Get Mystery Box with random crypto!

አንዳንዴ ለምናደርገው ነገር ሁሉ ምላሽ ስለምንሻ ነገሮች እንዳሰብናቸው ካልሆኑ ደስታችንን ያጎድሉብ | ስብዕናችን #Humanity

አንዳንዴ ለምናደርገው ነገር ሁሉ ምላሽ ስለምንሻ ነገሮች እንዳሰብናቸው ካልሆኑ ደስታችንን ያጎድሉብናል። ሰዎችን ሳይወዱን መውደዱን አናውቅበትም፤ ብናውቅበት እንኳን ሞኝነት ይመስለናል፣ሰዎች ይቅር ሳይሉን ይቅር ማለቱን አንችልበትም ፤ ብንችልበት እንኳን ገር የሆንን ይመስለናል።ሰዎች ሳያከብሩን ማክበሩን አንችልበትም፤ ብንችልበት እንኳን የተዋረድን ይመስለናል።

ስንሰጥ ምላሽ ካልጠበቅን ሰዎች ክፉ ቢሆኑብን ግር አይለንም። ስንወድ ለመወደድ ብለን ካልሆነ ፤ ፍቅራችን ሲገፋ አይከፋንም፣ስንረዳ ለክፉ ቀናችን ብለን ካልሆነ፤ ሰዎች እርዳታቸውን ሲነፍጉን አይደንቀንም። የምናደርገው ነገር ሁሉ ከልባችን ሲሆን፤ ደስታችን ሌሎች በሚሰጡን ምላሽ ላይ አይወሰንም።

ስትሰጥ መስጠት ስላለብህና ስለሚያስደስተህ ብቻ እንጂ በምላሹ ግብር ጠብቀህ መሆን የለበትም፣ የዜኖች የህይወት ፍልስፍና ሚጠቅሰው አንዱ ነገር ይህንን ነው! ምንም ነገር ቢያደርጉ ማድረግ ስላለባቸው እንጂ ገና ለገና ይሰጠኛል ብለው ስላልሆነ! ሰጥተን ከጠበቅን መስጠታችን ትርጉም አልባ ነው፣ ምላሽ ጥበቃ ከሆነ የነፍስያ [Ego] እንጂ፥ እውነተኛ መስጠት አያደርገውም።

ስጥ፣ ስትሰጥ ግን ምስጋናን ፈልገህ አትስጥ። ስጥ፣ ስትሰጥ ግን ምላሽን ጠብቀህ አትስጥ።ስጥ፣ ስትሰጥ ግን ዛሬ መስጠትህ ነገ ትርፍ እንደሚያመጣልህ አስበህ አትስጥ፣የሌላውን ምላሽ ሳትጠብቅ ትክክለኛውን ነገር ማድረግ ከቻልክ ከራስህ ላይ ትልቅ ቀንበር አንስተሀል ማለት ነው።

ውብ ምሽት

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot