Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያዊነት የኪነ-ጥበብ ሥራዎች በትረ ጊዮን ካስት ኤጀንት

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioenku — ኢትዮጵያዊነት የኪነ-ጥበብ ሥራዎች በትረ ጊዮን ካስት ኤጀንት
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioenku — ኢትዮጵያዊነት የኪነ-ጥበብ ሥራዎች በትረ ጊዮን ካስት ኤጀንት
የሰርጥ አድራሻ: @ethioenku
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 584
የሰርጥ መግለጫ

#ማንኛውንም አይነት #የቪዲዮ ሥራ በጥራትና በፍጥነት እንሰራለን::
#We do all kinds of #Video work efficiently and quickly
#በታማኝነት ልናገለግሎት ዝግጁ ነን
#We are ready to serve you faithfully
#ይደውሉ:-09-42-55-6130 / 09-24-54-83-65
#በውስጥ ማናገር ከፈለጉ
#If you want to talk inside
@Babilove12

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-02 21:05:42 #ደራሲ_Hila
#ምትኬ
ክፍል25
'ቤቲ ምን እያሰበች ይሆን? ግሩምስ ምን አስቦ ነው ለሁለቱም አንድ ሩም እሚይዘው? መቼም አብሯት ሊጋደም አይደለማ ደሞ እንዴት ምንም አይልም? ወይስ አስገብቶን ሊሄድ ነው?' ይሄን እያሰብኩ የኔና የብሩክ የሩም በር ላይ ደረስን::
'ብሩኬ ይሄ የአንተና የሙሽሪት ክፍል ነው በሆቴሉ የተገኘው ሁለት ክፍል ብቻ ስለሆነ ያለው አማራጭ ጥንድ ጥንድ ሆኖ ማደር ነው ወይ ደግሞ ቤቲ ከደበራት እኔ ሌላ ሆቴል ፈልጋለሁ መቼም ብሩኬ አከራዬ እንደማይከፍቱልኝ ታቃለህ በዚህ ሰአት" እኔም ቤቲም ተያየን አብረው ቢያድሩ ምን እንደሚፈጠር አናቅም ደግሞ በዚህ ሰአት ሂድ አይባልም የት ይሄዳል ቤቲ ምን እያሰበች እንደሆነ አላቅም እኔ ግን አንድ ሀሳብ መጣልኝ ቤቲ እና እኔ አብረን እንደር እነሱም አብረው ይደሩ የሚል ግን ደግሞ ለብሩኬ እንዴት ልንገረው
"ይቅርታ ብሩኬ አንዴ ቤቲዬን ብቻዋን ላውራት" አልኩት
"እሺ ውስጥ ግቡና አውሩ ችግር የለውም" ብሎኝ ተያይዘን ወደ ውስጥ ገባን በሩን ከዘጋሁት በኋላ
"ቤቲዬ ምን እያሰብሽ ነው?"
"እኔጃ አላቀውም ሩም ከገባ በኋላ እንዳይለወጥ ፈራሁ ግን ደግሞ አማራጭ የለንም ብሌንዬ መቼም አይደፍረኝ እምቢ ካልኩት የብሩክ ጓደኛ ስለሆነ ሊያፍር ይችላል"
"እና አብረሽው ልታድሪ ወሰንሽ?"
"አማራጭ የለማ "
"አማራጭ አለን አንድ ያሰብኩት ነገር አለ ብሩኬ ካልከፋው"
"ምን አሰብሽ?"
"እኔ እና አንቺ አብረን እንደር እነሱ ደግሞ አብረው"
"ያምሻል ብሌን ይሄ አይሆንም ለኔ ብለሽ ብሩኬን ታስቀይሚዋለሽ ባልሽ ሊሆን የተዘጋጀን ሰው ጓደኛው ፊት እንዲ እንዳትይው ሆሆሆሆሆ በይ ነይ ውጪ ጉደኛ"
"አንድ ነገር ቢያረግሽ እኔ ምን አፍ አለኝ ቤቲዬ"
"ምንም አያረገኝም ደግሞ አይዞሽ የኔ እህት እኔ እንዳቺ ድንግል አይደለሁም ታቂ የለ ልቤንም ድንግሌኔም መሌ እንደወሰደው አታስቢ"
"አትቀልጂ ቤቲ ስሚኝ....."
"ኡፍፍፍፍፍ አታበሳጪኝ ጠዋት ስራ ገቢ ነን ተነሽ እንውጣ በቃ"
ብላኝ በሩን ከፍታ ወጣችና "ብሩክ ግባ በቃ እኔና ግሩም አንድ ሩም ለአንድ ምሽት እንጋራለን መልካም አዳር"
"እርግጠኛ ነሽ ?" አላት ግሩም ገርሞት
"አዎ " አለች ያለማመን ቅላፄ እያወጣች ብሩኬ ወደ እኔ ገባ እነሱም ተያይዘው ወደ ሩም ሄዱ፡፡
"እናቴ በጣም ነበር እኮ የናፈቅሺኝ " ወደ ደረቱ ስቦ አቀፈኝ አስተቃቀፉ ጉልበት ነበረው የሆነ ምትሀት ነገር ነበረው ልቡ በፍጥነት ስትመታ ወድያ እምትገፈትረኝ መስሎኝ ነበር የኔ ሰውነት መንቀጥቀጥ አይሉት አቅም ማጣት ብቻ አንዳች ነገር ሆኖብኛል ከአንገቴ ቀና ሲያረገኝ ከንፈሬ ተንቀጠቀጠ ቀስ ብሎ መሳም ሲጀምር እኔም አፀፋውን መለስኩ ሳናስበው ጥልቅ ስሜት ውስጥ ገባን ተያይዘን አልጋው ላይ ወደቅን የብሩኬ እጆች መላ አካላቴን በአንዴ መዳሰስ ይችል ይመስል ገላዬ ላይ ያርመሰምሰው ጀመር ከላይ የለበስነውን ተጋግዘን አወለቅነው አንገቴን ጆሬዬን ጡቶቼን እንብርቴን መሳም ጀመረ በጥልቅ ስሜት ውስጥ ሆነን ሁሉን እረሳን
* * *
"ቤቲ ፈራሽ እንዴ" አላት ግሩም
"አይ አልፈራሁም ሁሉም ሰው የራሱ ጌታ ነው "
"ማለት አልገባኝም"
"ማለትማ እራስህን የምትገዛው እራስህ ነህ ስሜትህን የምትቆጣጠረውም እንዲቆጣጠርህ ምትፈቅድለትም አንተው ነህ ስለዚህ ከፈራሁ ለፈራሁት ነገር እድል እየሰጠሁት ነው ማለት ነው ስለዚህ አልፈራም"
"እሺ ብደፍርሽስ"
"ትችላለህ እሚገርምህ መጥፎ ነገሮች እንደሰዉ ማንነት ነው ተፅእኖ እሚኖራቸው ብደፍረኝ ለሰው የነበረኝ የመጨረሻ ጠብታ እምነት ይደርቃልሰው ማመን አቆማለሁ ከዛ ውጪ እራሴን አልጠላውም አንተን ነው ምጠላህ እኔ ንፁህ ነኝ አልቆሸሽኩም አንተ ግን በሰራከው ስራ ስታፍር ትኖራለህ ባየኸኝ ቁጥር ትሸማቀቃለህ"
"የምርሽን ነው እሺ ግን ከኔጋር ለምን ተስማምተሽ ገባሽ"
"የገባሁት አንሶላ ልጋፈፍህ አይደለም ሰአቱ መሽቷል ሰው ነኝ ህሊና ያለኝ በዚህ ሰአት ወጥተህ የሆነ ነገር ብትሆን ፀፀት ይይዘኛል እራስ ወዳድ አይደለሁም"
"እሺ በቃ እንተኛ እኔ ሶፋ ላይ ተኛለሁ አንቺ አልጋው ላይ ተኚ "
"ሶፋው አይመችም ና እዚው ጋር ተኛ ችግር የለውም"
"ካልሽ እሺ ለነገሩ ሶፋው አጭር ነው"
ግሩም እና ቤቲ እንቅልፍ እስኪወስዳቸው ብዙ ነገር አወሩ ቀድማው ቤቲ ተኛች እያያት ድፍረቷ እና አመለካከቷ ገረመው ቆንጆ ነች በዛላይ ብሎ እያሰበ ተከትሏት ተኛ::
* * *
ብሩኬ ጠዋት ስነቃ እንዴት ቀና ብዬ ልየው እሱም አንገቱን ደፋ በዝምታ ሻወር ወስጄ ቤቲ ስራ እንግባ ብላ ስለደወለች ተያይዘን ወደ ታች ወረድን ቤቲ ና ግሩም እየተሳሳቁ ቁርስ አዘው ጠበቁን እኔና ብሩኬ ግን ፊታችንን የሀፍረት ደፍተን በዝምታ ተቀላቀልን የሆነውን መጠየቅ አላስፈለጋቸውም ለመቀለድ ቢሞክሩ ቢያወሩ መልስ አልነበረንም ብቻ ከዛ ቦታ እስክነሳ ጨነቀኝ አየር አጠረኝ ቁርሱ ሲደርስ የመብላት ፍላጎት አልነበረኝም ነካክቼ ተውኩት ብሩኬም እንደዛው ቤቲን በአይኔ እንነሳ ስለት "በቃ ስራ እየረፈደ ነው እናንተ ብሉ እኛ እንሂድ ብላ ብድግ ስትል ተከትያት ልነሳ ስል የተቀዳው የብርጭቆ ውሀ እላዬ ላይ ተገለበጠ ብሩኬ ደንግጦ "እኔን የኔ እናት ተረፍሽ" አለኝ
"ደና ነኝ ይደርቃል " ብዬ እየቸኮልኩ ወጣሁ ቤቲ ከሩጫ ባልተናነሰ አጠገቤ ደርሳ "ቆይ ምን ተፈጠረ ምንሆናቹ ነው የተኮራረፋችሁት"
"አልተኮራረፍን አተፋፍረን ነው አሁን ከዚህ እንሂድ ነግራሸለሁ"
"እሺ" ታክሲ አስቁመን ወደ ስራ ልብሴ የተወሰነ እየደረቀ ነበር
በይ ቀጥይ ልስማሽ" አለች ቤት ታክሲ ውስጥ ሆነን
"ቤቲዬ ጉድ ሆንኩልሽ እኮ ደግሞ ብሩኬን ማስደበሬ ነው ያሳፈረኝ"
"ምንድነው ንገሪኝ እስኪ"
" ማታ በሞቅታ እኔ እና ብሩክ የማይሆን ስሜት ላይ ደርሰን ነበር"
"እሺ ከዝያስ መቼም ሰጠሁት አትይኝም"
"ቆይ ከመጀመሪያ ልንገርሽ በቃ ተያይዘን በስሜት ፈረስ መጋለብ ስንጀምር ቤቲዬ ምን ልበልሽ በቃ አንዳች የማላውቀው ነገር ውስጤ ተቀጣጠለ ለሆነ ያህል አይምሮዬ ማሰብ አቆመ ብቻ እርቃናችንን በውስጥ ሱሪ ብቻ ስንቀር ድንገት እማዬ ፊት ለፊቴ ቆማ በትዝብት ስታየኝ አየኋት ከዛ ብሩኬ ላይ ጮኩ እማዬ ቃሏን አፈረስኩ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ ያሁሉ የጋለ ስሜት በሰከንድ ቀዘቀዘ ከዛ በቃ አፈርኩት እርቃኔን እርቃኑ ነበርን ለዛ ነው የተፋፈርነው"
"አልነካሽማ ግን መቼም አልዋሸሽኝም?"
"እመኚኝ ቤቲዬ ግን ስሜቱን ወድጄው ነበር ተሳስቼም ነበር... ቤቲዬ?"
"ወዬ"
"ግን ሲወሰድ እንዴት ነው ሚያደርገው?" አልኳት እየተሽኮረመምኩ
"ሆሆሆሆ በይ ስራ ቦታ ደርሰናል እንግባ ከዚህ በኋላ ከሰርጋቹ በፊት አብሮ ማደር የለም የተቀመሰ ነገር ካልተደገመ ማለታቹ ስለማይቀር ተናግሬያለሁ"
"እህህህህ የጠየኩሽን ንገሪኛ "
"በኋላ እናወራለን እሺ"

ክፍል-26 ይቀጥላል.....ከተመቻችሁ

#አስተያየት ካላችሁ...

@Babilove12

#joine #share

https://t.me/Ethioenku
58 views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 07:44:02 #ደራሲ_Hila

#ምትኬ

ክፍል24

አስጠንቅቃን ወጣች ተያይዘን ሹሉክ ብለን ወጣን ብሩኬን ደውለን ያለንበትን ነገርኩት፡፡ መጥቶ ካለንበት ወሰደን አብረውት ሁለት ጓደኞቹ አሉ አንዱ ጠየም ያለ ሲሆን ፂሙ እጅግ በጣም ያምራል ቁመቱና ተክለ ሰውነቱ ወንዳወንድ መሆኑን ይመሰክራል ሁለተኛው ፊቱ ላይ አንዳችም የፀጉር ዘር በቅሎበት እንደማያቅ ያስታውቃል ሳቂታና ፊቱን ሀዘን የጎበኘው አይመስልም በቃ ፈገግ ፈገግታ መልክ ቢኖረው እሱን ነበር የሚመስለው ብዬ አሰብኩ፡፡ ብሩኬ ከነሱጋር አስተዋወቀን ሳቂታው ዳዊት ሲሆን ወንዳወንዱ ደግሞ ግሩም ይባላሉ እኔ ጋቢና ቤቲዬ ከኋላ ተቀምጠን ጉዞ ጀመርን፡፡
"ባሌ ማለቴ የወደፊት ባሌ ወዴት ነን?"
"እሺ የኔ ሚስት ለኔ ግን የወደፊት አልልሽም እንዳገባሁሽ ነው የማምነው"
"ኧረ ቀስ ወዴት ወዴት መች ቤትህ ገባሁ አሁንም እናቴ ቤት ነኝ አቶ ብሩክ ብዙ አያቅራሩ መሰረዝም እችላለሁ መቼም"
"እኔ መች ካንቺ ጋር አወራለሁ ማዘርን ጠይቄ ተፈቅዶልኛል ስለዚህ ወይዘሪት ብሌን የርሶ ፍቃድ አያሻኝም" በንግግራችን ሁላችንም እየሳቅን ነበር በተለይ ሳቂታው ዳዊት ከማንም በላይ እየተንፈራፈረ ሲስቅ ሳቄ አገረሸ እንዲው እያወራን እየተሳሳቅን ከአንድ ሆቴል ደርሰን ወደ መኪና ማቆሚያው ገባን ሁላችንም በደስታ ወርደን ወደ ባሩ መግባት ስንጀምር በመሀል ግሩም ረጋ ባለ ድምፅ "ብሩክ እሚበላ ቀማምሰን እንግባ አይሻልም እኔ ርቦኛል" አለን ባይርበንም መብላቱ ስለማይከፋ ወደ ሬስቶራንቱ ገባን ለአምስታችንም እሚበቃ ነገር አዘን ማውራት ስንጀምር ብሩኬ
"እናቴ ግሩም አንደኛ ሚዜዬ ነው ዳዊት ደግሞ ሁለተኛ ከመሀካከላች አልተገኘም እንጂ ሶስተኛው ሚዜዬ መርድ ይባላል መቼም የኔ ቆንጆ ቤቲ አንደኛ ሚዜሽ ነች ሁለቱን ግን እስካሁን ምንም አላልሽኝም ምን አሰብሽ"
"እኔጃ ፍቅር ቤቲ ከቢሮ ሁለት ጓደኞቻችንን እንዳናግራቸው ነግራኛለች ነገ ስራ ስገባ አዋርቻቸሁ አሳውቅሀለሁ"
"ብሌንዬ በኔ ይሁንብሽ ሂዊም ፌሩዝም ደስተኛ ነው ሚሆኑት እመኝኝ" አለችኝ ቤቲ ፈገግታ ከአይኗ ሳይጠፋ ቀበል ብሎ ዴቭ "ካልሆነ ሚዜ እንከራያለና " ብሎ በሳቅ ፍርስ አለ ተከትለነው ሳቅን፡፡
ቤቲ አይኗን ማን ላይ እንደጣለች ለማወቅ ብጥርም አቃተኝ ከሁለቱም ጋር ከልቧ ታወራለች ለሁለቱም ትሽኮረመማለች ያዘዝነውን በልተን እያወራን ወደ ባሩ ገባን መጠጥ ቮድካ ቦትል ወረደ እኔ ብዙም ስለማይመቸኝ ለኔ ነጭ ወይን ታዘዘልኝ ቤቲዬም ወይኑ እንደሚሻላት ተናግራ አብረን መጠጣት ጀመርን ሳቅ ጨዋታው ደራ ምሽቱ እየገፋ መጣ ሞቅታው ዘፈኑ ሳቁ በቃ ሁሉ ነገር ተደበላለቀ ብቻ ደስታ በደስታ ሆነ ብሩኬ እና እኔ ተያይዘን መውረግረግ ሆነ ስራችን ምሽቱ ሳይታወቅ እጅግ እየገፋ መጣ ነገ ስራ መግባታችንን ሁለታችንም እስክንረሳ ድረስ ሞቅታ ውስጥ ገባን ወንዶቹም በጣም ሞቅ ስላላቸው መኪና መንዳት እንደማይችሉ ነገሩን እንደምንም ብዬ በታክሲ ወደ ቤት መግባት ባስብም ሰአቴን ሳየው መሽቷል ወደ 8ሰአት እየተጠጋ ነው ያለን አማራጭ ሩም መያዝ ነበር ዴቭ ወደ ቤቱ መሄድ እንደሚችል ተናግሮ ታክሲ ጠርቶ ሄደ ለአራታችን ሩም ለመያዝ ግሩም ሄዶ ሁለት ቁልፍ ብቻ ይዞ ተመለሰ እኔም ቤቲም በግርምት ተያየን የኔና የብሩኬ አብሮ ማደር የተለመደ ቢሆንም ቤቲን የት ሊያሳድር ነው ወይም እሱ የት ሊያድር ግራ እንደተጋባሁ ቤቲም ጥያቄ እንደተፈጠረባት ተያይዘን ወደ ተያዙት ሩሞች አመራን፡፡
ዛሬ የኔም ልብ ምት ጨምሯል ከመጠጡ እና ከቤቱ ሙቀት ጋር ተደመሮ መላ ሰውነቴ እንደሳት ይፋጃል የብሩኬም ሰውነት ከኔ የባሰ እሳት ሆኗል ልባችን ቢፈራራም ተለያይተን ማደርን ግን አንመርጥም፡፡ 'ቤቲ ምን እያሰበች ይሆን? ግሩምስ ምን አስቦ ነው ለሁለቱም አንድ ሩም እሚይዘው? መቼም አብሯት ሊጋደም አይደለማ ደሞ እንዴት ምንም አይልም? ወይስ አስገብቶን ሊሄድ ነው?' ይሄን እያሰብኩ የኔና የብሩክ የሩም በር ላይ ደረስን::

ክፍል-25 ይቀጥላል.....ከተመቻችሁ

#አስተያየት ካላችሁ...

@Babilove12

#joine #share

https://t.me/Ethioenku
71 views04:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 09:31:27 #ምትኬ

#ደራሲ_HiLA

ክፍል23

ከብሩኬ ጋር የተቀጣጠርንበት ሰአት ሲደርስ ከቤቲ ጋር ወጣን እሷም ወደቤቷ እኔም ወደ ፍቅሬ ሄድን
ብሩኬ ስለሁሉም ነገር አስቦ አስተካክሎ ስለ ሰርጉ አስቦ ጨርሷል ለሳምንቱ የሽማግሌ ድግስ አስፈላጊውን ሁሉ ነገር አሟልቶልኛል ብሩኬ ባሌ ሂወቴ አለሜ ሊሆን ቀናት ብቻ ነው የቀረን ልቤ በጣም ፈርቷል
* * *
ዛሬ ሽማግሌዎች የተቀጠሩበት ቀን ነው መልሱን ሁላችንም ብናቀውም እኔ ግን በጣም ፈርቻለሁ እናቴ ባትከለክለውም ግን መልሱን እስካቀው ከናቴ አፍ እስክሰማው ልቤ በአፌ ልትወጣ ነው የሚመጡበት ሰአት ሲደርስ ወደ መኝታ ክፍሌ ገባሁ ቤቲም አብራኝ ቁጭ ብላለች ቤቱ ውስጥ መለስተኛ ቀለበት ያለ ይመስላል ሽማግሌዎቹ ከገቡ በኋላ እናቴ እና የንስሐ አባታችን መልሱን ሰጧቸው ቤቲ በሩ ላይ ተለጥፋ ያለውን ነገር በተመስጦ ስትሰማ ተነስቼ ከጎኗ ሽጉጥ አልኩ
" እንኳን ደና መጣቹህ የፈጣሪ ፍቃድ ሆኖ በተቀጣጠርንበት ቀን ሁላችንም ተገኝተናል አምላክ የተመሰገነ ይሁን ከቁጥር አላጎደለንም፡፡ እንግዲ ምንድነው የጠየቃችሁን ውድ የሆነችውን በምንም የማንቀይራትን ለእናቷ አንድና መተኪያ የሌላትን ልጃችንን ነው መቼም ከጉያዋ ባትወጣ ከአይኗ ባትርቅ የእናትየው ደስታ ነው ልጆች ለቤተሰቦቻቸው ውድ ንብረቶች ናቸው እናም ሁሌም ደግሞ ልጆች ናቸው፡፡ አሁን የፍቅርተማርያም እናት እምትለው ነገር ካለ ትበላችሁና መልሳችንን እንነግራችኆለን" ብለው ለእናቴ እድሉን ሰጧት እንደው የኔ ልብ ለምን እንደሆነ ባላቅም መዝለል ጀምሯል "አይሆንም ልጄን ከጉያዬ አልነጥልም ልጄ የባሌ አደራ ናት ያይን ማረፊያዬ ምትኬ መመኪያዬ ሂወቴ ናት እሷን አሳልፌ ለማንም አልሰጥም እንድታገባ አልፈልግም" ብላ ልቤን እንዳትሰብረው ፈራለሁ የኔንም የብሩኬንም ልብ እንዳታደማው በጣም ሰጋሁ እናቴ ግን "እንደው አባ ሁሉን ብለውታል ምን እምለው አለኝ ብለው ነው፡፡ እንደው ልጄን አደራ እንዳታስከፋብኝ" ብቻ አለች አባ ቀጠል ብለው "በሉ እንግዲ ፈጣሪ የተባረከ ያድርገው ፈቅደናል ትዳሩን ፈቅደናል ልጃችንን ሰጥተናል" ከዛም ሽማግሌዎቹ ቁጭ አሉ እኔም ደስ አለኝ ለብሩኬ ደውዬ ነገርኩት በቃ ቤታችን ፌሽታ በፌሽታ ሆነ ምግብ መብላት መጠጣት መደሰት ተጀመረ የሰርጉን ቀን መነጋገር ጀመሩ ብሩኬ ደውሎ ማታ እንድናከብረው ጠየቀኝ ከቤቲ ጋር እንደምንመጣ ነገርነው፡፡
ቤታችን በጎረቤት ተሞላ በቃ ደስታ በደስታ ሆነ፡፡
ከቤቲዬ ጋር ማውራት ጀመርን፡፡ "ቤቲዬ እኔኮ ካንቺ ውጪ ሚዜ የለኝም እንዴት ነው ምናረገው ?"
"ውይ ብሌንዬ መስሪያ ቤት ሂወትም አለች ፌሩዝም ብትሆን ሚዜ ትሆንሻለች ሚዜ አያሳስብም ዋናው ስር ሚዜሽ እኔ ልሁንልሽ የልብ ጓደኛ ነው አንደኛ ሚዜ መሆን ያለበት ስለዚ አታስቢ የኔ ውድ"
"እሺ የሂወት ይሆን ፌሩዝ እኮ ሙስሊም ነች ብሌንዬ"
"እና ትሁና ፎጣ አታወልቅም ከኛጋር አንዳይነት ትለብሳለች አትገላለጥም ብቻ አንቺ ፈልጊ"
"እሺ በቃ ከብሩኬ ጋር ተነጋግረን ቀለበት እና ልብስ እንመርጣለን አሁን እየጓጓሁ ነው እውነት "
"ሳትዋሺ ብሌንዬ የጓጓሽው ለሰርጉ ነው ለብር አምባሩ እስቲ ንገሪኝ" ተሽኮረመምኩ ያላሰብኩ ጥያቄ ነበር ግን ድንገት አንዳች ነገር ጭንቅላቴ ውስጥ ሲፈነዳ ታወቀኝ ቤቲን በቁጣ አይን ገርመም አድርጊያት ወሬ ለመቀየር ሞከርኩ
"ቤቲዬ ሰርጉ እንዴት የሚሆን ይመስልሻል?"
" እንግዲ የሽማግሌ ድግስሽን ያየ ሰርግሽን መገመት አያዳግተውም እድለኛ ነሽ በሁሉም ነገር ብሌን ፈጣሪሽን አመስግኝ መልካም እናት ልጅ አሁን ደግሞ ባል ሊኖርሽ ነው ሁሉን አሟልቶ ነው ያደለሽ የኔ ቆንጆ"
"ቤቲዬ ምነው እራስሽን አራቅሽብኝ አንቺስ እህቴን አድሎኝ የለ፡፡ በይ ተነሽ እንዘጋጅ ብሩኬ ይጠብቀናል"
"እሺ በቃ ልብስ እንምረጥ የኛ ሙሽራ"
ተሳስቀን እየተቀላለድን መዘጋጀት ጀመርን ቤት ሽርጉዱ ጭፈራው ሁሉ ደርቷል የእናቴ ደስታ ከአቅሟ በላይ ሆኖ ከፊቷ ይነበባል እንደው ንጉስ የምትሾም አንዲት ሀገር መስላለች፡፡ የእናቴ ደስታ አስደሰተኝ እጅግ ሲበዛ ካሰብኩት በላይ ለኔ ደስተኛ ናት እውነትም እድለኛ ነኝ በሁሉ የባረከኝ በሁሉ የጎበኘኝ ፈጣሪ ይመስገን ደስታዬን የዘላለም ያርግልኝ
ከቤቲዬ ጋር ለባብሰን ብሩኬን ለማግኘት ልንወጣ ስንል እማን ጠርቼ ነገርኳት እሺ ብላኝ ግንባሬን ስማኝ እራሳችንን እንድንጠብቅ አስጠንቅቃን ወጣች ተያይዘን ሹሉክ ብለን ወጣን ብሩኬን ደውለን ያለንበትን ነገርኩት

ክፍል-24 ይቀጥላል.....ከተመቻችሁ

#አስተያየት ካላችሁ...

@Babilove12

#joine #share

https://t.me/Ethioenku
85 views06:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 19:40:28 #ምትኬ

#ደራሲ_HiLA

ክፍል22

ከብሩኬ ጋር ተነጋግረን በዚህ ሳምንት መጨረሻ ሽማግሌ ሊልክ ተስማምተናል፡፡ ለእማዬም ነግሪያታለሁ በጣም ደስተኛ ናት፡፡ የብሩክ እናትም ቀኑ አልደርስ ብሏቸዋል፡፡ የተዘጋጁት ሽማግሌዎች በጣም የተከበሩና ታዋቂ ባለሀብት ናቸው፡፡ እማዬም ንሰሀ አባቷን ጨምሮ በሰፈሩ የተከበሩ ኽማግሌዎችን ጎረቤቶቿን አብረዋት እንዲሆኑ ነግራቸዋለች አሁን ትልቅ ሰው ፣ ሙሉ ሴት መሆኔ አመንኩ ከእናቴ ተለይቼ ሌላ እማስብለት ሰው መፈጠሩ የራሴን ቤት ሶስት ጉልቻ መመስረቴን ማመን አቃተኝ ይገርማል ያንን የምጠላውን ብሩክን በልቤ አፍቅሬ አብሬው አንድ አመትን አስቆጠርኩ አሁን ደግሞ ባሌ ላረገው አካሌ አካሉ ሊሆን ጠዋት ከጎኑ ልነቃ ማታ አብሬው ልተኛ በቃ የብቻዬ መከታዬ ሊሆን ተቃርቧል ፈጣሪ ያሳካው አምላክ ደስተኛ ትዳር ይስጠኝ ምኞቴ ይህ ነው፡፡
* * *
ሽማግሌዎቹ ዛሬ ነው ሚመጡት እማዬ እንደወጉ ተዘጋጅታ ጠበቀች በተላኩበት ሰአት ቤታችን ደረሱ የግድ መደበቅ ስለነበረብኝ ቤትዬ እና እኔ ሴናዬን ይዘን መኝታ ቤት ተቀመጥን
"ሰላም ለዚህ ቤት" አለ ከውጪ የትልቅ ሰው ድምፅ
""ሰላም ለሁላችን ግቡ" አለች እማዬ
ሽማግሌዎቹ ተከታትለው ገቡ አንደኛው ሽማግሌ አለባበሱ ሙሉ ብሉብላክ ሱፍ ሆኖ ሞላ ደንደን ያለ ሰውነት መካከለኛ ቁመት አለው መነፅር ይጠቀማል ድምፁ አንዳች ነገር እንዳነቀው ነገር ያስጨንቃል ሁለተኛውና ከመሀል የቆመው አጠር ብሎ በወጣትነቱ የተስተካከለ ቁመና እንደነበረው የሚመሰክር የስፖርተኛ አቋም የሚመስል ሰውነት አለው ሙሉ ጥቁር ሱፍ ከነጭ ሸሚዝ ጋር ለብሷል ወፈር ያለና ማራኪ የአባትነት ድምፅ አለው፡፡ ሶስተኛው ሽማግሌ ሙሉ ጥቁር ሱፍ ኮስተር ያለ ፊት ረጅምና ጠይም ነው ወታደራዊ አቋም አለው ሲናገርም በተኮሳተረ ድምፅ ነው፡፡ ሶስቱንም አንድ ሚያረጋቸው ግን ንግግር አዋቂነታቸውና ሀብታምና በከተማው የተከበሩ መሆናቸው ነው፡፡ ብሩኬ ሰው መምረጥ ይችልበታል
"ተቀመጡ" አለች እማዬ
" የመጣንበት ሳናሳካ አንቀመጥም"
"ምንድነው የምታሳኩት ጉዳይ " አሉ የእናቴ ንሰሀ አባት "መቼም እኛ የመጣነው ከእናንተ ዝምድናን ፈልገን ነው የተከበረን ቤተሰብ በዝምድና ለማሰር" አሉ መሀል ያሉት ሽማግሌ
" እኮ በምን መልኩ ነው ዝምድናችንን እምትፈልጉት እኮ እንዴት" አባ ናቸው የሚናገሩት እናቴም እርሶ እያሉ እኔ አልቀበልም እርሶ ያውሩ ብላ ሙሉ መብት ሰታቸዋለች
"ልጃችሁን ለልጃችን ብለን" አሉ የመጀመሪያው ሽማግሌ
"ጥሩ እሱ ጥሩ ነው አምላክም የተቀደሰን ትዳር ይፈልጋል ቢሆንም ልጃቹህ ማነው?"
" ልጃችን የተከበረ ጥሩና የተመሰገነ በሀሪ ያለው ነው ልጃችሁንም እስከ እድሜ ፍፃሜው በፍቅርና በደስታ የሚያኖር ነው ስሙም አቶ ብሩህ ይሁነኝ ይባላል"
"መልካም ማለፊያ ነው ልጃችሁ ምን አለው ለልጃች የሚመጥን"
"ልብ አለው እንደው ለልጃችሁ የሚመጥን ከልብ ሌላ የሚሰጣት ባይኖርም አለማዊ ሀብት ካላችሁ ሞልቶ የተረፈው ነው ሰርቶ የሚያምን ጥሩ እና ሀቀኛ ታታሪም ነው"
"ጥሩ እንግዲ ለዛሬ ሳምንት ውሳኔያችንን እናሳውቃለን ምን ትላላችሁ እናንተስ"
"እሺ መልካም ፈጣሪ ለዛ ያድርሰን" በመጡበት እግራቸው ሳይቀመጡ ወጡ በጣም ደነገጥኩ ከሄዱ በኋላ አባ ለእናቴ "መቼም አሰካለማርያም ልጆቹ ተዋደዋል ቢሆንም ትንሽ መልፋት አለባቸው ልጃችንን ዝም ብሎ ማግኘት የለም ሳምንት ሲመጡ መልስ እንሰጣለን" ብለው እኔን ከውስጥ እንድጠራኝ ነገራት መጥቼ መስቀል ተሳልሜ ተባርኬ አጠገባቸው ቁጭ አልኩ
" እህተ ማርያም እንደው መልካም እና የተባረከ ትዳር ይሁንልሽ መቼም ልጄ ሁለታችሁ ነገሩን ሁሉ ፈጥማቹህ እንደው ለወጉ ቢሆንም ሽማግሌ የተላከው ወግና ስርአቱን ባህሉን መጠበቅ አለበት ሳይቀመጡ የሸኘናቸው ልጃችን ገና በመጀመሪያ ጥያቄ አንስተን አንወረውርም ብለን ነው ቀጣይ በቀጠሮአቸው ሲመጡ እንደፈጣሪ ፍቃድ መልሳችንን እናሳውቃቸዋለን ያኔ ምናምንም ቀምሰው ይሄዳሉ እሺ ልጄ"
"እሺ አባ መልካም " ምግብ ቀርቦ ቡና ተፈልቶ መጨዋወት ተጀመረ፡፡ ብሩኬን በስልክ ላወራ መኝታ ቤት ገባሁ ያለውን ሁሉ ነገርኩት አወራን ሳምንት እሺታ እንደሚሰጥ ተማምኗል በኋላ እንደምንገናኝ ተቀጣጥረን ስልኩን ዘጋሁት በዛው ትንሽ አረፍ አልኩ ቤቲዬ አጠገቤ መታ ከጎኔ ጋደም አለች፡፡
ከብሩኬ ጋር የተቀጣጠርንበት ሰአት ሲደርስ ከቤቲ ጋር ወጣን እሷም ወደቤቷ እኔም ወደ ፍቅሬ ሄድን

ክፍል-23 ይቀጥላል.....ከተመቻችሁ

#አስተያየት ካላችሁ...

@Babilove12

#joine #share

https://t.me/Ethioenku
90 views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 12:45:19

87 views09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 20:11:20 #ምትኬ

#ደራሲ_HiLA

ክፍል-21

ሂወት በድግግሞሽ የተሞላች ነገር ግን ሰርክ አዲስ የሆነች የምትጣፍጥ የምታጓጓ ናት ዛሬ ያስተዋልናትን ፀሀይ ነገም ደግመን ማየት እንናፍቃለን የትላንቱን ዝናብ፣ አየር አበባ ተክል ሌላው ቢቀር የማንወደውን የጠላነውን ሰው እንኳ ነገ ማየት እንሻለን ዛሬ የሰራነውን ነገ ስንደግመው አይሰለችንም ህይወት የድግግሞሽ ውጤት ብትሆንም ሁሌ ተናፋቂና አዲስ ናት በተለይ ደግሞ የምንወዳቸው ሰዎች በዙሪያችን ሲሆኑ ሂወት ታሳሳለች እኔ አሁን ላይ ፈጣሪ በብዙ ሰዎች ባርኮኛል እናቴን የማፈቅረውን ብሩክን እህት የሆነች ጓደኛዬን ቤቲዬን ልጄ ሴናን የእማዬ አጋዝ ፈለቁን እነዚህን ሁሉ ወደሂወቴ አምጥቶ ደስተኛ አርጎኛል ታድያ ከዚህ ወዲያ እኔ ምን አነሰኝ ፈጣሪንስ ምን እጠይቃለሁ? ምን የጎደለኝ አለና ደፍሬ ጠይቀዋለሁ? አምላክን ማማረር አይሆንብኝም? እንደው ብጠይቀው አምላክ እራሱ አይታዘበኝም?
አሁን ላይ አንድና አንድ ሀሳቤ ከብሩኬ ጋር መጋባት መሞሸር እናቴን እንደምትለው አለሟን ማሳየት ነው የኔ ሀሳብ ፈጣሪ እድሜ ጤና በዙሪያዬ ያሉቱን ሀሉ ይስጥልኝ እንጂ ሌላው ሁሉ ትርፍ ነው
ይኸው ስራ ከጀመርኩ 1አመት ሞልቶኛል እኔና ብሩኬ ለወደፊት ቤታችን አንዳድ ነገሮች እያስተካከልን ነው በርግጥ የብሩኬ ቤት የተሟላ ቢሆንም ያው ከአንድ ሁለት ያውም የትዳር አጋር ሲኖር አንድ አይደለምና ብዙም ባይሆን ነገሮችን እያስተካከልን ነው ብሩኬ እማን አብራን እንድትኖር ቢፈልግም የኔ እናት ግን ፈቃደኛ አይደለችም በቃ እማ እንዲ ናት "ልጆች ከተጋቡ ትዳር ከያዙ በኋላ ከቤተሰብ መራቅ አለባቸው ምክንያቱም እንደው አይደለም ሰው እና ሰው ጥርስና ጥርስም ፣ ምላስና ጥርስም ይጋጫል እና በነፃነት ለመነጋገር አይችሉም ሁሉም ቤተሰብ ለልጁ ስለሚያደላ አንዱን ማስቀየሙ ሆድ መሻከሩ አይቀርም ስለዚህ ቃሉም ሰው እናትና አባትን ይተዋል ከሚስቱም ይጣበቃል ተብሎ ተፅፏል መራቅ አለባቸው" ብላ ታስባለች
እማዬ በዚህ ሀሳቧን ብደግፋትም ከአጠገቤ እንዳትርቅ ስለምፈልግ ብዙ ለመንኳት እሷ ግን "ይኸውልሽ ምትክ አባትሽ ጥሎኝ ወደ መኖሪያው ወደ እርስቱ ሰማይ ቤት ሲሄድ እኔ እዚች የኪራይ አለም ላይ ብቻዬን እንዳልሆን አምላክ አንቺን የአይን ማረፊያዬን ብሌኔን ሰጠኝ ደግሞ አንቺ እንደምታገቢ ቤተሰብ እንደምትመሰርቺ አምላክ ሲያስተካክል ሴናን አጫዋች የብቻዬ ልጅ አርጎ ሰጠኝ እና የኔ ልጅ አጠገብሽ ነኝ ግን ደግሞ አንድ ቤት አንኖርም ይሄ ቤትሽ ነው በፈለግሽው ሰአት መምጣት ትችያለሽ" በቃ የእማን ቃል ማስቀየር ስለሚከብድ ቤቱን በጥሩ ሁኔታ አሳደስነው ሴናዬ ልጄም ምንም እንዳይጎልባት በማሰብ ሁሉን አስተካከልን አሁን የኔም የብሩኬም ቤተሰቦች ሰርጋችንን ብቻ መጠበቅ መናፈቅ ጀምረዋል የብሩኬ እናት ሽማግሌ ለመላክ በጣም ጓጉተዋል እማዬም እንደዛው እኔ ያን ያህል የተጋነነ ሰርግ አልፈለኩም ብሩኬም በሀሳቤ አልተናደደም እናቶቻችን ግን እንኳን ሊስማሙ ጭራሽ አኮረፉን ቁጣቁጣም አላቸው የነሱ ፍላጎት ማሟላት ስለሆነ ሀሳባችን ሁሉንም ነገር በሚፈልጉት ያህል እንዲያስቡና እቅድ እንዲያወጡ መብት ከመስጠት ውጪ ምንም ማረግ አልቻልንም፡፡ የኔ ብሩክ ከመጋባታችን በፊት ስራ እንድለቅና የራሴን ቢዝነስ ሊከፍት ቢጠይቀኝም ፍቃደኛ አልሆንኩም ከተጋባን በኋላ ማስተርሴን መማር እንደምፈልግ ነግሬው ተስማምቷል "እናት በፈለግሽው መስክ የፈለግሽውን ቢዝነስ ጀምሪ እባክሽ በወር ከምጠብቂ የራስሽን ነገር ልክፈትልሽ ይህን ያህል ጊዜ ሰራሽ አይደል በቃ አሁን የሆነ ነገር ልክፈትልሽ"
"ብሩኬ ስራውን እኮ ወደዋለሁ ስራዬ ለኔ ብቻ አይደለም የሚጠቅመው እኔ ስሰራ እናቴ ደስ ትሰኛለች ትኮራለች 'ልጄ ተምራ ተመርቃ ስራ ይዛልኛለች' ትለኛለች የአባቴ ነብስ ዘወትር በኔ ደስ የምትሰኘው ስሰራ ነው ብሩኬ ቢያንስ የተማርኩበትን እንኳ መስራት አለብኝ"
"አሁንም እኮ ስራ ትተሽ ቁጭ በይ አላልኩም ግን ተቀጣሪ መሆን ይብቃሽ ነው ያልኩት"
"ገብቶኛል እኮ ፍቅር ትንሽ ጊዜ ለፍቶ ማግኘትን ሰርቶ መብላትን ልየው እናቴም ብትሆን የላቤን ሳበላት ነው ደስ የምትሰኘው ስራውም ቢሆን አድካሚ አይደለም እኮ ታቀው የለ አሁን እኮ በደንብ ለምጄዋለሁ "
"በቃ አንቺ ግትር ካልሽ እሚመልስሽ የለማ ደግሞ እኮ በምንም ማሳመን አልችልም አንቺን ወይጉድ በቃ የኔሚስት መቼም አትረቺማ "
"ሴት አይደለሁ እማዬ ሴት ልጅ ብልሀተኛ እና ባሏን በፍቅር እምታሸንፍ መሆን አለባት ትላለች ለዛ ነው"

ክፍል22 ይቀጥላል.....ከተመቻችሁ

#አስተያየት ካላችሁ...

@Babilove12

#joine #share

https://t.me/Ethioenku
102 views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 21:04:04 #ምትኬ

#ደራሲ_HiLA

ክፍል20

ወደታች ተያይዘን ወረድን ደስ የሚሉ ሰአታትን የሚጣፍጡ የሚያጓጉ ደቂቃዎች በየሰከንዱ አንዳች የተለየ ስሜትን የሚያጭር ነገር አለው ብሩኬ የት እንደሚወስደኝ ምን እንደሚያሳየኝ እየጓጓሁ ነው ግን መጠየቅ አልፈለኩም መጨቅጨቅ መስሎ ተሰማኝ ብቻ አንዴ ቀና አንዴ ጎንበስ እያልኩ በፈገግታ ከብሩኬ ጎን በደስታ ወደታች መውረድ ጀመርን ወደ ሆቴሉ የመዋኛ ቦታ ስንደርስ ቦታው በአበባና በሻማ የተዋበ ነበር አንድ ጠረጴዛ ብቻ አለ ጠረጴዛው በነጭ አበባ ከላይ እስከታች አጊጧል በጣም ነበር የሚያምረው በሚገርም ሁኔታ በውበቱ እየተገረምኩ ልክ ጠረጴዛው አጠገብ ስንደርስ ሁለታችን ቆምን ከዛ ብሩኬን ሄጄ በፍቃዴ ከንፈሩን ሳምኩት ጎን ለጎን ቆመን ከልብ እየሳቅን እያወራን እየተቃቀፍን እየተላፋን ወይናችንን እየጠጣን
" ብሌንዬ የኔ እናት"
" ወዬ ብሩክዬ"
" ታቂያለሽ አንቺን ያገኘሁ እለት ሁሉ ነገር ነው የተገለባበጠው ማንነቴን በሙሉ በአንድ ጊዜ ነው የቀየርሽው ታቂያለሻ እናቴን ሰጠሺኝ ማንነቴን ነው ያገናኘሽኝ እና ብሌንዬ......"
"ብሩኬ" ሳላወራ ጣቱን ከንፈሬ ላይ አስቀምጦ
"አስጨርሽኝ ዝም ብለሽ አዳምጪኝ ይኸውልሽ እናት አንቺ በአጭሩ ህይወቴ ነሽ አንቺን ካጣሁ መኖር አልችልም ብሌንዬ አንቺን ዘላለም የኔ አካሌ ቤቴ ክብሬ እንድትሆኚ ፈልጋለሁ እናት ዛሬ ዘላለም የኔ ትሆኛለሽ ሚስቴ ትሆኛለሽ " ብሎ ከፊቴ የቃልኪዳን ቀለበት ይዞ ተንበረከከ ያልጠበኩት በመሆኑ ቃል ማውጣት አቃተኝ እንባዬ በአይኔ ሞላ ቢያንስ ትንሽ ደቂቃ ቆይቼ እንደመባነን አረገኝ
"ብሩኬ ይህን ያህል ለኔ ይገባኝ ይሆን የኔ አባት" ብዬ አጠገቡ ተንበርክኬ
"የኔ ፍቅር አንተ የኔ በመሆንህ እኔ ደስተኛ ነኝ አየህ ብሩኬ ባሌ ሆነህ አብሬህ ለመኖር እመኛለሁ የልጅህ እናት እሆናለሁ" ብዬው ቀለበት ጣቴን ሰጠሁት ቀለበቱን አረገልኝ ግንባሬን ሳመኝ አለቀስኩ ተያይዘን ቆምን ተቃቅፈን ትንሽ ከቆየን በኋላ በቃ አለም ለኔ እና ለእሱ ብቻ የተሰራች እስኪመስለኝ ድረስ አለም ጠበበቺኝ ብቻ እስከ እኩለ ለሊት እዛው ቦታ ላይ አመሸን ብዙ ነገር አወራን ስለነገ አብረን አለምን ሁለታችንም ሲደክመን ተቃቅፈን ወደ ክፍላችን ገባን ሞቅ ብሎናል ስንገባ አልጋ ላይ ገዝቶ የተቀመጠ ፒጃማ ነበር እሱን አሳየኝ እስክቀይር ወደ መታጠቢያ ቤት ገባ እሱም ቀይሮ እኔም ቀይሬ ተቃቅፈን እያወራን ተኛን ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ ደረቱ ላይ ነበርኩ ዛሬውኑ ባሌ ቢሆን ተመኘሁ ግን ጊዜው ገና ሆነብኝ ቁርስ በልተን ወደቤት ሸኘኝ ከእማዬ ጋር ምሽቴን ሁሉ አወራሁ ሴናዬን ታቅፌ የእማዬን ምክር ተቀብዬ ከቤቲዬ ጋር አውርቼ ተኛሁ ነገዬ ናፈቀኝ አሁኑኑ ባሌ ቢሆን ብዬ ተመኘሁ ብቻ አምላክ ፍቅሬን ይጠብቅልኝ እንጂ ሌላው ሁሉ ትርፍ ነው

ክፍል 21 ይቀጥላል.....ከተመቻችሁ

#አስተያየት ካላችሁ...

@Babilove12

#joine #share

https://t.me/Ethioenku
116 views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 09:28:43 #ምትኬ

#ደራሢ ህሊና

ክፍል19

ፍቅረኛዬ አጠገብ ሳይሆን ሌላ ሰው አጠገብ የተቀመጥኩ መሰለኝ
"እንውረድ እናት?" በቃል ሳይሆን በአንገት ምልክት ሰጠሁት ቀድሞኝ ወርዶ የመኪናውን በር ከፈተልኝ ወረጄ ክንዱን እንድይዘው እጁን አስተካከለ ተያይዘን ወደ ውስጥ ገባን አንድ ልጅ እግር አስተናጋጅ ወደ እኛ ቀርቦ በሚገርም ፈገግታ "ሰላም አቶ ብሩክ ቦታው ተዘጋጅቷል እባካችሁ ተከተሉኝ " በአግራሞት ቀና ብዬ ተመለከትኩት ፈገግ ብቻ ብሎ ልጁን ተከተልነው ወደ ሆቴሉ የመጨረሻ ክፍል በመሄድ ከቴራዙ ላይ ወጣን በነጭ ጨርቅ ያጌጡ የንጉስና የንግስት ዙፋን የሚመስሉ አንድ ጠረጴዛ እና ሁለት ወንበር ብቻ ይታያል እየመራ እንድንቀመጥ ከጋበዘን በኋላ ለመታዘዝ በተጠንቀቅ ቆመ የሚጠጣና የሚበላ ካዘዝን በኋላ አስተናጋጁ ጥሎን ወረደ ቦታው በጣም የሚማርክ እይታ አለው ወደታች ከተማውን ስመለከት አንዳች የመብራት ትርኢት የማይ መሰለኝ ሰአቱ በመምሸቱ ጭለማውን ለማሸነፍ ከየአቅጣጫው የበሩት አምፖሎች አንዳች የተለየ ስሜትን ይፈጥራሉ ያውም ከልብ ሰው ጋር ሲሆን ዝምታችንን አንዳችን መስበር እንዳለብን ቢገባንም የደፈረ አልነበረም ድንገት ዞር ስል ፈዞ እየተመለከተኝ ነበር
"ምነው ብሩኬ" አልኩት እንደማፈር ብዬ
ምነው የኔን ሴት ማየት አልችልም?" በዚህ መሀል አስተናጋጁ የታዘዘውን ይዞ መጣ ከዛም የምንፈልገውን በየፊታችን ካስቀመጠ በኋላ "መልካም ጊዜ ሰአቱ ሲደርስ አሳውቆታለሁ አቶ ብሩክ"
"እሺ አመሰግናለሁ" የምን ሰአት ይሆን እየተገረምኩ "ብሩኬ የምን ሰአት ነው?"
"አይ ተጨማሪ ነገር አዝዤ ነው.... እእእ ምን ነበር ያልሽኝ ማየት አችልም ነው?" አለ ወሬ ለማስቀየር እንደሆነ ስለገባኝ ቀየርኩለት " ኧረ ትችላለህ እንደው ሀሳብ የገባህ መስሎኝ ነው" አልኩት የመጀመሪያ ጉርሻ እየተቀበልኩት ቀጥሎ ያዝነውን ነጭ ወይን እየቀዳ ነበር
"አይ ምን ያህል እድለኛ ነኝ የሚለውን እያሰብኩ ነው በዚህ ዘመን ከነ ሙሉ ክብሯ ያለችን ሴት ማግኘት እድለኝነት ነው በዛላይ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያላት ሰው ወዳጅ ሁሉን አክባሪ ለክብሯ ሟች በቃ አንቺ እኮ ሁሉን ሳይሰስት የሰጠሽ የእጁ ስራ ነሽ እናትሽ ቢጨነቁና ከሰው አይን ቢሸሽጉሽ አይፈረድባቸውም የሚያምር ፅጌረዳን ሁሉም መቅጠፍ ይመኛል ቀጥፈዋት ስደርቅ ለመጣል ከመንከባከብ ይልቅ ለጊዜያዊ ደስታ ያጠወልጓታል አንቺንም እናትሽ እንዳጠወልጊ ስለሚሹ ነው የሚከላከሉልሽ" አውርቶ ሲጨርስ እኔም አጎረስኩት
"ብሩኬ ግን እኮ እኔ ይህን ያህል አይደለሁም በዛ ላይ ሁሉም እናቶች ለልጆቻቸው እንዲህ ነው ሚያስቡት... ግን ብሩኬ ድፍረቱን ከየት አገኘህ እማዬን የመጠየቅ?" አልኩት መብላቴን እየቀጠልኩ የጎረሰውን በወይን ካወራረደ በኋላ " በቃ ናፈቅሽኝ ናፍቆትሽ ሲያሸንፍ ልቤ ላይ አንዳች ሀይል ሰጠኝ አንቺነትሽ ከኔ ሲገዝፍ ይዘሀት ጥፋ አለኝ ለእማማ ሳላስፈቅድ ብወስድሽ ምን አልባት ገና ሳንጀምር እንጨርስና ወደ ቤት መሄድ ትፈልጊያለሽ ያለኝ ይሄ ብቻ ነበር" በመሀል ለተወሰኑ ደቂቃዎች በልባችን እያወራን ተመገብን ከዛም አስተናጋጁን በእጁ ምልክት ሰጠውና እንዲያነሳ ጠየቀው ወደኔ ጠጋጋ ብሎ ተቀመጠ አሁን በነፃነት ወይናችንን መጠጣት ጀመርን መሳሳቅ መጫወት መላፋት ደሞ መሳቅ ደሞ ማውራት ፍርሀቴ ተኖ ጠፍቶ እሱን ብቻ እያየሁ ደስተኛ ሆንኩ ብሩኬ በእጆቹ አቅፎ ክንዶቹ ላይ ጋደም አርጎኝ የፈራሁትን ጥያቄ ጠየቀኝ
" ብሌን ፈርተሻላ አብረን በማደራችን"
" አዎ ብሩኬ በጣም "
" ክብርሽን ለኔ መስጠት ትፈልጊ የለ ለምን ፈራሽ"
"ብሩኬ ሳንጋባ አይሆንም"
"አውቃለሁ እኔም እንዳፈሪ ነው ምፈልገው ሌላው ቢቀር ያመኑኝን እማማን ቃል አልበላም አፈቅርሻለሁ" ብሎ ከአገጬ ቀና አርጎ ከንፈሬን ጎረሰው ትንፋሽ እስኪያጥረኝ ሳመኝ መላ አካላቴን አንዳች ስሜት ውርር አለኝ እየሳምኩት ነው ግን እንዴት እንደሆነ አላቀም እሱ እየመራኝ ረዘም ላለ ጊዜ ሳንላቀቅ ቆየን በመሀል ድምፅ የሰማን ስለመሰለን ተላቀን ዞር ስንል ምንም አልነበረም ከጎኔ ብድግ ብሎ "መጣሁ እሺ እናት አልቆይም" ብሎ ግንባሬን ስሞኝ ተነሳ ምነው ባይነሳ እንደው እንደተቃቀፍን እንደተሳሳምን ቀናት ዘመናት በላችን ላይ ባለፋ እንደው ምናለ በተቀመጥንበት በሸበትን በጃጀን ባረጀን እንደው ጊዜው በላችን እንደ ዳመና ከበላያችን በከነፈ ብሩኬ ትንሽ ቆይቶ ተመልሶ መጣ "እናት ወደታች እንውረድ"
"ለምን ብሩኬ ቦታው ደስ ይል የለ በእናትህ እዚሁ እንሁን"
" አንድ ማሳይሽ ነገር አለ ነይ"

ክፍል 20 ይቀጥላል.....ከተመቻችሁ

#አስተያየት ካላችሁ...

@Babilove12

#joine #share

https://t.me/Ethioenku
109 views06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 21:14:08 #ምትኬ
#ደራሲ_HiLA
ክፍል 18
ሴና ያለ እናቷ ትንሽ ጊዜ ብታስቸግርም ውስጧ ነገራት መሰለኝ ለመደችው አሁን ዝምተኛ ልጅ ሆናለች፡፡ እናቴን እምታግዛት ልጅም ተገኝታለች ሂወት እንደገና መስመሯን እየያዘች ነው ጥሩ እየሄደች ነው ብሩኬ ካሰብኩት በላይ የዋህና ቅን ሰው ነው በየጊዜው መጥፎ ማንነቱን እያስወገደ መልካምነትን ይላበሳል የሴን ስድስት ወር እና የኔ እና የሱን ስድስት ወር በጥሩ ሁኔታ አክብረነዋል ከልጃችን የልደት ቀን ጋር የፍቅር ቀናችን በመግጠሙ የተለየ ደስታ ነበረው፡፡
ዛሬ ብሩኬ ቆንጆ ሆኜ እንድመጣ ብቻችንን ጊዜ ማሳለፍ እንዳለብን ነግሮኛል እራት አብረን እንድንበላ እያሰበ ነው ከመቼውም በላይ አምሬና ተውቤ ለአለባበስ ምርጫዬ ቤቲዬ እና እማዬ እጃቸው አለበት ከቤቲ ጋር ብቻችንን ስንሆን የልቤን ጠየኳት
"ቤቲ እንደው ልቤ ፈርቷል?"
" ለምን ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ?"
" ምንም ግን ብሩክ እስከዛሬ እንደዚህ አይነት ፕሮግራም ይዞ አያቅም በዛ ላይ ቤቲ ስሞኝ እንኳን አያቅም አንገቴን ወይ ግንባሬን ካልሆነ በቀር ዛሬ ግን ለምን እንደሆነ እንጃ ልቤ ፈርቷል"
"ውይ የኔ እህት አትፍሪ መቼም የወደፊት ሚስቴ ያላትን ሴት ደፍሮ አያስገድም አንቺ ደግሞ ውሳኔሽን እንደማትለውጪ ንገሪው ምን አልባት አንቺ ዝም ብለሽ ይሆናል እኮ እሱ አላሰበው ይሆናል"
"እንዳፍሽ ያርግልኝ የራሱ አይደለሁ ስንጋባ ይደርስ የለ ብቻ ፈራሁ?"
"አይዞሽ የኔ ቆንጆ አምሮብሻል ደሞ ከአይን ያውጣሽ"
ተዘጋጅቼ እንደጨረስኩ ለብሩኬ ደወልኩ እየመጣ እንደሆነ ነገረኝ ከዛም ብዙም ሳይቆይ በር ተንኳኳ ቤቲ ከፈተች ብሩኬ ነበር
" ሰላም ለዚህ ቤት? ደና ዋላችሁ የብሌን እናት?" ብሎ ቤቲን ሰላም ብሎ ገባ እማዬም ከጓዳ መታ ጨበጠችው አምሮበታል የተለየ ግርማን አላብሶታል የለበሰው ውሀ ሰማያው ሸሚዝ ከግሬይ ጨርቅ ሱሪው ጋር የሆነ ሙሽራ አስመስሎታል ብሩኬ አለባበስ ዝነጣ ይችልበታል ቁመቱ ተክለሰውነቱ ምንም ቢለብስ እንዲያምርበት ይረዱታል ፀጉሩ በሚገባ ተስተካክሏል ሸሚዙን የተወሰነ ያህል ከፍቶታል ያንገት ሀብሉ ከመሀተቡ ጋር ተዳምሮ እዛ ሰፊ ደረቱ ላይ የተለየ ግርማን አላብሰውታል በእጁ ያሰረው ቅንጡ የእጅ ሰአት ከሸሚዙና ከእጁ ጋር ተስተካክሎ ተቀምጧል የተጫመተው የቆዳ ጫማ በአግባቡ ተወልውሎ መሬት ላይ ለመራመድ ያሳሳል በአጠቃላይ ሳየው ልቤ ደግሞ ደነገጠለት ሌላ ሴት ባታየው ብዬ ተመኘሁ ሰውሬ ላስቀምጠው ፈለኩ
"የኔ እናት በጣም አምሮብሻል" የብሩኬ ንግግር ከሀሳቤ አባነነኝ
"እኔ ምለው ሳትነግሩን ልትጋቡ ነው? ወይስ ሰርግ አለባቹሁ?" ቤቲ ነበረች ጠያቂዋ "እውነቷን ነው ይሄ ሁሉ መሽቀርቀር ምንድነው?" እማዬም ቀጠለች "መቼም የብሌን እናት ወግና ስርአቱን ረስተን ይቺን ተጠብቃ የቆየች ውድ እንቁ ልጅ እንደ ፌስታል አከንጠልጥዬ አልወስዳት የናቷን ምርቃት ሳልቀበል ቤቴ ይዣት አልገባም ግን ዛሬ አብረን እንድናሳልፍ ነበር ፍላጎቴ ፈቃዶት ከሆነ"
"አብረን እንድናሳልፍ ስትል እንዴት ማለት ነው አልገባኝም" "ማለቴ ምሽቱን ከኔጋር እንድታሳልፍ ማለቴ ነው ቨሌላ ነገር አይውሰዱብኝ ብሌን ከነ ክብሯ መሆኗን አቃለሁ እኔም ከሰርጋችን በፊት ላልነካት በእግዚአብሔር ስም ቃል ለራሴ ገብቻለሁ ግን በቃ ዛሬ የተለየች ቀኔ ትሆን ዘንድ ፈለኩ መቼም ከሰርጋችን በፊት አልነካትም ፈጣሪ ምስክሬ ነው ግን ዛሬን አብራኝ እንድትሆን ይፍቀዱልኝ" ይሄን ሲያወራ ቤቲ እና እኔ እየተያየን ነው ደግሞ እንደማፈር እላለሁ እማዬ ፊቷ ላይ ምንም ማንበብ አቃተኝ ዝም ብላ ሁላችንንም ካስተዋለች በኋላ
"ይኸውልህ ልጄ ንቀከኝ ነው ብዬ አልልም ብትደፍረኝ ፍቃዴን አጠይቅም ግን እሳት እና ጭድ ጎን ለጎን ካሉ አንዱ አንዱን ያሸንፋል ያንን ነው ምፈራው በርግጥ ህፃናት አይደላችሁም ግን ከነ ክብሯ ነው ለባሏ መስጠት ያለብኝ ብዬ ስለማስብ ነው እንደው ፈጣሪ ባይፈቅድና አንተን ባታገባ ልጄ ሁለት ያጣች ትሆንብኛለች ወንድ ልጅ ደግሞ አንዴ ክብር እንደሌላት ካወቀ ካገኘችው ጋር እምትጋደም ነው አርጎ ሚስላት አልጋ ላይ ሊያቃት ሚገባው ባልዋ ብቻ ነው ስለዚህ አሁን አልከለክላችሁም ግን አደራ ብሌን እራስሽን ተቆጣጠሪ ሂዱ በሉ መልካም ጊዜ" ብሩኬ ከወገቡ ጎንበስ ብሎ እጇን ሳመ አመስግኖ ተያይዘን ወጣን ምንም ሳንነጋገር አንድ ሆቴል ጋር ስንደርስ መኪናውን አቆመ ብሩኬ ለምን እንደሆነ ባላቅም ያለ ወትሮው ዝምታው እጅግ በዛብኝ እኔም ውስጤ እጅግ ፈራ ለምን እንደሆነ ባላቅም መመለስ አማረኝ....

ክፍል 19 ይቀጥላል.....ከተመቻችሁ

#አስተያየት ካላችሁ...

@Babilove12

#joine #share

https://t.me/Ethioenku
110 views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 21:52:11 #ምትኬ

#ደራሲ_HiLA

ክፍል 17

ሴናን ከተኛችበት ብድግ አርጌ ማባበል ጀመርኩ እናቴ ትንሽዬ ብጫቂ ወረቀት ከሴና ስር አገኘች
" ልጄን አደራ ብሌን ልጅሽ ናት አልመለስም ከዚህ በኋላ " ይላል ወረቀቱ ገና ጡት ያልጠገበች ህፃን ጥላ መሄዷ እጅግ አበሳጨኝ ራስወዳድ ሆና ታየችኝ ይቺን ትንሽ ልዕልት ለመተው ከሆነ ለምን ወለደቻት እናትነት ክብሩን አጣብኝ ነገ ሴና አድጋ ማንነቷን ታሪኳን ስጠይቅ ምን ይመለስላታል ብቻ ግራ እየተጋባሁ ነበር
ሴናን እንደምንም አባብዬ እናቴን ጠየኳት
"እማ እንደው አንጀቷ እንዴት ቻለላት የወለደቻትን ለመጣል ቆይ ግን እናቴ እዚሁ ብትኖር ምን ትሆናለች"
"አይ የኔ ልጅ አንጀቷማ እንዴት ይችላል ብለሽ ማን ያውቃል ይህን ስትወስን ከራስዋ ጋር ስንቴ እንደተጣላች ምን አልባትም በሂወቷ ትልቁን ውሳኔ ይሆናል እያነባች የወሰነችው ወይ ደግሞ እንዳልሽው እራስ ወዳድ ሳትሆን የልጇን ነገ መስመር እያስያዘች እንዳለችውም ታሪክ እየፃፈችላት ይሆናል ብቻ አንድ ነገር እርግጠኛ እንደነበረች አስባለሁ ልጇን ቤተሰብ ሰታታለች እናት አርጋሻለች ለሷ ካንቺ የተሻለ እናት እንደማታገኝላት ታውቅ ነበር ከብሩክ የተሻለ አባትም ከየትም አይመጣም ስለዚ አሁን ልጄ ሰናይትን መውቀስ አቁሚ የሷን ጉዳት ማንም አይጎዳም ልጅሽን ብቻ አምነሽ ተንከባከቢ ነገ የሚሆነው አይታወቅም ፍርዱን ለባለቤቱ ስጪ"
በቃ እማ እንዲ ነች ማንንም አትወቅስም ማንም ላይ እጅ አጠቁምም ሁሉም ነገር የራሱ ምክንያት አለው ብላ ታምናለች መሆን ስላለበት ሆነ ትላለች፡፡ እማዬ የተለየች ናት ሁሌም እኔ በሆነ ጉዳይ በንዴት ስብሰለሰል የሆነ ነገር ብላ እንዳስብ ታረጋለች ከራሴ ጋር ታስታርቀኛለች፡፡ ዛሬም እንደ ሁልጊዜው አረጋጋችኝ ወደስራ መግባት ስለነበረብኝ ተነስቼ ሻወር ወሰድኩ ስጨነቅ ስናደድ ሻወር ያረጋጋኛል ቀጥዬ ለብሩኬ ደውዬ የተፈጠረውን ነገርኩት
" የኔ እናት በቃ አንቺ ተረጋጊ ሴናን እናሳድጋታለን ከስራ ስትወጪ በደንብ እናወራለን መቼም ልጃችን አትከብደንማ"
"አዎ ብሩኬ በቃ ላሳውቅህ ብዬ ነው ቻው እወድሃለሁ "
"እኔም የኔ እናት አፈቅርሻለሁ መልካም ቀን"
በዚሁ ጨራርሼ ስራ ገባሁ እማዬ እየገረመችኝ እየተደነኩ የስዋ ልጅ በመሆኔ እየተደሰትኩ ስራዬን መስራት ቀጠልኩ የሻይ ሰአት ላይ ከቤቲ ጋር አወራንበት ቤቲ በሚገርም ሁኔታ መጀመሪያውኑ ጠርጥራ እንደነበር ነገረችኝ ገረመኝ ብቻ ብዙ ነገር አወራን ቤቲዬ በሚገርም መንገድ እንዳየው አረገችኝ
"ብሌንዬ ምንአልባትም እኮ እናተጋር መኖሯ ለሷ ምቾት አልሰጣት ይሆናል አሁን እንደምታይው ኑሮው ከብዶ የለ ምንአልባት ስራ ለመስራት አስባ ይሆናል ጥላት የሄደችው ደግሞ ለእናቷ ነው የሰጠቻት አንቺ እኮ ክርስትና እናት ነው በሀይማኖታችን መቼም ክርስትና እናት ከእናት በላይ ነው መሆን ያለበት የቃልኪዳን ልጅሽ ናት ስለዚህ አልጣለቻትም ቤቷ እናቷ ጋር ጥላት ነው የሄደችው መቼም ትንሽ እሚከብደው አመት እንኳ ጡት ሳጠባ መሆኑ ነው እንጂ ብዙ አታካብጂው"
ልክ ናት እኔ የሴና እናት ነኝ ስለዚህ ሀላፊነት አለብኝ ሰናይት ግን የት ይሆን የሄደችው ስለሷ አንድ እንኳ እሚያቅ የለም ሰፈሯን እንጂ ቤት የላትም እስቲ ከብሩኬ ጋር ተነጋግረን እንወስናለን፡፡ ከስራ ስወጣ ብሩኬ መጥቶ ወሰደኝ አንድ ካፌ ቁጭ ብለን ማውራት ጀመረን
" ብሩኬ መጀመርያ እንዴት ብስጭት ብዬ እንደነበር እማዬና ቤቲ ሲያወሩኝ ተረጋጋሁ እንጂ"
" በቃ ተያት አሁን ስለ ልጃችን እናውራ ምን ተሻለ እማማ መቼም ብቻቸውን አይችሉም አይደል ?" ብሩኬ እናቴን እማማ ነው ሚላት እሷ ፊት ሲሆን ደግሞ የብሌን እናት ይላታል፡፡
" አዎ ግን እኮ ብሩኬ አሁን ላይ ባለው ሁኔታ ሞግዚት መቅጠር አልችልም የእማዬን ደስታ ፈልጋለሁ ቤት ላሳድስ ብር እያጠራቀምኩ ነው "
" አልገባኝም ቤቱን ለማሳደስ ሳነግሪኝ ነበር መደበቅ ጀመርሽ"
"ብሩኬ እንደዛ አይደለም ብዙ ነገር ተደራረበ ለዛ ነው ብነግርህ ካላሳደስኩ ትላለህ ወጪ በዛብሀ"
"እሺ ጥሩ አሁን ስለሱ አናወራም ሴናን እማማ ይንከባከቧ ቤት ውስጥ እምታግዛቸው ነገ እንፈልጋለን"
" እሺ ከየት እናገኛለን ጥሩ ሰው"
" ከደላላ ቤት ወይም በሰው በሰው እንፈልጋለን ሴናዬም እያደገች ነው 6 ወር ሊሆናት እኮ ነው አይገርምም"
"እኔ እና አንተም 6 ወር ሊሆነን ነው "
"አዎ አንቺ ፍቅሬን ከተቀበልሽ እኔ ካፈቀርኩሽ ግን ከዛ በላይ ሆኖኛል ብሌን መቼ ነው ሚስቴ ማረግሽ" አንዳች ነገር ውስጤን ወረረው እንባዬም መጣ ደስም አለኝ
"ፈጣሪ ሲፈቅድ ነዋ ባሌ ምትሆነው"
"ብሌኔ ከኔበፊት ፍቅረኛ ይዘሽ ታቂያለሽ? ወንድስ ታውቂያለሽ?"
"አንተ ስንት ሴት ታውቃለህ? የኔን ከመመለሴ በፊት "
"በፍቅር ከሆነ አንድ ሴት ናት ልቤንም ማንነቴንም የቀማኝችን ሙሉ ያረገችኝ በስሜት ከሆነ ግን ብዙ ሴት አውቃለሁ የአንድ ለሊት ትውውቅ ሲነጋ መልኳን እማላስታውሳት ብዙ ሴት አውቃለሁ ብሌን በፍቅር የመጀመሪያዬም የመጨረሻዬም ነሽ"
"እኔ ግን ካንተ ውጪ ማንንም አላቅም ለፍቅርም ለሁሉም የመጀመሪያዬ ነህ የመጨረሻዬ እንድትሆን ምኞቴ ነው "
ብዙ ነገር አውርተን ፍቅር ተነጋግረን የተወሰነ እቅዶች አውጥተን ወደ ቤት ሸኘኝ ሴናንም በዛው አይቷት ወጣ.....

ክፍል 18 ይቀጥላል.....ከተመቻችሁ

#አስተያየት ካላችሁ...

@Babilove12

#joine #share

https://t.me/Ethioenku
111 views18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