Get Mystery Box with random crypto!

የውል ቃሎችና ድንጋጌዎች አጠቃላይ ፍረጃ /General classification of Contractu | Ethio Construction

የውል ቃሎችና ድንጋጌዎች አጠቃላይ ፍረጃ /General classification of Contractual provisions/

የውል ቃላትና ድንጋጌዎች የስራውን ስፋት፣ መሰጠት የሚገባቸው አገልግሎቶችን፣ የአሰሪውና የሥራ ተቋራጩን መብትና ግዴታዎች ዝርዝር፣ የሥራ ተቆጣጣሪው/አማካሪው መሃንዲስ የስራ ድርሻዎች፣ ባለሞያዎች አሟልቶ ስለመስራት፣ የፕሮጀክት መሪ ባለሞያ  ተግባርና ሃላፊነቶች፣ የውል ቃላት ትርጉምና የመሳሰሉ አጠቃላይ ሁነቶችን የሚይዝ ሲሆን ከውሉ ጠቅላላ ሁኔታዎች በተጨማሪ ከሚሰጠው አገልግሎት የተለየ ባህሪ ጋር የሚሄዱ ልዩ ሁነቶችን/Special conditions/ እና ሥራው የሚከናወንበትን ቦታ የሚያመለክቱ ዝርዝር መረጃችን አካቶ የሚይዝ ነው፡፡

የውል ድንጋጌዎች በሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር /MoWUD/፣  በኢትዮጵያ መንግስት ግዢዎች ኤጀንሲ /PPA/ ፣ እና በዓለም አቀፍ አማካሪ መሃንዲሶ ፌደሬሽን /FIDIC/ ሰነዶች ውስጥ የተለየ አቀራረጽና አቀማመጥ ይዘው የተዘጋጁ ቢሆንም አጠቃላይ ይዘታቸው ላይ ግን እምብዛም ልዩነት የላቸውም።

በመሆኑም የውል ቃላትና ድንጋጌዎችን አሁን በሃገራችን በስፋት የምንጠቀምበትን የኢትዮጵያ መንግስት ግዢዎች ኤጀንሲ /PPA/ ሰነድን በመጠቀም የውል ድንጋጌዎችን በይዘታቸው በአጠቃላይ በ6 ልንፈርጃቸው እንችላለን።እነዚህም:

1.ጊዜን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች/Time provisions/

2. ስለክፍያ/ቀብድ/መተማመኛ/Payment related provisions/

3.የሥራ ተቋራጩ፣ የአሰሪውና፣ የመሃንዲሱ ግዴዎችና ሃላፊነቶች/Parties Obligation/

4.ውል ስለመፈፀምና ስላለመፈፀም እና  ስለሚያስከትሉት ውጤቶች ጋር ተዛማጅ የሆኑ የውል ድንጋጌዎች /Performance and Nonperformance of contract and their effect/

5.ልዩ ልዩ ሁነቶች /Conditions /

6.ባለአማራጭ ሃሳብ ድንጋጌዎች/Alternative Provisions ናቸው።

በሌላ ጊዜ በምናቀርባቸው ፅሁፎች በእያንዳዱ ስር ስለሚካተቱት ድንጋጌዎች ዝርዝርና በእያንዳንዱም ላይ ማብራሪ የምንሰጥ ይሆናል።

https://t.me/ethioengineers1