የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ በጋሞ፣ ጎፋ፣ ወላይታ፣ ጌዲዮ፣ ደቡብ አሞ እና ኮንሶ ዞኖች እንዲሁም አሌ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ባስኬቶ እና ደራሼ ልዩ ወረዳዎች በምርጫ አስፈጻሚነት ለነበራችሁ ተሣትፎ በቅድሚያ እያመሰገንን በቀጣይ በእነዚህ አካባቢዎች ለሚካሄደው ሕዝበ ውሣኔ በምርጫ አስፈጻሚነት በድጋሚ ለመሣተፍ ፍቃደኛ መሆንዎን እንዲያረጋግጡልን እንጠይቃለን።
ፍቃደኛነትዎን ለመግለጽ ከላይ የተጻፈው መልዕክት (text message) በእጅ ስልክዎ ሲደርስዎ አንድን ተጭነው ይመልሱ፡፡ መልዕክቱ ከታች ከተያያዘው ማስፈንጠሪያ (Link) ጋር ከደረሰዎ የሚጠየቁትን ጥያቄዎች በመመለስ ፍቃደኝነትዎን ያሳዩ።
http://nebecertificate.org.et/recruitment
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