Get Mystery Box with random crypto!

ከ40 ሺ በላይ ሰዎች የአስተዳደር በደል ተፈጽሞብናል ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ። በ2015 ባለፉት ዘጠኝ | Ethio Fm 107.8

ከ40 ሺ በላይ ሰዎች የአስተዳደር በደል ተፈጽሞብናል ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ።

በ2015 ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ከ 40 ሺ በላይ አቤቱታዎች ቀርበውልኛል ሲል የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ለኢትዮ ኤፍኤም አስታውቋል።

40 ሺ 486 ሰዎች ከስራ፣ ከጡረታ፣ ከይዞታ፣ከካሳ ጥያቄ ከአገልግሎት ማጣት እና በሌሎም ጉዳዮች ላይ የአስተዳደር በደል ተፈፅሞብናል በማለት ነው ቅሬታቸውን ለተቋሙ ያሰሙት።

ተቋሙ በዚህ ዙሪያ ያደረገውን ምርመራ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ያስታወቀ ሲሆን ባለፉት ዘጠኝ ወራት ምርመራ እንዲደረግባቸው ከተመረጡ 1 ሺ 174 አቤቱታዎች ውስጥ 741 አቤቱታዎች እልባት ማግኘታቸው ተነግሯል፡፡

ቀሪ 433 መዝገቦች ምርመራቸው ባለመጠናቀቁ በሂደት ላይ ይገኛሉ ሲል ተቋሙ አስታውቋል::

የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ፤ ተቋሙ የማይመለከተውን አቤቱታ የመመርመር ግዴታ እንደሌለበት እና
በፍርድ ቤት የታዩ የወንጀል ጉዳዮች እንዲሁም በግል ድርጅቶች ላይ የቀረቡ አቤቱታዎች በተቋሙ ስልጣን ስር የማይወድቁ መሆናቸውንም ገልፃል፡፡

ወደ ተቋሙ የሚመጡ አቤቱታዎች ሲኖሩም ደረጃቸውን ጠብቀው መቅረብ ይኖርባቸዋል ያለው ተቋሙ ደረጃቸውን ጠብቀው ካልቀረቡ ምርመራ እንደማያካሄድባቸው አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በዜጎች ላይ የሚደርሱ አሰተዳደራዊ በደሎችን የመመርመርና ውሳኔ ሃሳብ የመስጠት ሃላፊነት ያለበት ተቋም ነው፡፡

በየውልሰው ገዝሙ
ግንቦት 01 ቀን 2015 ዓ.ም