Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ ASTROLOGY

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioastrology1 — ኢትዮ ASTROLOGY
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioastrology1 — ኢትዮ ASTROLOGY
የሰርጥ አድራሻ: @ethioastrology1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.27K
የሰርጥ መግለጫ

<<ሰለ ኮከቦ ይወቁ>>
የተወለዳቹበት ወር ሰለናት እንደሚናገር ያውቃሉ?
Le cross ena ማስታወቂያ 👉 @unverseand

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-02-19 13:13:45 ኮከቦችና ወሲባዊ ግፊት ከ12 እስከ 1; በቅደም ተከተል

አሊስ ሞራሌ የተባለች የአስትሮኖሚ ባለሙያ የወሲባዊ ፍላጎትና መነቃቃት መነሻ በማድረግ 12ቱን ኮከቦች በደረጃ አስቀምጣለች። በጽሁፏም ከዋክብት ሊቢዶ የተሰኘው ሆርሞን ላይ ተጽዕኖን እንደሚያሳድሩ አስቀምጣለች።

በዚሁ ጽሁፏ ሁሉም ኮከቦች (የሰው ልጆች) ለወሲብን ፍላጎትና ግፊት እንደሚኖራቸው አስቀምጣ አንዳንዶች ለወሲብ ያላቸው መነሳሳትና ግፊት (sex driven) ከፍ ያለ ሲሆን የአንዳንድ ኮከቦች መነቃቃት ደግሞ ሌሎች መሠረታዊ ፍላጎቶታቻቸው ሲሟሉ እንደሚመነጭ አስቀምጣለች።

እንግዲህ ለደረጃ አሰጣጡም መሰረታዊ መነሻ ይህ መሆኑ ነው። እኛም እንግዲህ በርሷ ትንተና ተመስርተን ከመጨረሻው በመጀመር እንቃኛለን።

12ኛ ሊብራ

ለሊብራዎች በዚህ ደረጃ መቀመጥ ወሲብን ከመጥላታቸው የመነጨ አይደለም። ምክንያቱ የተለያየ መልክ ያለው ጥልቅ ግንኙነትን ከመሻታቸው እንጂ። እንደ ጓደኛ፣ ቤተሰብ ወዘተ. ለሊብራዎች ወሲብ ተግባራዊነት የሚኖረው ፍቅርንና ቃል መግባትን ተከትሎ ነው። ከዚህ አንጻር ሁልጊዜም ወይም በድንገት ወሲብ የመፈጸም ሁኔታቸው ከሌሎች ኮከቦች በተነጻጻሪ ዝቅ ያለ ነው።

11ኛ አኳሪየስ

የአኳሪየሶች የበዛው ፍላጎት ነጻነት ነው። ከዚህ አንጻር ወሲባዊ መስተጋብራቸው በጥቂቱ እንኳን ከዚህ በተቃራኒ የሚቆም መስሎ ከተሰማቸው ምርጫቸው ፊታቸውን ማዞር ነው። ይህ መለያው አየር የሆነ ኮከብ (አኳሪየሶች) ለወሲብ ብቻ ሲሆን ጭንቅላታቸውን በደመና ውስጥ የሚቀብሩ አይነት ሲሆን የግንኙነቱም መሠረት ወሲባዊ መስተጋብር ብቻ ከሆነ ለመጨበጥ የሚከብዱ አይነት ናቸው።

10ኛ ቪርጎ

በርግጥ ቪርጎዎች በመኝታ ላይ ደፋሮች (adventuries) ናቸው። ራሳቸውን ለቀቅ አድርገው የሚገልጡበትም ቦታ ነው። ችግሩ እነርሱን ወደዚያ ከማድረስ ላይ ነው። ቪርጎዎች አዕምሯቸውን ነጻ የሚያደርግላቸውና ውስጣቸውን እንደፈለጉ እንዲገልጡ የሚያደርጋቸው ወዳጅ ቀዳሚው ጥያቄና መሠረት ነው።

በቀደመው ክፍል አስትሮሎጂስቷ አሊስ ሞራሌ ሁሉም ኮከቦች (የሰው ልጆች) ለወሲብን ፍላጎትና ግፊት እንደሚኖራቸው አስቀምጣ ኮከቦች ግን ሊቢዶ በተሰኘውን ወሲባዊ መነቃቃትን የሚወስን ተፈጥሮ ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩበት መግለጿን አስቀምጠን ነበር።

በዚህ መነሻት አንዳንዶች ለወሲብ ያላቸው መነሳሳትና ግፊት (sex driven) ከፍ ያለ ሲሆን የአንዳንድ ኮከቦች መነቃቃት ደግሞ ሌሎች መሠረታዊ ፍላጎቶታቻቸው ሲሟሉ እንደሚመነጭ ማስቀመጧን ጠቅሰን ከዚህ አንጻር ከ 12-10 ያለውን ደረጃ የያዙ ኮከቦች አስቀምጠን ነበር ያበቃነው። የዛሬው ተከታይ እነሆ!

9ኛ ጀሚኒ

ጀሚኒዎች ፈጥነው የወሲባዊ መጋጋል ውስጥ የማይገቡ ናቸው። ንግግር፣ ሳቅና ጨዋታ እና የአዕምሮ መጣጣም ስሜታቸው እንዲነቃቃ አስፈላጊ ናቸው። በሂደቱ የሚፈጠር ትንሽ ስህተት ስሜታቸውን ሊያቀዘቅዘው ይችላል።

8ኛ ካፕሪኮርን

ካፕሪኮርኖች ከረር ያሉና ወግ አጥባቂ መሆናቸው አንዱ መታወቂያቸው ነው። በርግጥ ይህ ሁኔታቸው በመኝታ ክፍል ሲሆን ቀነስ ብሎ ይስተዋላል። ነገር ካፕሪኮርኖች ከወሲባዊ ግንኙነት በላይ ራሳቸውን በስራ መወጠርና መቅበር ደስተኛ ሆነው እንዲቆዩ የሚያደርጋቸው ነው።

7ኛ ካንሰር

ካንሰሮች የፍቅር/ወሲብ አጋራቸው ትርጉም የሚሰጡትና የሚንከባከባቸው እንዲሆን ይሻሉ። ከወሲብ እውነተኛውን ደስታ ለማግኘት መተማመን (trust) መሠረታዊው ጉዳይ እንደሆነ ያስባሉ። ይህ ደግሞ ጊዜ ሊወስድ ቢችልም ካንሰሮች ለመጠበቅ ያላቸው ትዕግስት ከፍላጎት በላይ ነው።

6ኛ ፓይሲስ

ፓይሲሶች በርግጥ በወሲብ ይዝናናሉ፤ ፍላጎታቸውም ጥሩ ነው። ነገር ግን የስሜት ግንኙነትና ቅርበት ከወዳጃቸው ጋር እንዲኖር ይሻሉ። ይህን ካገኙ የፍላጎታቸው ገደብ አበላያቸው ያለው የቤቱ ጣሪያ ይሆናል። ይህ ቅርርብ ከሌለ ደግሞ ስሜታቸው በአንታርክቲካ እንደሚገኝ በረዶ ይሆናል።

5ኛ ሊዮ

የሊዮዎች የወሲብ መነቃቃትና ፍላጎት በፍቅር/ወሲብ አጋራቸው ላይ የተመሠረተ ይሆናል። እንደሚያስቡት የጫካው ንጉስ አድርገው የሚቀበሏቸውና ታላቅነታቸውን ያለማወላወል የሚመሰክሩ ሲሆኑ ሊቢዶ የተሰኘውና የወሲብ መነቃቃት ደረጃን የሚወስነው ሆርሞን እንደ እሳት መንቀልቀል ይጀምራል። ያን መሠል የስሜት ግንኙነት ከሌለ ደግሞ ፑፍ...ስሜታቸው ከምትገምቱት ፍጥነት በላይ ስሜታቸው ይቀዘቅዛል።

4ኛ ሳጁታሪየስ

ሳጁታሪየሶች በአየር የሚወከሉ እንደመሆናቸው ፍላጎታቸው መልከ ብዙ ነው። ከሌሎች ኮከቦች በላቀ በመኝታ ክፍል ያልተለመዱ ነገሮችን የሚከውኑ ናቸው። ቃል መግባትና ቁርጠኝነትም አንዳንድ ጊዜ ሊስተዋልባቸው የሚችል ነው። በህይውታቸው የተለያየ ነገርን እንደመፈለጋቸው ጊዜያዊ የወሲብ ግንኙነትን መፍቀድ በጠረጴዛው ከተቀመጡ አማራጭች ውጪ ላያደርጉ የሚችሉበት እድል ሰፊ ነው።

3ኛ ኤሪስ

የኤሪሶች ገዢ ፕላኔት ማርስ ናት። ማርስ ተጽዕኖ ከምታሳድርባቸው ጉዳዮች አንዱ ደግሞ ወሲብን ነው። ከዚህ አንጻር ሂሳቡን እናንተ አስሉት። 1+1=2 ማለት አይቸግራችሁምና። ኤሪሶች ማማመለልኑም ሆነ በወሲብ አጋራቸውን መሪ ሆነው መጋራቱን እኩል ሊባል በሚችል ደረጃ የሚዝናኑበት ነው። Almost!

