Get Mystery Box with random crypto!

#በመላው_ዓለም_የምትገኙ_ውድ_አድማጮቻችን... በውሃልክ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን እየተዘጋጀ በኢ | Ethio Construction

#በመላው_ዓለም_የምትገኙ_ውድ_አድማጮቻችን...

በውሃልክ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን እየተዘጋጀ በኢትዮጵያውያን ቤተ-ሬዲዮ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የዓየር ሞገድ ላይ በዛሬው ዕለተ ቅዳሜ ሚያዝያ 29/14 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 እስከ 3 ሰዓት በተደመጠው ውሃልክ የኮንስትራክሽን ፕሮግራማችሁ….

በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ላለፉት ሁለት ዓመታት የኮቪድ ወረርሽኝ እና የሎክዳውኑ ተፅእኖ እንዲሁም ከፀጥታ ጋር በተያያዙ ችግሮች መነሻነት በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው ላይ የተፈጠረው ተፅእኖ ቀላል እንዳልነበር ይታወቃል።

ይኸው ዓለም ዓቀፍ ችግር በአገራችን የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ላይ የሚኖረው ተፅእኖ እስከምን ድረስ ነው?፤ መሠል ሁኔታዎች ሲያጋጥሙስ በተቋራጮች በኩል የኮንትራት ውል የማቋረጥ፣ የማራዘም ብሎም የካሳ ጥያቄዎች ወዘተ ፍላጎት ቢኖር ሕግን የተከተሉ የማሻሺያ ርምጃዎች ሊኖሩ ይችሉ ይሆን? እየተባባልን ከእንግዳችን አቶ ጀማል አሊ ጋር እንደተለመደው በልክ እና በቁም-ነገር ተጨዋውተናል።

በመሆኑም በተለያዩ ግለ ምክንያቶቻችሁ የዛሬው ፕሮግራም ያመለጣችሁ አድማጮች የዝግጅቱን ፍሬ-ነገር ዳግም ታደምጡልን ዘንድ ስንጋበዛችሁ፤ አንደሁልጊዜው ሁሉ ደስ እያለን ነው።

#የውሃልክ_ሕንፀት በውሃልክ_መሠረት!
#ሕይወትን በኮንስትራክሽን እንገንባ!
#ውሃልክ_ሚዲያ_እና_ኮሚዩኒኬሽን።