Get Mystery Box with random crypto!

ጌታዬ! 'Algorithm' የሚባል ነገር አለ! በአጭሩ አዘውትረህ የምትመለከታቸውን ቪድዮዎች፣ ዜና | ስብዕናችን #Humanity

ጌታዬ! "Algorithm" የሚባል ነገር አለ! በአጭሩ አዘውትረህ የምትመለከታቸውን ቪድዮዎች፣ ዜናዎች፣ መረጃዎች እና ፅሁፎች እነዚህ ማህበራዊ ሚድያዎች በደንብ ካጠኑ እና ከመዘገቡ በኃላ ማንነትህን የሚያውቁበት መንገድ ማለት ነው። ለምሳሌ "Youtube" ከፍተህ አንድ ሁለት ቪድዮ ስለ የሆነ ነገር ካየህ በቀጣይ "YouTube" ላይ ስትገባ ስለእዛ ጉዳይ ተመሳሳይ 100 ቪድዮዎችን " Recommended" ላይ ያመጣብሃል! "Facebook" ላይ ስለ አንድ ጉዳይ በተደጋጋሚ የምታነብ ከሆነ በቀጣይ ስትገባ ስለእዛ ጉዳይ ብዙ መረጃዎችን ያዘንብብሃል! የአንድ አካባቢ ሰዎችን ጓደኛ ካደረክ በቀጣይ እዛ አካባቢ ያሉ ብዙ ሰዎችን ጓደኛ እንድታደርግ ያመጣልሃል! ለምሳሌ "Tiktok" ላይ ገብተህ ተገላልጠው የሚደንሱ ሴቶችን አንድ ሁለት ቪድዮ ካየህ ከዛ በኃላ "tiktok" ተቆጥረው የማያልቁ ተመሳሳይ ቪድዮዎችን ያዥጎደጉድልሃል! የ "Tiktok" "Algorithm" ደግሞ ይለያል! ፍላጎትህን ለመለየት አንድን ቪድዮን ለምን ያህል ደቂቃ እንዳየህ ሳይቀር ያሰላሉ!

ሰዎቹ እንዲህ ይላሉ!

"...ስራችን የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎችን ልክ እንደ "ማሽን/ኮምፒተሮች" "program" ማድረግ ነው። ሰዎች አዲስ ማንነት እና ባህሪን እንዲላበሱ ማድረግ ነው። አንተ ለኛ ልክ እንደ የላብራቶሪ አይጥ ነህ። ዓለም ላይ ሁለት ኢንደስትሪዎች ብቻ ተጠቃሚዎቻቸውን "users" ብለው ይጠራሉ። አንደኛው የአደንዛዥ እፅ ኢንደስትሪ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የማህበራዊ ሚድያው ኢንደስትሪ ነው። ሌሎች ኢንደስትሪዎች ተጠቃሚዎቻቸውን "Customers(ደንበኞች)" ወይንም "Buyers(ገዢዎች)" ነው የሚሉት!
"Refresh" ባደረክ ቁጥር አዲስ ዜና፣ አዲስ መረጃ፣ አዲስ ፎቶ እንድታይ ነው የሚፈልገው። ምክንያቱም ግባቸው አንተን ከስልክህ አጣብቆ ማቆየት ነው።

