Get Mystery Box with random crypto!

ከመስከረም 14 እስከ ጥቅምት 13 ለተወለዱ በሙሉ ዞዳይካቹ ሊብራ ይባላል ትሁት እና ጨዋ አለመሆ | ኢትዮ ASTROLOGY

ከመስከረም 14 እስከ ጥቅምት 13 ለተወለዱ በሙሉ

ዞዳይካቹ ሊብራ ይባላል ትሁት እና ጨዋ አለመሆንን ከልባቸው ይጠሉታል አፍቅሬሰብ ቢሆኑም ታላቅ ጉባኤ የመፍራት አባዜ አለባቸው።

»» ሊብራዎች በተፍጠሯቸው የዋህ ሆነው የደስደስ ያላቸው ናቸው ፣ እንዲያም ሆኖ ግን አኩራፊነት እና እንቢተኝነትም የተፈጥሯቸው አንዱ አካል ነው።

»» የሊብራ ኮኮብ በወርቃማ የፍትሕ ሚዛን ትእምርት ይመሰላል፣ የሊብራም ባህሪ ልክ እንደ ሚዛን ነው አንዴ ይወርዳል አንዴ ይወጣል፣ የተመጣጠነ ሚሆነው አልፎ አልፎ ነው፣ የሊብረም ኑሮ ከፍ እና ዝቅ ነው።

»» እንደ ስብናቸው ሁሉ ፣የሊብራዎች መልክና ቁመና በቀላሉ ሊገለፅ የሚችል አይደለም፣ ሆኖም ብዙ ግዜ ፈገግ ሲሉ የሚገለጥ ስርጉድ ይታያል፣ በአገጫቸውም ላይም እንደዛው ፣ በፊታቸው ላይ እንኳን ከጠፋ ከእግራቸው ከሎሚው አጠገብ ዲምፕል አይጠፋም።

»» ሊብራዎች በድምፃቸው ቅላፄም ይላያሉ ድምፀ መረዋ ናቸው፣ ድምፃቸው ኩልል ያለ ነው

»» ሴቶቹ ሊብራዋች ውቦች ናቸው የደስ ደስ አላቸው ። ሊብራዎች ማራኪ ናቸው ፣ ተፍጥሯቸው አመዛዛኝ እና ፍታዊ ነው፣ ቢሆንም ግን ባህሪያቸው ወጥ አይደለም።

»» ሊብራዋች ክርክር ውስጣቸው ነው፣ ክርክር ይሁን እንጂ ከየትም ሆነው ይከራከራሉ።

»» የሆነ ግዜ ላይ በጣም ይሰሩ ይሰሩና ከሆነ ግዜ ቧላ ደግሞ ደክም ብሏቸው ከመሬትም የተሰበረ ብርጭቆ አያነሱም።

»» የአምሯውን የስሜት ሚዛን በመጠበቅ ረገድ ግን ሊብራዎች ደከም ይላሉ ፣ ሀዛን ይሰብራችዋል፣ ጤናቸው እስኪናጋ ድረስ በእንባ ይታጠባሉ።

»» የአምሯቸውን አና የአካላቸውን ጤና የሚጠብቁበት ብርቱ ደመነፍስ አላቸው ።

»» እነሱ ሚጠሉት ፍርድ ገምድልነት ፣ ኢፍታዊነትና ጭፍን እምነትን ነው።

»» ከውሳኔ ላይ ፈጥኖ ያለመድረስ ችግር ከሊብራዎች ላይ ባስ ሲል ይታያል፣ መዋከብ እና መቻኮልን አምርረው ይጠላሉ።

»» የሊብራ ልብ በፀዳና ባማረ ነገር ሁሉ ሃሴትን ታደርጋላች፣ የሊብራ ነፍስ አርቲስት ነች።

»» ሊብራ ሚለው ቃል መመጣጠንን፣ አቻ፣ እኩል መሆንን ያመለክታል። በተለይ ደግሞ ሚዛን የተሰኘው የአመርኛ ስያሜ ማመዛዘንን እና ማመጣጠንን የበለጠ ይግልፀዋል።

»» ታፍነው ፣ ተሸፍነውና ተዳፍነው ለመቆየት አይቻላቸውም።

»» የሊብራዎች ተፈጥሮ ቀለል ያለ እና ያልተወሳሰበ ነው። አመላቸው አይጎረብጥም፣ ዘና ያሉ ናቸው።
»» ጓደኝነትን ለመመስረት ይፈጥናሉ፣ በችኮላቸውም ሳቢያ በመጃመሪያ ሙከራቸው ላይ የሚገጥማቸው ሁነኛ ሰው አይደለም፣ ጋብቻም ላይ እንደዛው።

»» ሊብራዎች ሆደ ሰፊ ናቸው ፣ የሀይማኖት፣ የፖሎቲካና የአመላካካት ልዩነትን ያከብራሉ፣ በልዩነት ውስጥ ውበትና አንድነትን ማለምን ይችላሉ፣ ሊብራ የእኩልነትና ፍትህ ኮኮብ ነው።

Share Share

@ethiokokeb @ethiokokeb
@ethiokokeb @ethiokokeb