Get Mystery Box with random crypto!

ለመጀመሪያ ጊዜ 26 የአለም ሀገራት የሚሳተፉበት የኮንስትራክሽን አውደርእይ ሊካሄድ ነው ይሄ የ | Ethio Construction

ለመጀመሪያ ጊዜ 26 የአለም ሀገራት የሚሳተፉበት የኮንስትራክሽን አውደርእይ ሊካሄድ ነው

ይሄ የተባለው በዛሬው እለት የከተማ ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ጫልቱ ሳኒ የኮንስትራክሽን አውደርእይ በተመለክተ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው ።በመገለጫቸው የኮንስትራክሽን ዘርፉ 19 በመቶ ያህል በኢኮኖሚ  እድገት ላይ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ጠቅሰው ሆኖም የተለያዩ የግብአት ችግሮች በተለይ የሲሚንቶ እጥረት  ለዘርፉ ማነቆ መሆኑን መግለፃቸው ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

ይህንን እና መሰል ችግሮችን ይቀርፋል የተባለለት ቢግ 5 ኮንስትራክሽን ሲምፖዚየም እና የንግድ ትርኢትን መዘጋጀቱን ሚኒስትሯ ገልፀዋል። ይህም የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ DG ኢቨንትስ እና ከሀገር አቀፉ አጋር ኢትኤል ኢቨንት እንዲሁም የሲምፖሲየሙ ስትራቴጂክ አጋር ከሆነው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ በመሆን ከግንቦት 10 እስከ 12 ቀን 2015 በሚሊኒዬም አዳራሽ  በጋራ እንደሚያካሂዱት አንስተዋል።

ይሄ ለመጀመሪያ ጊዜ  የሚካሄደው ሲምፖዚየም 26 የአለም ሃገራት ብሎም  116 አለም አቀፍ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት ሲሆን 6000 ተሳታፊዎች ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል።

የግንባታው ዘርፍ ማነቆ የሆነውን ከአቅም ውስንነት ጋር የሚያያዙ ችግሮችን በቴክኖሎጂ ሽግግር ያለው ክፍተት የሚፈታበት ይሆናል ሲሉ አክለዋል።

ይህ ኮንስትራክሽን ዘርፉ ማነቆ የሆነበትን የግብአት  እጥረት በተለይ የሲሚኒቶ እጥረት ዙሪያ
አለም የደረሰበትን  የአመራረት ሂደት በዘርፉ ከተሰማሩት ልምድ እንዲወስዱ እድል ይሰጣል።

በመርሃ ግብሩ አምራች ተመራማሪዎች ፣ገዢና አቅራቢዎች ፣ከቱሪዝም ብሎም ከተማን ከማነቃቃት አኳያ እንዲሁም የኢትዮጲያን የገጽታ ግንባታ የምናሳይበት ነው ሲሉ ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ ተናግረዋል።