እንዳለበት #ከትምህርት_ሚኒስቴር ጋር አስፈላጊው መግባባት መፈጠሩን ገልጿል።

በትምህርት ቢሮው በኩል በጦርነት ተጽዕኖ ምክንያት ውጤታቸው የቀነሰባቸው ተማሪዎች ዝርዝር መረጃ እና አስፈላጊ ማስረጃዎች ሁሉ ለትምህርት ሚኒስቴር መቅረቡን ገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴርም በቀረበለት መረጃ እና ማስረጃ መሰረት ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ እያየው እንደሆነና ውሳኔውን #በቅርብ_ቀናት የሚያሳውቅ መሆኑን ኮሚቴው ለህዝብ አሳውቋል።

ሌላው ኮሚቴው የተለያዩ መረጃዎችን አደራጅቶ ወደ ፈተናዎች ኤጀንሲ በመሄድ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምርመራ ያደረገ ሲሆን የደረሰበትን በዝርዝር አሳውቋል ፤ (በዚህ ያንብቡ https://telegra.ph/Amhara-Education-Bureau-04-15)

ተማሪዎች ፣ ወላጆች እና መላው ማህበረሰብ የትምህርት ሚኒስቴርን የመፍትሄ ሃሳብ በትግስት እንዲጠብቅ ኮሚቴው ጥሪውን አቀርቧል፡፡

በሌላ በኩል ፤ የ2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በተፈጠረው ችግር ሳይዘናጉ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ እንዲዘጋጁ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ጥሪውን አቅርቧል።
Join
@ethiolearn
@ethiolearn_bot
Contact
@Ethio_E_learning_center_Bot
3.7K views08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 11:04:28
አሸናፊዎች አያቆሙም!

በዚህ አለም ከባዱ ሰው ተስፋ ቆርጦ ጥረቱን የማያቆም ብቻ ነው። ዛሬ የተሸነፈ ይመስላል፣ ያጎነበሰ ይመስላል ግን ጥረቱን ስለማያቆም ህልሙን በድል ደምድሞ በኩራት ቀና ብሎ መራመዱ አይቀርም።

ይሄን የሚያነብ ሰው ሁሉ የማሸነፍ ጥማት አለው፤ ለሚወዳቸው የመድረስ ፍላጎት አለው፤ ህልሙን የማሳካት ጥልቅ መሻት አለው፤ ትልቁ ሚስጥር የጀመርከውን ጥረት አለማቆም ነው! ወዳጄ አሸናፊዎች አያቆሙም፤ የሚያቆሙ አያሸንፉም!

የሚገርም ጁምአ (አርብ) ተመኘንላችሁ
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
2.7K views08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-14 11:32:17
" ከፍተኛ ጫና እያሳደረብን ነው "

የ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈትነው ምደባ የሚጠባበቁ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ምደባው እንዲፋጠንለቸው በድጋሚ ጠይቀዋል።

የመጀመሪያውን ዙር ፈተና ተፈትነው እና ውጤታቸውን አውቀው ቤታቸው የተቀመጡ ተማሪዎች 6ኛ ወራቸውን ሊደፍኑ እየተቃረቡ ይገኛሉ።

እስካሁን ምደባ ይፋ የሚሆንበት ቀን ይፋ ያልተደረገ ሲሆን ይህ ሁኔታ ተማሪዎችና ወላጆችን ጫና ውስጥ እየከተተ ነው።

መልዕክታቸውን የላኩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል የሆኑ አንድ ወላጅ ልጃቸው ብሄራዊ ፈተና ወስዳ ወራት ቢቆጠሩም እስካሁን የምትማርበትን ተቋም ባለማወቋ ጫና እየደረሰባት፤ በግል እንኳን ለማስተማር ውሳኔ ላይ ለመድረስ እንደተቸገሩ፤ አመቱም እየተጠናቀቀ በመሆኑ ከእሷም አልፎ ቤተሰብ ላይ ጫናው እየበረታ መምጣቱን ገልፀዋል።

ከትምህርት እንዳትርቅ ጥረት እያደረጉ መሆኑ የገለፁት ወላጅ ፤ ነገር ግን ከመደበኛው ትምህርት ስርዓት ተማሪ መነጠሉ የሚያሳድረው ጫና ከባድ ነው ብለዋል።

