Get Mystery Box with random crypto!

ፈገግታ መንፈስን የሚያነቃ የተቀመመ መደሃኒት ነው ብንል ውሸት አይሆንም ፣ በፈገግታ የታጠነ ገፅ | ስብዕናችን #Humanity

ፈገግታ መንፈስን የሚያነቃ የተቀመመ መደሃኒት ነው ብንል ውሸት አይሆንም ፣ በፈገግታ የታጠነ ገፅ መመለከት ሰፍሮብን የነበረውን የብሽቀት ጋኔን ድራሽ አባቱን ያጠፋል ። ሰው ፈገግ እያለ በጥፊ ቢመታህ እንኳን ለፈገግታው እንጂ ለጥፊው ምላሽ አትሰጥም እመነኝ ቢያምህም ፈገግ ትላለህ ፣ ፈገግታ ሀያል ነው ፣ ፈገግታ የሀሴት መርጫ ስሪንጅ ነው ፤ ፈገግታ ብርሃናማ ቀለማት መሳያ ሸራ ነው .... እስቲ ፈገግ በሉ !!!

ፈገግታ ካለህ ጠላት አይኖርህም፣ ሞት እንኳን አፍጦ ቢመጣብህ ፈግግበት ፣  ፈገግታ ነፍስን ይከፍታል ፣ እርካታና መዝናናትን ይፈጥራል። የውቅያኖስ ንፋስ ጭጋግን እንደሚበታትነው ሁሉ ፈገግታም ውስጥህ ያለውን ሀዘንና ጥላቻን ይገፋል። ለሰፊው ባህርም የመሬት ቀዝቃዛ ንፋስ ፈገግታው ነው፣ ባህር በንፋስ ላይና ታች እያለ ካልተጫወተ ውበቱን ያጣል፣ ሃይለኛ ሽታም ይፈጥራል። የሰው ልጅም መጥፎ ጠረን የሚጸዳው በፈገግታው ነው።

ደስተኛ ልብ ፊትን ያፈካል፣ የልብ ሀዘን ግን መንፈስን ይሰብራል እንዲል ቃሉም፣ ፈገግታ ሱና ነው እንዲል ሀዲሱም። በዓለም ላይ የሌለን ነገር ሁሉ ተደምሮ ያለንን ነገር አይበልጠዉም፣ሁሌም ለዓለም ሳቁ ፣ ስትስቁ ያን ጊዜ ውብ ናችሁ።

ዛሬን ትላንት አልኖርነውም ፣ ወደፊትም ፈፅሞ አናገኘውም ፣ ዛሬን በሃዘን አትግደሉ ፈገግታ ስጦታ ነዉ፣ፈገግ ስትሉ ኑሩልን

ለፍቅራችን፣ ውብ ቅዳሜ!

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot