Get Mystery Box with random crypto!

የግንባታ ዕቃዎች ዋጋ ንረት በግንባታ ዕቃዎች ላይ የታየው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በኮንትራት በተቀ | Ethio Construction

የግንባታ ዕቃዎች ዋጋ ንረት

በግንባታ ዕቃዎች ላይ የታየው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በኮንትራት በተቀበላቸው ፕሮጀክቶች ከመፈተኑም በተጨማሪ በቀጣይ ለሚረከባቸው ፕሮጀክቶችም ምን ማድረግ እንዳለበት እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን አስታውቋል።

ኮርፖሬሽኑ የግንባታ ዕቃዎች ዋጋ ከሁለት እስከ ሦስት እጥፍ መጨመራቸው ለኮንትራክተሮች ትልቅ ፈተና መሆኑን እና ከዚህ በኋላ ወደ ኮርፖሬሽኑ የሚመጡ ኮንትራቶች ላይ ትኩረት አድርጎ እይሠራ መሆኑን ገልጿል።

ለጊዜው ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች በግብዓት እጥረት እና በዋጋ መወደድ ምክንያት ከገበያ ውጪ መሆናቸው እየተነገረ ይገኛል።

ኮርፖሬሽኑ የገበያ ዋጋ የማይረጋጋ ከሆነ ችግር ውስጥ የሚገባ መሆኑን የገለፀ ሲሆ ከዚህ በኋላ የሚመጡ ኮንትራቶችን አሁን ባለው ዋጋ መቀበል እንደማይችል አስታውቋል፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት 37.1 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ 49 ፕሮጀክቶችን ቀደም ሲል ባስገባቸው ግብዓቶችና በአገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶችን በመጠቀም ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

በአገር ውስጥ የሚተኩ ምርቶችን አሁን ካለው የምርት መጠን  በላይ ጨምሮ  ለማምረት እየሠራ መሆኑንም ኮርፖሬሽኑ ማስታወቁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።
Via: tikvahethiopia

https://t.me/ethioengineers1