Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ ፍቅር❤️

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofiker4720 — ኢትዮ ፍቅር❤️
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiofiker4720 — ኢትዮ ፍቅር❤️
የሰርጥ አድራሻ: @ethiofiker4720
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.13K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮ ግጥም


😂ህዝቦችዋ ፈገግ ሲሉላት ኢትዮጲያም ትስቃለች
For any cross promotion
.
.
.
.
.HBD lemlet guwadwgnachiwn kefelgu bezi channel gabzuwachew
.
.
. ግጥሞች
.
Contact @djabrelal For Promotion Only

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2021-08-09 23:33:55 https://vm.tiktok.com/ZMdEXDLdA/
2.5K viewsabre lal , 20:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-06 23:13:50 የልቤ ሰራቂ

የውበቷ እንቁ ውቧ ፅጌረዳ
ደምቃ እንደወጣች ገና በማለዳ
አብራት ከወጣችው ከፀሀይዋ ልቃ
ልቤን ወሰደችው ካካሌ ፈልቅቃ
የምን ልቤ ብቻ የምን አካላቴ
በፍቅሯ የነደደው መላ እኔነቴ

የፍቅር ጀግናናት አይደፍሩትን ደፋር
ጥልፉ የጣለችኝ በውበቷ አድባር
ከልቤ ካንጀቴ እኔ እዬወደድኳትሰታ
በፍርሃት ተውጬ ፍቅሬን ስገልፅላት
በፈጣሪ ፀጋ በውበቷ ኮርታ
አሻፈረኝ ብላ ሄደች ጀራባ

የወንድነቴ ጥግ ተሰበረ ወሽመጡ
የማረገው ጠፋኝ አልገባኝም ቅጡ
ኸረ ወቸው ጉዴ አሁን ምን ተሻለኝ?
ከሷ ተነጥዬ መኖር አይቻለኝ
ቀን በቀን ስናፍቅ ልቤ ሲፈልጋት
እንዲው ጥላኝ ስትሄድ ፍቅሬ አልከበዳት
በፍቅሯ ብመንን ካአጀብ ተነጥዬ
መቼም አልጫናት የኔ ሁኚ ብዬ
ውደደኝ ሳትለው ልቤ ከወደዳት
እንዴትስ አድርጌ ሸንጎ ልገትራት
ቀንቶኝም የማያወቀው ደርሶ የኔ ዕጣ
እሷን አገኝ ብዬ እኔው ራሴን ልጣ?

@ethiofiker4720
@ethiofiker4720
@ethiofiker4720
2.5K viewsabre lal , 20:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-01 23:44:48 ፍቅር እና ጉንፋን
● ● ● ● ● ●


ከለታት አንድ ቀን ባንክ ቤት አየኋት
በጄ የያዝኩትን ብርቱካን ሰጠኋት
ሙሉ ማንነቴን ልቤን አስረከብኳት

••●••
ና ካለች ሔዳለሁ ካለችበት ቦታ
ሰዓት አይገድበኝ ቀንም ሆነ ማታ

••●••
ሰኞለት ፒያሳ እሮብ መካኒሳ
ሀሙስ ደግሞ ቦሌ አርብ ቀን ጉለሌ
እሁድና ቅዳሜ ከሷ ጋር ባብነት
አብረን እንውላለን በፍቅር ባንድነት
ሚስቴ ስላት ባሌ
ትለኛለች ሁሌ
አሁን ሁሉም ቀረ... ታሪክ ተቀየረ.....

••●••
የኔ ውድ ፍቅሬ ብላ እንዳልጠራችኝ
ዛሬ ሁሉም ቀርቶ ለአይኗ ጠላችኝ
ተመስገን ማለት ኑሮ አስተምሮኛል
ትናንት ፍቅር ይዞኝ ዛሬ ተሽሎኛል
የዘንድሮ ፍቅር ጉንፋን ሆኖብኛል
2.3K viewsabre lal , 20:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-01 23:35:08 አንቺን ያጠሁ ለታ

አንድ እውነት ልንገርሽ ስሚኝማ ውዴ
አንቺን ያጣሁ 'ለታ ከበፊት መውደዴ
ሲቃዬም አይሎ
እስትንፋሴ ግሎ
ጭንቀቴ ይጨምራል
የናፍቆቴ ልኬት ከመጠኑ ያልፋል

አዎ ውዴ አንቺን ያጣሁሽ 'ለታ .......