2ኛ ታውረስ

ስሜትን መረዳትና ማጣጣም የሚችሉበት ታውረሶች ሁሉንም አይነት ሊባል በሚችል ደረጃ አካላዊ መነካካቱንና ደስታን ማግኘቱን ይወዱታል። ከዚህ አንጻር ከዝርዝሩ ቀዳሚዎቹ ተርታ መሠለፋቸው የሚገርም አይሆንም። ይህንን ካሳኩም በኋላ ቀሪ ስራዎቻቸውን በተሻለ ደረጃ የመፈጸም አቅማቸው ከፍ የሚል ነው፤ ጥሩ ስሜትም ይኖራቸዋል።

1ኛ ስኮርፒዮ

መቼም እስከ ዘጠኝ ያሉትን ደረጃዎች የሳተ ቢኖር እንኳን በዝርዝሩ ቀዳሚ የሚሆነውን መሳት የሚቻለው አይመስለኝም። አዎ! ስኮርፒዮ ነው! ግምታችሁ ትክክል ነው ። ስኮርፒዮዎች ከፍ ባለ የወሲብ ፍላጎታቸው ይታወቃሉ። ይህም በቅርበትና በመሞከር ፍላጎታቸው የሚወረስ ነው።

ብዙ የወሲብ አጋሮችን የሚፈልጉ ሆነው ግን አይደለም፤ እንዲያውም ምርጫቸው የተጠና ነው። (they are selective) ምክንያቱ ደግሞ ድብቅ ባህሪዎቻቸውን እንዲያውቁ የሚፈቅዱላቸው ሰዎች ጥቂት ከመሆናቸው የመነጨ ነው።


ምንጭ ኮኮቦች ስለ እኛ

Share Share

@ethiokokeb @ethiokokeb
@ethiokokeb @ethiokokeb
200 viewsedited  10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 09:36:26 የተወለዳቹበት ወር ስለ እናንተ ምን ይናገራል?

መስከረም፡

ጠንቃቃ፣ንቁ፣አስተዋይ፣ብዙ እውቀት ያላቸው፣ጥሩ የማስታወስ ችሎታ ያላቸው ናቸው።

ጥቅምት፡

ከፍተኛ የማውራት ችሎታ ያላቸው፣በብዙ ጉዳዮች ውስጥ እራሳቸውን እንደ ባለቤት መጨመር ይወዳሉ፣ከሚወዷቸው ሰዎች ጋር ብቻ መሆንን ይመርጣሉ፣

ህዳር፡

አስገራሚ የማሰብ ችሎታ አላቸው፣ትዕግስተኛ፣አስተዋይ ናቸው።

ታህሳስ፡

ታማኝ፣ቸር፣ለጉርብትና እና ለማህበራዊ ህይወት ከፍተኛ ትርጉም ይሰጣሉ፣

ጥር፡

አስቸጋሪ፣ትልቅ ህልም ያላቸው፣ትጉህ ሰራተኞች፣ግለኝነት እና ዝምታ ያበዛሉ፣

የካቲት፡

ነፃነታቸውን በጣም የሚወዱ፣ታማኝ፣ጎበዝ፣እውነተኛ ናቸው።

መጋቢት፡

አይንአፋር፣ግለኛ፣ሁሉን ነገር ሚስጢር ማድረግ የሚወዱ፣ታማኝ ጓደኞች ናቸው።

ሚያዚያ፡

ፈጣን፣ንቁ፣ጠንካራ የአስተሳሰብ ችሎታ እና የመወሰን ብቃት አላቸው፣ደፋር፣

ግንቦት፡

ጠንካራ ሰራተኛ፣ረዥም ህልም ያላቸው፣በራስ ተነሳሽነት ያላቸው፣ቁጡ፣ኩርፍተኛ፣

ሰኔ፡

ትሁት፣ለስላሳ፣ስሜታዊ፣ንቁ፣ቀልድ እና ክርክር የሚወዱ፣በቶሎ የማይወስኑ፣

ሐምሌ፡

ለመረዳት እጅግ አስቸጋሪዎች፣ተጫዋች እና እውነተኛ በህርይ ቢኖራቸውም ዝም ያለ እና የማይታወቅ ጎንም አላቸው።

ነሐሴ፡

እጅግ ደፋር፣ለየት ያለ በህርይ ስላላቸው ቡዙ ሰዎች እንደ ሞዴል ይከተሏቸዋል፣ቁጡ፣

Share Share

@ethiokokeb @ethiokokeb
@ethiokokeb @ethiokokeb
284 viewsedited  06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 09:34:42
ሊብራ የጄሚኒ ትክክለኛ ውሀ አጣጭ ናት ይባላል።

አዎ እውነት ነው ግን የሚያሳዝነው ሊብራ እና ጄሚኒ የሚገጣጠሙበት እድል ያነሰ መሆኑ ነው ሊብራ ሌላ ኮኮብ እያባረረ ውሀ አጣጫ ማን ይሆን እጀያለ ይብሰከሰካልጄሚኒውም እንደዛ ሲንግል የሆናችሁ ባለ ሁለቱ ኮከቦች እስቲ ጥምረት ትፈጥሩ ዘንድ በ ኮሜንት ሊብራ የሆናችሁ ሊብራ ጄሚኒ የሆናችሁ ጄሚኒ በሉና እርስ በርስ ተያያዙ የማይሰበር ጥምረት ፍጠሩ

Share Share

@ethiokokeb @ethiokokeb
@ethiokokeb @ethiokokeb
226 viewsedited  06:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 11:02:16 በአለም ላይ ያሉ ታዋቂ የካንሰር ኮኮብ ያላቸው

። ሃይለማርያም ደሳለኝ HD
። ሃይለመለኮት መዋእለ ደራሲ
። ሊዮኔል መሲ ኳስ ተጫዋች
። መረራ ጉዲና ፖሎቲሺያን
። ታይሰን ቦክሰኛ
። አል አሙዲን ቢሊየነር
። ቀነኒሳ በቀለ አትሌት
። በእውቀቱ ስዩም ደራሲ
። ታደለ ገመቹ ሙዚቀኛ
። ቴድሮስ ታደሰ ሙዚቀኛ
። ቴዲ አፍሮ ሙዚቀኛ
። ኔልሰን ማንዴላ ፕሬስዳንት
። አብዱ ኪያር ሙዚቀኛ
። አደነ ግርማ ኳስ ተጫዋች
። አፄ ዮሃንስ 4 ንጉስ
። ኤድዋርድ ስኖደን ሃከር
። እርነስት ሄሚንግዌይ ደራሲ
። ኩኩ ሰብስቤ ሙዚቀኛ
። ዚነዲን ዚዳን አሰልጣኝ
። ደረጄ ሃይሌ ኮሜዲያን
.
.
.
For all cancer proud to be yourself

Share Share

@ethiokokeb @ethiokokeb
@ethiokokeb @ethiokokeb
314 viewsedited  08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 11:01:09 ከጥር 13 እስከ የካቲት 12 ለተወለዳቹ በሙሉ።

»» ዞዳይካቹ ወይም ኮኮባቹ አኳሪየስ ይባላል

»» አኳሪየስ ኮኮብ ያለው ሰው እውቀትን በማንበብ፣ በመመርመር፣ በመስማት አንድአንዴም ከየት እንደሚያውቀው ለመገመት በሚያስቸግር መልኩ የሰበሰበውን እውቀትና ጥበብ ወደ ሰው ልጆች ይረጫል።

»» የአኳሪየስ ኮኮብ ያለው ሰው ዕውቀቱን ሲዘራ በሰው ልጆች መካከል ልዪነት አያደረግም፣ በአርሶ አደሮች ጉባዬ ላይ ስለ አስትሮፊዚክስና ስለ ማይክሮባዮሎጂ ሊናገር ይችላል፣ በገዳም ለተሰበሰቡ መነኮሳት ስለ ዳርዊን የዝግመተ ለውጥ ትወራ ማብራርያ ሲሰጥ አያስገርምም።

»» አኳሪየስ ስለመጭው ዘመን አስቀድሞ ያያል፣ የአዲስ ዘመንን ንጋት ያበስራል፣ ከጊዜው ቀድሞ የሚፈጠርና ኑሮውንም በመጭው ዘመን ውስጥ የሚየደርግ ፍጡር ነው፣ በዚህም ምክንያት በሌሎች ዘንድ እንደ ተራ ሊታይ ይችላል።

»» አኳሪያሶች ያልተጠበቀ ነገርን ሁሌም ያደርጋሉ፣ አካሄዳቸውን መገመት ያስቸግራል፣ የብዙሃኑን አመለካከትና እምነትን ፉርሽ ማድረግን ይደሰቱበታል፣ በልተጠበቀ ድርጊታቸውና ንግግራቸውም ወግ አጥባቂ ሰዎችን ማስደንገጥ ይወዳሉ።

