Get Mystery Box with random crypto!

ሐና! 'አቤት ቲቸር!' ድንገት በመጠራቷ ደንግጣ ታፈጣለች። የክፍላችን ጎበዝ ተማሪ ናት ሐና… | ስብዕናችን #Humanity

ሐና!

"አቤት ቲቸር!" ድንገት በመጠራቷ ደንግጣ ታፈጣለች። የክፍላችን ጎበዝ ተማሪ ናት ሐና…

"የሰው ልጅ መሠረታዊ ፍላጎት ምንድ ነው?" ይጠይቋታል።

"ምግብ…ልብስ…መጠለያ" መለሰችው እንላለን እኛ በሽክሹክታ። ገና ትላንት ነው አከባቢ ሳይንስ መምህራችን ያስተማረችን።

"አይደለም! በጭራሽ አይደለም! ሳይንሱ እውነታውን ጋርዶብናል። እንጀራ ማን ሕሊና ውስጥ ቦታ ሰጠው? 'የምድር ፍሬ፣ የወንዝ ውሃ ይሙላህ' የተባለን ሆድ ማነው የሰው መሠረት ያደረገው? የለም! በየጫካው በየዱሩ የሚኖሩ ወገኖቻችን ርቃናቸው ጌጣቸው ነው፤ ቤትስ ቢሆን - የሰው ልጅ ተንኮሉን ሊከልል፣ ለግርዶሹ ስም አወጣ።

ልጆች ልብ በሉ…የሰው መሠረታዊ ፍላጎት አንድ ነው፣ እሱም ፍቅር ነው። ካለፍቅር ሰው የቁም ሙት ነው። ሰው ሰውን ሲያፈቅር፣ ሰው አምላኩን ሲያፈቅር፣ ሰው አገሩን ሲያፈቅር፣ ሰው እውነትን ሲያፈቅር፣ ሰው ነፃነትን ሲያፈቅር ነው ሕያው የሚሆነው። ሰው ነገውን ሲወድ፣ ነገውን ሲያፈቅር ነው ነገ ለሚፈጠር ትውልድ ፍቅር የሚያወርሰው…እስትንፋሱ የሚቀጥለው።"

"ዶክተር አሸብር፣
የታረሙ ነፍሶች"115
በአሌክስ አብርሃም

ውብ ምሽት

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot