Get Mystery Box with random crypto!

#በሰው_መሬት_ላይ_ለተሰራ_ቤት_ሕጉ_ምን_ይላል አንድ ሰው የራሱ ይዞታ ባልሆነ መሬት ላይ | Ethio Construction

#በሰው_መሬት_ላይ_ለተሰራ_ቤት_ሕጉ_ምን_ይላል

አንድ ሰው የራሱ ይዞታ ባልሆነ መሬት ላይ ወይም በሌላ ሰው መሬት ላይ ቤት ከሰራ ከህግ አንፃር እንዴት ይታያል ለሚለው የፍትሀ ብሔር ሕጉን ቁጥር 1170 ና 1179 እናያለን።

የአንድ የመሬት ይዞታ ባለቤት በይዞታው ላይ የመጠቀም መብቱ የራሱ ነው፡፡ ሌላ ሰው በዚያ መሬት ላይ ህንፃ ወይም ቤት ሊሰራ አይችልም።ልስራ ካለም ባለይዞታውን በማስፈቀድ መስራት አለበት አለበለዚያ ባለይዞታው በመሬቴ ላይ ቤት መስራት አትችልም ብሎ መቃወም ይችላል።

ነገር ግን መሬቴ ላይ ቤት መስራት አትችልም እየተባለና ባለይዞታው እየተቃወመ በእምቢተኝነት በሌላ ሰው መሬት ላይ ቤት የሰራ ሰው በሰው መሬት ላይ በሰራው ቤቱ አንዳችም መብት የለውም። ባለይ ዞታው በመሬቱ ላይ እየተቃወመው ቤት የሰራው ሰው ሁለት አማራጭ የህገ መፍቴዎች አሉት

1. ለቤቱን መስሪያ ያወጣውን ወጪ ሳይመልስለት ቤቱን ለቆ እንዲሄድ ማድረግ ይችላል።

2. ቤቱን የሰራው ሰው በራሡ ወጪ ቤቱን አፍርሶ እንዲሄድ ለመፍቀድ ይችላል፡፡ ባለመሬቱ በይዞታው ላይ ባለመኖሩ ወይም በሌላ ምክንያት በመሬቱ ላይ ቤት የሚሰራውን ሰው በወቅቱ መቃወም ባይችልም ቤቱ መሰራቱን እንዳወቀ ቤቱን ማስለቀቅ ወይም ማስፈረስ ይችላል።

➥ስለዚህ የራስ ያልሆነ ይዞታ ላይ ቤት መስራት አይቻልም። ይቻላልም ከተባለ ባለመሬቱ ፍቃደኝነቱን መግለፅ አለበት።በመሬቱ ላይ ሌላ ሰው ቤት ቢሰራ እንደማይቃወም በግልፅ ወይም በዝምታ መፍቀድ ይችላል።

በግልፅ ወይም በዝምታ በመፍቀድ (ተቃውሞ ሳያቀርብ) በመሬቱ ላይ ሌላ ሰው ቤት ሲሰራ ያልተቃወመ ወይም የተስማማ ባለይዞታ እንደ ፌደራል ሰበር.በመዝገብ.ቁጥር 30101.ቅፅ 6 እና በመዝገብ.ቁጥር.105125.ቅፅ 20 በተወሰነው ውሳኔ መሰረት ቤቱን የሰራው ሰው ባለቤት ይሆናል። የመሬቱ ባለይዞታም በእንዲ አይነት ሁኔታ ቤቱን ለሰራው ሰው የቤቱን ግምት ከፍዬ ላስለቅቅ ማለት አይችልም።

የፍ/ህ/ቁ.1179ን አስመልክቶ ሰበር በቅፅ 25 የመ/ቁ. 189608 የሰጠው ትርጉም
***
በፍ/ህ/ቁ. 1179 ላይ የተመለከተዉ ድንጋጌ ተፈፃሚነት የሚኖረዉ በባለይዞታዉ እና ይዞታዉን ይዞ ቤት በሰራ ሰዉ መካከል የታወቀ ግንኙነት በሌለበት ሁኔታ ብቻ በመሆኑ የባድ ቦታ ሽያጭ ዉል መፍረሰን ተከትሎ በቦታዉ ላይ የተሰራ ቤት ህጋዊ ዉጤትን አስመልክቶ ለጉዳዩ ተፈፃሚነት ያለዉ በፍ/ህ/ቁ. 1818 ነዉ።

ሳሙኤል ግርማ
የሕግ አማካሪና ጠበቃ
0911 190 299


https://t.me/ethioengineers1