Get Mystery Box with random crypto!

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዛሬ ሴናተር ክሪስ ኩንስን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚልኩ ፎሬን ፖሊሲ | HabeshaNet.

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዛሬ ሴናተር ክሪስ ኩንስን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚልኩ ፎሬን ፖሊሲ መጽሄት ዘግቧል፡፡ መልዕክተኛው የተላኩት ስለ ትግራዩ ግጭት ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ እና ከአፍሪካ ኅብረት ሃላፊዎች ጋር ለመነጋገር እና ፕሬዝዳንቱ ስለ ትግራዩ ግጭት የገባቸውን ስጋት ለማስረዳት እና መፍትሄ እንዲፈለግ ለመገፋፋት እንደሆነ ኩንስ ለመጽሄቱ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር የገባችበትን የድንበር ውዝግብ እንድትፈታም የመገፋፋት ተልዕኮ አላቸው ተብሏል፡፡ ኩንስ በአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ አባል እና የውጭ ዕርዳታን የሚቆጣጠረው ኮሚቴ ሰብሳቢ ናቸው፡፡

[Wazema]


@ethiocoronainfo