Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ አበባ ለህንጻ ግንባታ በተቆፈረና ውሃ ባቆረ ጉድጓድ ዉስጥ ዋና ለመዋኘት የገባ የ27 ዓመ | Ethio Construction

አዲስ አበባ

ለህንጻ ግንባታ በተቆፈረና ውሃ ባቆረ ጉድጓድ ዉስጥ ዋና ለመዋኘት የገባ የ27 ዓመት ወጣት ህይወቱ ማለፉን የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቃል።

የወጣቱን አስከሬን የኮሚሽኑ ዋናተኞች ከአንድ ሰዓት ፍለጋ በኃላ ማግኘታቸውን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ በተለይ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

አደጋው ዛሬ ዓርብ  ከቀኑ 8 ሰዓት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታዉ ሚሊኒየም አዳራሽ ጀርባ ለህንጻ ግንባታ በሚል በተቆፈረና ዉሀ ባቆረ ጉድጓድ ዉስጥ ደርሷል።

በአዲስ አበባ ተቆፍረዉ ክፍቱን በሚተዉ ጉድጓዶች ዉስጥ ዋና ለመዋኘትና በሌሎች ምክንያቶች በ2015 ዓ.ም ብቻ የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል።(ብስራት ሬዲዬ)


https://t.me/ethioengineers1