Get Mystery Box with random crypto!

ነዳጅ ላኪ ሀገራት አቅርቦት ለመቀነስ መወሰናቸውን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል! የዓለማችን ግዙፍ | EthioipaNews

ነዳጅ ላኪ ሀገራት አቅርቦት ለመቀነስ መወሰናቸውን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል!

የዓለማችን ግዙፍ ነዳጅ ላኪ ሀገራት ያልተጠበቀ የምርት ቅነሳን ይፋ ካደረጉ በኋላ የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል። ያልተጣራ ድፍድፍ ነዳጅ በበርሚል ከ5 ዶላር ወይም ከ7 በመቶ በላይ ጭማሪ አሳይቷል። ይህንኑ ተከትሎ ያልተጣራ ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል ከ80 ዶላር ወደ 85 ዶላር ከፍ ብሏል።

ጭማሪው የተከሰተው ሳዑዲ አረቢያ፣ ኢራቅ እና በርካታ የባህረ ሰላጤው ሀገራት በቀን ከአንድ ሚሊዮን በርሜል በላይ ከምርታቸው ላይ እየቀነሱ መሆናቸውን ተከትሎ ነው። ሩሲያ ዩክሬንን በወረረችበት ወቅት የነዳጅ ዋጋ ጨምሮ የነበሩ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ግጭቱ ከመቀስቀሱ በፊት ወደነበረበት ተመልሷል። ይሁን እንጂ አሜሪካ የነዳጅ ዋጋን ዝቅ ለማድረግ አምራቾች ምርታቸውን እንዲጨምሩ ስትጠይቅ ቆይታለች።

ባለፈው አመት ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መደረጉ በመሰረታዊ ምርቶች ላይ ግሽበት እንዲፈጠር ማድረጉ ይታወሳል።የዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ የጸጥታ ምክር ቤት ቃል አቀባይ ስለ ቅርብ ጊዜ የምርት ቅነሳ በሰጡት መግለጫ ቅነሳው በአሁኑ ጊዜ ጠቃሚ ነው ብለን አናምንም ይህንንም ግልፅ አድርገናል ብለዋል። የምርት ቅነሳው በኦፔክ የነዳጅ ዘይት አምራቾች አባላት ሀገራት እየተደረገ ይገኛል።

የኦፔክ አባል ሀገራት ከዓለም ድፍድፍ ዘይት ምርት 40 በመቶውን ድርሻ ይይዛሉ። ሳዑዲ አረቢያ በቀን 500,000 ፣ ኢራቅ 211,000 በርሜል ያልተጣራ ድፍድፍ ነዳጅ ምርትን እየቀነሱ ይገኛል። የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ፣ ኩዌት፣ አልጄሪያ እና ኦማን ቅነሳ በማድረግ ላይ ናቸው። የሳውዲ ኢነርጂ ሚኒስቴር ባለስልጣን እርምጃው የነዳጅ ገበያውን መረጋጋት ለመደገፍ የታለመ የጥንቃቄ እርምጃ ማለቱን የሳውዲ ፕሬስ ኤጀንሲ ዘግበል።

[ዳጉ ጆርናል]
@EthioipaNews