Get Mystery Box with random crypto!

Warning Attentions ማሳሰቢያ ! ትኩረት ! እባክህ ወንድሜ Fias ስለሚባል ድርጅት | Ethio Job Vacancy

Warning Attentions ማሳሰቢያ ! ትኩረት !
እባክህ ወንድሜ Fias ስለሚባል ድርጅት የምታውቀው መረጃ ካለ ብታካፍለን?
ወንድሜ Fias የሚባል ድርጅት እውነት መስሎኝ ገንዘብ ከፍዬ ተጭበረበርኩ ለማን አቤት ልበል?
መሰል ጥያቄዎች ከተለያዩ ግለሰቦች ይደርሱኛል።
ለማንኛውም ስለ Fias ድርጅት ከሳምንታት በፊት ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ሕገ ወጥ ስለመሆኑና የኢትዮጵያ ፋይናንሻል ኢንተለጀንስ አገልግሎት ጉዳዩን ይዞ እየተከታተለ መሆኑን አሳውቆ ነበር።
የእኔን እይታና ምልከታ እንደሚከተለው ለመግለጽ እወዳለሁ።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ አንዳንድ ግለሰቦች Fias የሚል እና መሰል ዌብሳይቶችን በመክፈት ብዙ ሰዎችን እያጭበረበሩ ይገኛሉ።
የሚገርመው እናንተ ትክክለኛ ነው ዋው ይሔማ ምርጥ ቢዝነስ ነው ብላችሁ እንድታምኑ VIP ደረጃ እንድታሳድጉ ክፍያ ይጠይቋችኋል። ከዚያ የተወሰነች ብር ወደ አካውንታችሁ ያስገባሉ። አሁንም የከፈላችሁትን የብር መጠን ያክል ሳታወጡ(ሳይከፈላችሁ) ወደቀጣይ VIP ደረጃ ማሳደግ አለባችሁ ይሉና ሌላ ከእናንተ ተጨማሪ ክፍያ ይጠይቃሉ።
እያለ እያለ እናንተ የከፈላችሁትን ብር መጠን ሳትቀበሉ ከዚህ መጠን በላይ ማውጣት አትችሉም፣ ተጨማሪ ገንዘብ ለማውጣት በእናንተ ውስጥ ሌላ ሰው ከፍሎ የሚሚመዘገብ ሰው መጋበዝ አለባችሁ። አለበለዚያ ተጨማሪ ክፍያ መጠየቅ አትችሉም ብሎ ያግዳችኋል።

እንዳትጭበረበሩ ተጠንቀቁ።
100% የተጭበረበሩና በየፖሊስ ጣቢያው ለክስና አቤቱታ የሚመላለሱ በርካታ የተጭበረበሩ ሰዎች ስላሉ እንጂ የእነርሱን ስራ ለማጣጣል ፈልጌ አይደለም። የሚገርማችሁ የቴሌግራም ቻናል ይከፍሉና የተወሰኑ ግለሰቦች የማሳመን (lobbyist) ሥራ ይሰራሉ፤ ዋው የሚገርም ቢዝነስ ነው 8,000፣ 10,000 ፣ 20,000 ፣ የሌለ የብር መጠን እየጠቀሱ ወደ አካውንቴ ገብቷል እናንተም ኑ አብረን እንስራ፤ እከሌ የሚባል ኤጀንት ምርጥ ሰው ነው በቀላሉ ከፍዬ VIP ደረጃዬን ቶሎ አሳድጎልኝ የሌለ ብር እያገኘሁ ነው የሚሉ የማባበያ፣ የማሳመን ስራ ይሰራሉ። እንዴ ትሉና እናንተም ኤጀንት ለተባለው ከ1,000 ብር ጀምሮ እስከ 30,000 ብር ትከፍሉና እድለኛ ከሆናችሁ የተወሰነች ብር ሊያስገቡላችሁ ይችላሉ ነገርግን እናንተ የከፈላችሁትን የኢንቨስትመንት ብር መጠን ግማሹን እንኳን ማውጣት አትችሉም። ልክ እንደ Fias, hulu, workxon, የመሳሰሉት ተመሳሳይ ፕላትፎርም ያላቸው በየሶሻል ሚዲያው ኑ ገንዘብ ይስሩ እያሉ የሚያደነቁሩ ናቸው።
ለማንኛውም ከዚህ በፊት እውነት መስሏችሁ የተጭበረበራችሁ ክፍያ የፈፀማችሁበትን መረጃችሁን ለፖሊስ ማሳወቅና ሪፖርት ማድረግ ትችላላችሁ።
Fias የ Tians የአጭበርባሪው እህት ኩባንያ! ምንም ልዩነት የላቸውም፤ ሁለቱም ስራቸው ግለሰቦችን ማጭበርበር እንጂ መጥቀም አይደለም።
Period!