መንግስት የሚስተካከሉ እና የቀረቡ ቅሬታዎች ካሉ በፍጥነት አስተካክሎ እና መፍትሄ ሰጥቶ ተማሪዎችን በፍጥነት ምደባቸውን እንዲያሳውቅ ጠይቀዋል።

ሌሎች መልዕክታቸውን የላኩ የቤተሰቡ አባላት ተማሪዎች ከመደበኛው ትምህርት ውጭ ሆነው የሚያሳልፉት ጊዜ ከፍተኛ የስነልቦና ጫና ውስጥ እየጣላቸው በመሆን መንግስት መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከጥቂት ቀናት በፊት ምደባን በተመለከተ ለቲክቫህ በላከው መልዕክት ትንሽ እንዲታገሱ መልዕክት ማስተላለፉ ይታወሳል።

የ2013 ዓ/ም ፈተና የመጀመሪያ ዙር #ከጥቅምት 28/2014 ጀምሮ ለ4 ተከታታይ ቀናት የ2ኛው ዙር ፈተና #ከጥር 24 ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀን መሰጠቱትና ውጤትን ጨምሮ መቁረጫ ነጥብ ይፋ መደረጉ ይታወሳል።
2.7K views08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-14 10:12:24
ወሳኙ መቀጠልህ ነው!

"ስኬት የደስታ መጨረሻ አይደለም፤ ውድቀትም ተሰብሮ መቅረት አይደለም፤ ወሳኙ ነገር ሁለቱም ነገር ገጥሞህ እንኳን መቀጠልህ ነው" ይለናል የእንግሊዙ ታላቅ መሪ ዊንስተን ቸርችል።

ሁሌም ፀሀይ ብትወጣ ወይ ጨለማው ቢተካ አበቃ ማለት አይደለም! ነገ መልሶ ይነጋል፤ ያንተም ህይወት ውስጥ ሁሉም ይቀጥላል፤ ያበቃ የመሰለህ ነገር ሁሉ መልሶ ሲስተካከል ታየዋለህ፤ ተስተካከለህ ብለህ ግን አትዘናጋ ስኬት የቤት ኪራይ ነው ያውም በየቀኑ የምትከፍለው፤ ወዳጄ ሁሌም የማይቆም ጥረት እያደረክ መቀጠል አለብህ!

ተዓምረኛ የተባረከ ሀሙስ ተመኘንላችሁ
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
2.4K views07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-12 08:26:49
አልፋችሁ ሂዱ!

ፈጣሪ በዚህች ምድር ላይ እንድትኖሩ የሰጣችሁ ይህ ሕይወት በራሱ፣ ምንም ነገር ሳይጨመርበት እጅግ ውብ ነው፡፡ ይህንን ውብ የሆነ ሕይወት ምንም ነገር እንዲያበላሽባችሁ አትፍቀዱ፡፡

• በአንድ ሰው ተግባር ብቻ ይህ ውብ የሆነ ሕይወት እንዳይበላሽ ሰዎች ከሚያደርጉባችሁ ወይም ካላደረጉላችሁ ነገር አልፋቸሁ ሂዱ!

• በአንድ ነገር አለመሳከት የተነሳ ውስጣችሁ ወድቆ ይህ ውብ የሆነ ሕይወት እንዳይበላሽ ጊዜያዊ ከሆነው የመሳካትና ያለመሳካት ገጠመኝ አልፋችሁ ሂዱ!

• ሰዎች ከሚያደርጉብን፣ ከሚያደርጉልንና ከከለከሉን ነገሮች ይልቅ በሕይወት መኖር በራሱ በብዙ እጥፍ ይበልጣል፡፡ ከተሳካውና ካልተሳካው ሁኔታ ይልቅ በሕይወት መኖር በራሱ በብዙ እጥፍ ይበልጣልና ከሁኔታዎች አልፋችሁ ሂዱ!

በሕይወት መኖር ስለተፈቀደልን ብቻ ፈጣሪን በማመስገን በደስታ ለመኖር በቂ ምክንያት አለን፡፡

መልካም ቀን!
2.9K views05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