ደግሞ ስትናፍቂኝ ሀገር ይጠበኛል
ከአንደበቴ ቃላት ማውጣት ይጨንቀኛል
የማወራው ሁሉ ግራ ይገባኛል
በቀን በጠራራ ለኔ ይጨልማል
ማታም በጨረቃ
ድንገት እያነቃ
ተነስ ተነስ ተነስ ብረርና
ካለችበት ደርሰህ እቅፍ አርጋትና
ናፍቆትህ ይውጣለህ
ሳማት እንደልብህ
ይለኛል መንፈሴ
እስክትወጣ ነብሴ
አዎ የኔ መውደድ አንቺን ያጣው ለታ
ድምፅሽ የራቀለት ከሰማይ ከፍታ
የቆጡን የባጡን መልሼ መልሼ
በሀሳቤ ቅኝት ሁሉን አዳርሼ
ደግሞ ምንአገኛት ምን ሆናነው ፍቅሬ
በናፍቆት ልትቀጣኝ የጠፋችው ዛሬ
ብዬ አስባለው አገኝሽ ይመሥል
ከምናቤ ጓዳ ካንቺጋ ስዋልል።
ያለፈን ትዝታ እያነሳው ስጥል
በሳቆችሽ ድምፀት ደግሞ ፈገግ ስል
ከተጓዝኩት ዓለም ከምናብ ስነቃ
ትውስ ይለኝና የናፍቆቴ ሲቃ
ስብር ስብርብር እያለ መንፈሴ ሲከዳ
ቃልሽ ሲሆን ብርታት የእምነቴ እዳ
በዝምታ ልሳን በመጥፋት አለንጋ
ሲገርፈኝ ያደረው ናፍቆትሽ ለሊቱ እስኪነጋ
ለቀን ይጥለኛል እንቅልፌን ሳልተኛ
ለፀሐዩ ግለት አድርጎ ተረኛ
ዳግም ሊያዋትተኝ ባይን እያስማተረ
ድምፅሽን በንፋስ ጭኖ እያመጣ ጆሮ እየቀሰረ
ስሞችም ሲጠሩ ለኔ እያስመሠለ
ሲያሰዞረኝ ይውላል ቀና እያስባለ

እናም የኔ ናፍቆት :- ......

እውነታው ይሄ ነው አንቺን ያጠሁ ለታ
ናፍቆትሽ ሲበዛ ሳቄም ተደብቆ ያልፋል በዝምታ
2.2K viewsabre lal , 20:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-21 21:07:20 አባቴን ያያችሁ?



አንተ የአባይ ውሃ የበረሀው ንጉስ
አባቴን ላክልኝ አደራህን መልስ
ለማን አቤት ልበል ምን ብየ ልጣራ
የአባይ አዋይ ቆሌ በላብኝ አደራ
ምስክርም አጣሁ አየሁ የሚል ጠፋ
ያባቴ ደም ቀረ ሜዳ እንደተደፋ
አንች አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ
አደራ በልተሻል ተቀብለሽ ከአባይ
አደራሽን መልሽ ለጠየቀሽ አሳይ
አይቶሻል ፈጣሪ በጠራራ ፀሀይ
አንችን ካስደሰተሽ ያለአባት መኖሬ
አንችን ካስከበረሽ አባት ያጣው ክብሬ
አንችን ካስወደደሽ አባት ያጣው ፍቅሬ
መጓዣ ከሆነሽ መሄጃ አልባው እግሬ
እኔ አልተመቸኝም ይመችሽ ሀገሬ
ተራሮች አልቅሱ ዛፎች ተናገሩ
ፀሐይ ያየችውን እናንተም መስክሩ
የት ነበር አባቴ ስትነጋገሩ
ሀዘኔን ባይቀንስ ምንም ባልሰጣችሁ
አባት ገዳዮችን አጥፉልኝ ባካችሁ
ልሂድ ልንከራተት ሲጓዝ ይኑር እግሬ
ትርጉም አጥቷልና የልጅነት ፍቅሬ
ያለአባት መኖሩ ከአባት ተፈጥሬ
እናቴ በስደት አባቴ መቃብር
ሁለት ህጻን ይዤ በምን አቅሜ ለኑር
ተውኝ አልማርም መማር ይቅር ወዲያ
በጠራራ ጸሀይ ለሚአስገድል ሙያ
ተመለሽ እናቴ ይቅርብሽ ትምህርቱ
በሰው ሀገር ሆነሽ አትልፊ በከንቱ
ጥሩ ሙያ መማር ይሄው ነው ውጤቱ
ልብ በይ እናቴ ነይ ሀገርሽ ግቢ
ብዙ ልማር ብለሽ እሩቅ አታስቢ
ውለታ እንዳልዋሉ ብዙ እንዳልደከሙ
አደራ እያወጡ ብዙ እንዳልጠቀሙ
በጠራራ ጸሐይ መንገድ እያስቆሙ
ዶክተር ኢንጅነሩን እየለቃቀሙ
ተዋቸው እያለ እያለቀሰ አባይ
ገድለው ጨረሷቸው በጠራራ ፀሐይ
ይሄነው እንግዲህ የመማር ትርጉሙ
ሳይታፈስ ቀረ የስመኘው ደሙ
የለም እማራለሁ እማየም ተማሪ
እኔም ስመኘው ነኝ አንቺም ታሪክ ሥሪ
ጀግና ሞተ አትበሉ እንኳን ታሪክ ሰርቶ
እንኳን ዘር ተክቶ
ገዳይ ነው የሞተው ድርብርብ ሞት ሞቶ
አባቴ አልሞተም ለወገኑ ዘምቷል
ግድቡን ካልፈጸምን በእርግጥ ያኔ ሞቷል።

@ethiofiker4720
2.1K viewsabre lal , 18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