Get Mystery Box with random crypto!

የሰንበት ረፋድ ምርጥ ቀደዳ!! . . እንደምነህ ጌታዬ? እንዴት ነሽ እ | ስብዕናችን #Humanity

የሰንበት ረፋድ ምርጥ ቀደዳ!!

.
.
እንደምነህ ጌታዬ? እንዴት ነሽ እናቴ? የዚህ ሳምንት ቀደዳችን ደግሞ ይለያል! የፀዳ ነው! ይጠቅምሃል አንብበው!
.
.
ጠዋት ስትነሳ ግራ እግርህ ይስራ አይስራ ሳታረጋግጥ መጀመርያ ስልክህን አንስተህ "facebook" ቼክ ታደርጋለህ። ሽንት ቤት ቁጭ ብለህ "Instagram" ላይ ቆንጆ ቆንጆ ሴቶችን "scroll" እያደረክ ትኮሞኩማለህ። ስልክህ ካርድ ከሌለው ቶሎ ገዝተህ "ማህበራዊ ሚድያ" ላይ እስክትጣድ ያንቀለቅልሃል! የሆነ ፅሁፍ ለጥፈህ ምን ያህል "like" እና "comment" እንዳገኘህ ለማወቅ በየደቂቃው "Refresh" እያደረክ ታያለህ። የለጠፍሽው ፎቶ ምን ያህል "like" እንዳገኘ ለማወቅ ያቅበዘብዝሻል። የጠበቅሽውን ያህል "Reaction" ካላገኘ ተበሳጭተሽ ፎቶውን ታጠፊዋለሽ። "ማህበራዊ ሚድያ" ላይ የምታውቃቸው ሰዎች ለተወሰነ ግዜ ሲጠፉብህ ይጨንቅሃል። ስማቸውን ሳይቀር ፅፈህ ትፈልጋቸዋለህ። ፎቶሽ ላይ ሁል ግዜ "...የኔ ቆንጆ፣ የኔ ልዕልት፣ ስታምሪ.." ምናምን እያለ "comment" የሚያደርግልሽ ልጅ በሆነ አጋጣሚ አዲስ የለጠፍሽው ፎቶ ላይ "comment" ካላደረገ ያሳስብሻል። የለጠፍከው ፎቶ ወይም ፅሁፍ "like" ብዙም ካላገኘ እራስህ "like" ታደርጋለህ። መስሪያ ቤትህ በሰጠህ ኮምፒውተር "facebook" ትጠቀማለህ። ከሰዓት ማስገባት ያለብህ ወሳኝ ስራ እያለ አንተ "tiktok" ላይ ትጣዳለህ። ጠዋት ተነስተህ ወደ ስራ መሄድ እንዳለብህ እያወቅ ማታ ላይ አንድ ሰላሳ ደቂቃ "Tiktok" ልይ ብለህ እስከ ለሊቱ 9 ሰዓት ድረስ ተጥደሃል። በንጋታው ስራ ረፍዶብሃል ወይም "Tiktok" ላይ ለሊቱን ሙሉ ተጥደህ በቂ እንቅልፍ ባለማግኘትህ ምክንያት ጠዋት ታክሲ ውስጥ አንቀላፍተሃል፣ ቀንህ ተጦልቧል። አንድ ቪድዮ "YouTube" ላይ አያለው ብለህ የገባህ ሰውዬ ሳታስበው "30 ቪድዮ" አይተሃል። "Facebook" ላይ ተጀናጅናችሁ፣ የባጥ የቆጡን ሳትተፋፈሩ አውርታችሁ፣ ተዋዳችሁ፣ ሳትገናኙ እዛው "Facebook" ላይ ተጣብሳችሁ በመጨረሻም በአካል ስትገናኙ ተሽኮርምመሃል፣ አፍረሃል፣ መሬት መሬት አይተሃል፣ ተንተባትበሃል። ከጓደኞችህ ጋር ምሳ ለመብላት ተገናኝታችሁ ምግቡ እስኪመጣ በፊት ስለ ውሏቹ፣ ገጠመኞቻችሁ፣ ስለ ቤተሰቦቻችሁ፣ ስለ ስራችሁ ምናምን በሰፊው የምትቀዱ ሰዎች አሁን ሁላችሁም ስልካችሁ ላይ አቀርቅራችኃል። እየበላችሁ ሳይቀር ከስልኩ ጋር የሚበላ ከመካከላችሁ አይጠፋም። ስልክህን አብዝተህ ከመውደድህ የተነሳ ትራስህ ስር ወሽቀኸው ትተኛለህ። መብራት ሲጠፋ መጀመርያ የሚያሳስብህ ምግብ ማብሰል አለመቻልህ፣ ቴሌቪዥን ማየት አለመቻልህ ወይም ጨለማ መሆኑ ሳይሆን ስልክህን ቻርጅ ማድረግ አለመቻልህ ነው። ስልክህ ላይ ተጥደህ በመዋልህ ምክንያት ለሚስትህ የምትሰጣት ግዜ ቀንሷል፣ የምትተኙበት እና የምትነሱበት ሰዓት ተለያይቷል፣ ከልጅህ ጋር የምትጫወትበት ግዜ ወርዳል። ማህበራዊ ህይወትህ ተመቷል። ሰዎችን በአካል አግኝተህ ከምታወራቸው ይልቅ በ "Telegram" ወይም "Messanger" ብታወራቸው ይቀልሃል፣ በአካል መገናኘት ይጨንቅሃል። ጆሮህ ላይ የምትተክለው "Earphone" መገለጫህ እስኪሆን ድረስ ተጣብቆብሃል። የ "Internet' መቋረጥ ሞት እስኪመስልሽ ድረስ ያስጨንቅሻል። ብቻ ምን አለፋህ ስልክህ ህይወት ሆኗል!

አባዬ! ወደ ዋናው ጉዳይ ላምጣህ!

ዓለማችን ካላት ወደ 7 ቢልዮን ከሚገመት ህዝብ ቁጥር ውስጥ ወደ 3 ቢልዮን የሚሆነው ማህበራዊ ሚድያ(facebook, Instagram, snapchat, twitter, tiktok.....) ይጠቀማል። በቅርቡ በ"Netflix" የተሰራ "The Social Dilemma" የሚል ዶክመንተሪ አየሁ። ተራ ዶክመንተሪ አይደለም ጌታዬ! እዚህ ዶክመንተሪ ላይ ቃለ መጠይቅ የሚደረግላቸው ግለሰቦች ከባድ ሚዛን ናቸው። "Instagram" መጀመርያ ላይ ሃሳቡ ሲጠነሰስ አብረው የነበሩ ፣ "Twitter" ውስጥ ለአመታት በኢንጅነርነት ያገለገሉ፣ "pintrest" የመጣ ሰሞን ፕሬዝዳንት ሆኖ የሰራ፣ "Facebook" ውስጥ የ "monetization" ክፍል ዳይሬክተር የነበረ፣ "Google Drive"ን የፈጠሩ፣ "Facebook" ላይ ያለችውን "Like button" የሰራ፣ "Google" ውስጥ በዲዛይነርነት የሰሩ ፣" Gmail" መጀመርያ ሲፈጠር አብረው የነበሩ እና የ "Facebook" ስራ አስፈፃሚ(Executive) ቡድን ውስጥ ሳይቀር የነበሩ ሰዎች ናቸው።

ከነዚህ ከባባድ ሰዎች ውስጥ አንዳንዶቹ በፍቃደኝነት ስራቸውን የለቀቁ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ እነዚህ ማህበራዊ ሚድያዎች የሚሰሩት ትውልድን ሽባ የሚያደርግ ስራ ስለቀፈፋቸው ተጣልተው ወይ ተባረው የወጡ ናቸው።

የሚያስደነግጥ ነገር!

