Get Mystery Box with random crypto!

ስለ ሐመር ቴስት #ሐመር ቴስት/Hammer test/ አፍራሽ ያልሆነ (Non destructive) | Ethio Construction

ስለ ሐመር ቴስት

#ሐመር ቴስት/Hammer test
/ አፍራሽ ያልሆነ (Non destructive) የአርማታ ጥንካሬ ደረጃ ማወቂያ ፍተሻ ሲሆን ትክክለኛ እና ፈጣን መመርመሪያ ዘዴ ነው።
.
ሐመር ቴስት የሚከናወንበት መንገድ ስፕሪንግ መቆጣጠርያ
ያለውን ክብደት መለኪያ መሳርያ ከላይ በምስል እንደሚታየው
የአርማታውን ገፅ ተጭኖ በመያዝ መልሶ የሚመታበትን አሀዝ
ልኬት መዝግቦ በመያዝ ይሆናል።
.
የሐመር ቴስት አላማውም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያካትታል፤
1. የአርማታ የመታመቅ አቅም/compressive strength/
ለማወቅ።
2. የአርማታውን አንድ አይነትነት ወይም ወጥነት ለመገምገም።
3. የአርማታውን ክብደት የመሸከም አቅምን ከተወሰነለት ዲዛይን አንፃር ትክክል መሆኑን ለማረጋገጥ።
.
የሐመር ቴስት ከማሰራት በፊት ሊደረግ የሚገባ ቅድመ
ሁኔታዎች፤
1) የአርማተዉ ገፅ የለሰለሰ፣ንፁህ እና ደረቅ መሆን ይጠበቅበታል
2) ናሙና የሚወሰደው ቦታ ቢያንስ 20ሚሊ ሜትር ከጠርዝ ሊርቅ ይገበዋል።
3) ስድሰት (6) ንባብ ከእያንዳንዱ የአርማታ አካል ይወሰዳል፤
አማካይ ስሌት ተሰርቶ ጥንካሬ መለኪያ ይደረጋል።
4) አርባ አምስት(45) ቀን የሞለው አርማታ መሆን ይጠበቅበታል።

@ethioengineers1