Get Mystery Box with random crypto!

ወንድሜ! ራስ ወዳድነት የታወረ የበላይነትን የመሻት መክንያቱ ነው።የወንድምህ የበላይ የመሆን ፍላጎ | ስብዕናችን #Humanity

ወንድሜ! ራስ ወዳድነት የታወረ የበላይነትን የመሻት መክንያቱ ነው።የወንድምህ የበላይ የመሆን ፍላጎት ጎሳና ነገድ እንዲፈጠር ምክንያቱ ሆነ፤ጎሳና ነገድ ደግሞ እርስ በርስ መጋደልና አንዱን መጨቆን አስከተለ።

ፍቅር በእዉቀት ሃይል ታምናለች ፤ ፍትህ ደግሞ በጨለማው አላዋቂነት ላይ ትሰለጥናለች። ታላቋን ባቢሎን ካጠፍ ፣የኢየሩሳሌምን መሰረቶች ካናወጠ፣ሮምን ከፍርስራሿ ጋር ካስቀረዉ ከዚያ ሰልፍ ከሚያቀብል ሥልጣን፣አላዋቂነትና ጭቆናን ከሚያንሰራፋ የሥልጣን ሃይል ጋር ፍፁም ትቃረናለች። ዳሩ ታላላቅ ሰዎች ተብለው ሲጠሩ የኖሩ እንዲህ አይነቶቹ ወንጀለኞች ናቸው።

አኔ የምቀበለው ብቸኛ ስልጣን በተፈጥሮ ሕግ ላይ የተመሰረተዉን ፍትሕና እሱን የሚቀበለውን እዉቀት የያዘውን ብቻ ነው። የራሱን ጉዳይ ብቻ የሚያቅፍ ባለሥልጣን ላይ ፍትህ ምን የምታደርግ መስልሃል?

አንተ ወንድሜ ነህ፤ስለዚህ እወድሃለሁ! ፍቅር ደግሞ ታላቅ ፍትህ ነው! ከየትኛውም ጎሳ ወይም ነገድ ብትመጣ  ለአንተ የምሰጠው ፍትህ "ፍቅር" ብቻ ነው።

ፍቅር ስለ ራስ ብቻ ማሰብ ሳይሆን ስለሌላውም ማሰብ ነው ። ፍቅር ሲታመም ሁሉም ነገር ይታመማል። ስብእናም አስተሳሰብም  ስሜትም ይታመማል ። ወዳጀ ሆይ አንተም አስተውል ያንተ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ድረስላቸው ከራስህ ከፍታ ይልቅ ለሰዎችና ለሃገርህ ከበሬታ ይኑርህ ፡፡የወደቁትን አንሳ ያዘኑትን አጽናና ፍቅር ስጣቸው እርሱ ከሁሉም ይበልጣልና!!

                     ካህሊል ጂብራን

ውብ አሁን

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot