Get Mystery Box with random crypto!

ገና ስትፀነስ በሕይወት ዘመንህ ትልቅ ቦታ የመድረስ ምርጫ ተመነሻውም የተሰጠህ መሆኑን ተገንዘብ። | ስብዕናችን #Humanity

ገና ስትፀነስ በሕይወት ዘመንህ ትልቅ ቦታ የመድረስ ምርጫ ተመነሻውም የተሰጠህ መሆኑን ተገንዘብ። ፈጣሪ ሕይወት ሰጥቶኻል፥ ሕይወትህን ደርዝ የምታስይዘው ግን አንተ ነህ። ቢያንስ መሞከር አለብህ። ወኔ ማለት መለወጥ እምትችለውን ነገር መለወጥ መቻል ነው። እረኛ እንድሆን ተፈርዶብኛል ካልክ እረኛ ሆነህ ትቀራለህ።…" (26)

ሕይወት ትርጉምና እና ዓለማ ያላት እንደሆነች ይሰማኛል። ልብህን ማድመጥ እንድትማር ነው ይህን ሁሉ ላንተ መንገሬ። ልብህ የፈቀደው ነገር ዕጣፈንታህ ነው። ፈጣሪ ያን ፈቃድ በልብህ ያሳድረዋል፣ እንግዲህ ያንተ ሥራ የሚሆነው ልብህ የሚነግርህን መከተል ነው። ዛሬ፥ ልቤ የሚያዘውን የምከተል በመሆኔ ነጻ ሰው ነኝ። የችግሮቼ ሁሉ ምንጭ እኔው ራሴ ነበርኩ። ይህንንም ለመረዳት ዓመታት ፈጅቶብኛል።" (57)

"ኀሠሣ" በሕይወት ተፈራ

ውብ ምሽት

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot