Get Mystery Box with random crypto!

ከፍተኛ መጠን ያለው የዕርዳታ ምግብ እንደተመዘበረ ማረጋገጡን የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት አስታወቀ፡፡ | Ethio Fm 107.8

ከፍተኛ መጠን ያለው የዕርዳታ ምግብ እንደተመዘበረ ማረጋገጡን የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት አስታወቀ፡፡

የአሜሪካ መንግሥት የዓለም አቀፍ ልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ)፣ ባደረገው የምርመራ ውጤት ከፍተኛ መጠን ያለው የዕርዳታ ምግብ አቅርቦት ምዝበራ መፈጸሙን በማረጋገጡ፣ በኢትዮጵያ የሚያደርገውን ዕርዳታ እንዳቆመ አስታውቋል፡፡

ውሳኔውም አስቸኳይ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሃያ ሚሊዮን ዜጎችን እንደሚጎዳ ነው የተገለጸው፡፡ድርጅቱ እንደገለጸው፣ በፌዴራልና በክልሎች መንግሥታት አማካይነት ወታደራዊ ክፍሎች ከሰብዓዊ ዕርዳታው ተጠቃሚ ነበሩ ብሏል፡፡

ዩኤስኤአይዲ ባደረገው ምርመራ ደርሼበታለሁ እንዳለው ከሆነ፣ ባለሥልጣናት ለተረጂዎች ተብሎ የቀረበን የዕርዳታ ምግብ ወታደራዊ ኃይሎችንና የቀድሞ ተዋጊዎችን ለመመገብ ከመዋላቸው በተጨማሪ፣ ዱቄቱን ወደ ውጭ ለሚልኩ ድርጅት በግልጽ ገበያ ቀርቦ እንዲሸጥ ማድረጋቸውን አረጋግጫለሁ ማለቱን የሪፖርተር ዘገባ ያመለክታል፡፡

ይህን ተከትሎ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ቁልፍ እሴት ከሆኑት ቀዳሚውና ዋናው ከራስ በፊት ለህዝብና ለሃገር ጥቅም መቆም መሆኑን አስምሮበታል፡፡
(USAID) ሰሞኑን አጣርቻለሁ ብሎ ባወጣው መግለጫ ለሰብአዊ እርዳታ የመጣን እህል ከሌሎች መንግስታዊ አካላት ጋር በመሆን፣ መከላከያ ሰራዊታችንም እንደተጠቀመ አድርጎ ያቀረበውን ሪፖርት የተለያዩ ሚዲያዎች ሲዘግቡት ተመልክቻለሁ ብሏል፡፡



ይሁንና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በጥብቅ ድስፕሊን የሚመራ ዘመናዊ ሰራዊት ነው ያለው መግለጫው ፣ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚደረግላቸውን ወገኖቹን ቀለብ ሊቀማ ቀርቶ፤ ከቀለቡ ቀንሶ የሚያካፍል ሰራዊት መሆኑን የሃገሩ ዜጎች ብቻ ሳይሆኑ፣ በአጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ሰላም ማስከበር በተሰማራባቸው ቦታዎች ሁሉ የዕለት ከዕለት ተግባሩ መሆኑን የደረሰላቸው ህዝቦች፤ መንግስታት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሁሉ የሚያውቁት ሰመ ጥር ህዝባዊ ሰራዊት ሲል ገልጧል፡፡


የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት በቂ ሎጄስቲክ ያለው በዓለም አቀፍና በአገር ውስጥ ለተፈናቀሉትና በድርቅ ለተጎዱት፣ በዓይነትና በገንዘብ የሚረዳ እንጂ ተቸግሮ ከአሰራር ውጭ የሚጠቀም አለመሆኑም ሊታወቅ ይገባል ብሏል፡፡



ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 05 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/.../UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos