Get Mystery Box with random crypto!

የዓለማቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት መመስረቻ ስምምነት ፈራሚዋ ደቡብ አፍሪካ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚ | EthioipaNews

የዓለማቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት መመስረቻ ስምምነት ፈራሚዋ ደቡብ አፍሪካ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቱን ለ"ብሪክስ" አገራት የመሪዎች ጉባኤ ሲሄዱ እንደምታስተናግዳቸው ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ ናለዲ ፓንዶር በኩል አስታውቃለች።

የዓለማቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ፑቲን በዩክሬን "የጦር ወንጀል ፈጽመዋል" በማለት የእስር ማዘዣ ማውጣቱን ተከትሎ፣ በቀጣዩ ነሐሴ የ"ብሪክስ" አገራት የመሪዎች ጉባኤ አዘጋጇ ደቡብ አፍሪካ አቋሟ ምን እንደሚኾን በጉጉት ሲጠበቅ ነበር። ደቡብ አፍሪካና ሩሲያ በሌሎች አገራት ግፊት በድንገት ጠላት ሊኾኑ አይችሉም ያሉት ፓንዶር፣ ፑቲንን በጉባኤው እንዲገኙ እንደተጋበዙ ተናግረዋል። በዓለማቀፉ ፍርድ ቤት ስምምነት መሠረት፣ ደቡብ አፍሪካ ፑቲን ግዛቷን ከተረገጡ አስራ ለፍርድ ቤቱ የማስረከብ ግዴታ አለባት። "ብሪክስ" በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉት ኃያላኑ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ሕንድና ብራዚል የመሠረቱተ ቡድን ነው።

@EthioipaNews