እቅዳቸው ተጠቃሚዎቻችን "perfection(ፍፁማዊነት)" እና "Social Approval(ማህበራዊ ተቀባይነት)" እንዲሰማቸው ማድረግ ነው።አንዲት ሴት ዝም ብላ አንድ የራሷን ፎቶ ምንም ሳትጨምርበት ብትለጥፍ የምታገኘው "like" ያንሳል። ነገር ግን የተለያዩ የውበት መጨመርያ ፊልተሮችን ተጠቅማ ፎቶዋን ብታሳምር፣ ሻዶው ብትጨምር፣ የቆዳ ቀለሟን ፈካ ብታደርግ እና ፊቷ ላይ ያለውን ብጉር ብታጠፋ የምታገኘው "like" እና "comment" ይበዛል። "...ቆንጆ፣ ስታምሪ፣ ከንፈርሽ፣ ፊትሽ..." ምናምን የሚሏት ሰዎች ይጨምራሉ። ግባችን የተወደደች፣ ሰዎች በውበቷ የሚቀኑባት፣ ከሌሎች ጓደኞቿ የተሻለ ተከታይ እና "social approval" ያላት ሴትን መፍጠር ነው። የሚያሳዝነው ልጅቷ ያንን ሁሉ "comment" እና "like" ያገኘችው እሷን ሆና አይደለም! የውሸት/የተጋነነ ማንነትን እንድትፈጥር አድርገናታል። ትክክለኛ መልኳን እና ማንነቷን እንድትጠላው አመቻችተናል! ለዛም ነው ብዙ ሴቶች ጭንቀት እና የአዕምሮ መታወክ የሚያጋጥማቸው። የሚለጥፉትን ፎቶ ለመምሰል ብዙ ሴቶች ቀዶ ጥገና እስከማድረግ ደርሰዋል!ማህበራዊ ሚድያዎች ዋነኛ አላማቸው የተጠቃሚዎችን "Social Media Engagement (ማህበራዊ ሚድያ ቆይታ)" ማሳደግ ነው። በአሁኑ ሰዓት ወደ 214 ሚልዮን የሚጠጉ ሰዎች የማህበራዊ ሚድያ ሱሰኞች ሆነዋል። የማህበራዊ ሚድያ ሱስ ከ "Cocaine" ሱስ ጋር አንድ ነው። የሰው ልጅ አዕምሮ ውስጥ "Dopamine" የሚባል የደስታ ስሜትን የሚረጭ ሆርሞን አለ! ሱሰኛ ሰዎች ሲጋራ፣ ኮኬይን ወይም ሌላ አደንዛዥ እፅን ሲያስቡ አዕምሮዋቸው "Dopamine" ይረጫል፣ ደስታ ይሰማቸዋል። ማህበራዊ ሚድያም እንደዛ ነው! ማህበራዊ ሚድያን ከፍተህ ለማየት እንድትንቀለቀል የሚያደርገህ ወደ ሰውነትህ የሚረጨው "dopamine" ነው! በአማካይ ሰዎች በቀን 2 ሰዓት ማህበራዊ ሚድያ ላይ የሚጠቅማቸውንም የማይጠቅማቸውንም ነገር በማየት ግዜያቸውን ያጠፋሉ! ይህ ማለት ከአጠቃላይ እድሜያቸው ድፍን አምስት አመታትን ያባክናሉ ማለት ነው! አሁን ላይ ከሶስት ፍቺዎች ውስጥ አንዱ ከማህበራዊ ሚድያ ሱስ ጋር በተያያዘ ሆንዋል!...." እያሉ ይቀጥላሉ! ከዚህ በላይ ከቀጠልኩ ሙሉ ዶክመንተሪውን መጨረሴ ነው!

ማጠቃለያ!

ይህንን ሁሉ ካወሩ በኃላ እንደ መፍትሄ ከሚያስቀምጧቸው ሃሳቦች ውስጥ አንዱን ላስቀምጥ እና ልውጣ!

"Notification" የሚባል ነገርን "off" ማድረግ! በየደቂቃው ስልክህ ላይ "እንትና አዲስ ፅሁፍ ለጠፋ፣ እንትና አዲስ ፎቶ ለቀቀች፣ እገሌ እንዲህ ሆነ..." እያሉ "Notification" የሚልኩልህ ትኩረትህን ለመሳብ ነው። የቆይታ ግዜህን ለማሳደግ ነው። ያንተን "Algorithm" በደንብ ቀርጥፈው ስለበሉት ነው። አንተ ተቆጣጠራቸው እንጂ እነሱ እንዲቆጣጠሩህ አታድርግ! ማየት ስትፈልግ እራስህ ግባ እንጂ "Notification" አይቆስቁስህ!

ጌታዬ! ተጨማሪ መፍትሄዎቹን ማወቅ ከፈለክ ዶክመንተሪውን እይ! ትጠቀማለህ፣ ታተርፋለህ፣ ብዙ ነገር ትባንናለህ! በይበልጥ ማንበብ ከፈለክ እዛው ዶክመንተሪ ላይ ቃለ መጠይቅ ከሚደረግላቸው ሰዎች መካከል "Jaron Lanier" የሚባል ፀዴ ሰውዬ የፃፈው መነጋገርያ የሆነ "Ten Arguments for deleting your social Media accounts right now!"የሚል መፅሃፍ አለ! አንብበው! ከፈለክ እንደ ሁል ግዜው በውስጥ መስመር አቀብልሃለሁ!

ፀዴ ሰንበት ይሁንልህ፣ ፈታ ብለሽ አምሺ!

መልካም ምሽት!

ወንድዬ እንግዳ

#በሀሳቡ ላይ ሀሳብ አለኝ የሚልም ካለ ለመስማት ዝግጁ ነን

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@Nagayta