ሁሉም የሚያወሩት አንድ አይነት ነገር ነው። ምን ይላሉ መሰለህ ጌታዬ!

"....የየትኛውም ማህበራዊ ሚድያ የ " Business Model" እንዴት ተጠቃሚዎቻችንን ስክሪን ላይ ማቆየት እንችላለን የሚል ነው! አንድን ተጠቃሚ "Facebook" ወይም "Youtube" ላይ ለማቆየት እና በይበልጥ ትኩረቱን ለመሳብ ምን እናድርግ? የህይወቱን ስንት አመታት ለኛ እንዲሰጠን እናድርግ? የሚለውን ታሳቢ አድርገው ነው የሚሰሩት! እነዚህ "Tech ካምፓኒዎች" ተጠቃሚዎቻቸው "Online" የሚመለከቱትን ማንኛውንም ነገር ያያሉ፣ ይከታተላሉ፣ ይመዝናሉ፣ ያጠናሉ። አንድን ፎቶ ለምን ያህል ደቂቃ ቆም ብለህ እንዳየህ እና የሆነን ቪድዮ እስከ ስንተኛው ደቂቃ ድረስ እንደተከታተልክ ሳይቀር ያውቃሉ! ሲከፋህ ያውቃሉ፣ ሲጨንቅህ ያውቃሉ፣ ስትጓዝ ያውቃሉ፣ ማታ ማታ ምን እንደምታይ ያውቃሉ፣ ቀን ቀን ምን አዘውትረህ እንደምታይ ያውቃሉ። እኛ ከምናስበው በላይ እነዚህ ካምፓኒዎች ጋር ስለኛ ብዙ መረጃ አለ!...."

አባዬ! "Youtube" ልትገዛው ያሰብከውን እቃ መሃል ላይ አስተዋውቆት አስደንግጦህ ያውቃል? የሆነ ልትማር ያሰብለውን ትምህርት በምታየው "Video" መሃል በማስታወቂያ መልክ አምጥቶብህ አልተገረምክም? "Facebook" የዛሬ 10 ዓመት የምታውቀውን እና ከዛ በኃላ አግኝተኸው የማታውቀውን ሰውዬ "people you may know" ላይ ገጭ አድርጎት አይተህ ገርሞህ አታውቅም? "Google" ላይ የሆነ "lipstick" "Search" አድርገሽ ከወጣሽ በኃላ በንጋታው ሌሎች ማህበራዊ ሚድያዎችን ስትከፍቺ የ"lipstick" ማስታወቂያዎች አስሬ እየመጡ አዝገውሽ አያውቁም?

ሰዎቹ እንዲህ ይላሉ!

"...አብዛኛዎቻችን የምንጠቀማቸው የማህበራዊ ሚድያ መተግበርያዎች ነፃ ይመስሉናል! ነገር ግን አይደሉም! ለነዚህ ማህበራዊ ሚድያዎች ማስታወቂያ ድርጅቶች ብዙ ሚልዮን ዶላሮችን ይከፍላሉ! እኛ ልክ እንደ እቃ(product) ነን! እነዚህ ማህበራዊ ሚድያዎች የምንወደውን፣ የምንጠላውን፣ የምናደርገውን እና ያቀድነውን ስለሚያውቁ ለነዚህ ማስታወቂያ ድርጅቶች የኛን መረጃ(data) ይሸጡላቸዋል!...በቀላሉ ካሌንደርህ ላይ በቀጣይ ወር መነፅር እንደምትገዛ ከፃፍክ ቀኑ እየቀረበ ሲመጣ ብዙ የመነፅር ማስታወቂያዎች ይመጡብሃል! ኢሜልክ ላይ የሆነ ሃገር የምትሄድበት ትኬት ካለ እዛ የምትሄድበት ሃገር ላይ ያሉ የሆቴሎች ማስታወቂያ ይመጣብሃል!..."