»» አለባበሳቸው ወቅቱን ይጠብቅ አይጠብቅ ልብ አይሉትም፣ ሲፈልጋቸው በባዶ እግራቸው ከአደባባይ ይወጣሉ፣ የሳቀባቸውን መልሰው ይስቁበታል፣ ነገረ ስራቸው ሌላው ሰው ከሚያስብውና ከሚያደርገው የተገላቢጦሽ ነው።

»» በሌላ በኩል ደግና ቸር ናቸው፣ የተቸገረን በመርዳት አቻ የላቸውም፣ የበጎ አድራጎት ድርጅትን በገንዘብ ይደግፋሉ፣ ስለብዙሃኑ ይጨነቃሉ፣ የህዝብን ኑሮ የሚያቀሉ ፈጠራዎችንና ሐሳቦችን ያመነጫሉ

»» ሌላው መገለጫቸው ደግሞ ጓደኛ ፣ ወዳጅ ወይም ባልንጀረ የሚለው ቃል ነው ፣ ጓደኝነትን ከብዙ ነገር በላይ አክብረውት ይታያሉ፣ የቅርብና የነፍስ ጓደኛ የሚሉት ባይኖራቸውም የሰውን ልጅ በሞላ እንደ ጓደኛቸው ያዩታል፣ አለማቀፋዊ ጓደኝነትን እና ወንድማማችነትንም አጥበቀው ይሰብካሉ፣ ጓደኛ የሚለውን ቃል ደጋግመው ስለሚጠቀሙም በዚ ይታወቃሉ።

»» አኳሪየስ የለየለት መርማሪ ነው ፣ ሰውን መኪናን፣ ራዲዮን ዕፅዋትን ሁሉን ይመረምራል፣ ይፈትሻል አንዱን ሲጨርስ ወደ ሌለው ይሄዳል ፣ ቀጣዩም ተመርማሪ እርሶ ሊሆኑ ይችላሉ፣ አምዕሮ በብዙ ኪሎሜትሮች መጥቆ እና ጠልቆ የሚሄድ ነው ፣ በስውር ማይክሮስኮፕ ሰዎችን አየቆራረጠ የሚመረምር ነው ሚመስለው፣ ምንም እስከማይቀረው ድረስ ብትንትን አድርጎ ያቆታል፣ እርሱ ግን አይታወቅም፣ ትንግርት ነው፣ ምርመራውን ሲጨርስ ጥሎት ይሄዳል፣ የዚህ ሁሉ ሰበብ ጉጉ መሆኑ ነው።

»» አይኖቻቸው ሩቅ ተመልካች ነው፣ የሚያልሙና ትንግርትን ያዘሉ ነው ሚመስሉት ፣ ታድያ የአኳሪያስ አቀራረብ ቀዝቀዝ ያለ ነው፣ እርጋታውም ያስገርማል፣ ለኑሮ ያዎቅበታል የነገን ቢያልምም የዛሬን በወጉ ይኖራል፣ ገንዘቡን በጥንቃቄ ይይዛል።

»» የአኳሪየስ ቁመና ልዕልናን የተጎናፀፈ ነው ፣ ገፅታቸው እንደ ሳንቲም ላይ ምስል ቁርጥ ያለና ጠርዝ አለው፣ ሲናገሩ ጭንቅላተቸውን ወደታች ወይም ወደ ጎን ዘንበል የማድረግ ልማድ አለቸው፣ ለብቻቸውም ፈገግ እያሉ ሊሆን ይችላል።

»» ለራሱ የሆነ ግዜ ሁሌም ያስፈልገዋል፣ ብቸኝነቱንም ይናፍቃዋል

»» ከሌሎች ኮኮቦች የበለጠ አእምሮ ጥልቅ እና ምጡቅ ነው ከእርሶ ጋ እያወራ ከጎን ሚደረገውን ከነ ሁኔታው ይራዳል።

»» አኳሪየሶች የወግ፣ የልማድና የባህል ፀር ናቸው። እንዲሁም ልዩ የመነጠል አባዜ አለባቸው ፣ ሰዎችም በአግባቡ አይረዱትም፣ የነሱ ኑሮ በነገ እና በተነገ ወዲያ ነው ፣ ዘሬን ብቅ የሚለው አልፎ አልፎ ነው ፣ስለዚህም ለተራው ሰው ግራ ፍጥረት ሆኖ ይታያል፣ እሱም ይህን ያይና መነጠሉን ያበዛዋል፣ እኛ ተራዎቹ ደግሞ ምን እያደረገ ነው ብለን እንገረማለን።

አስትሮሎጂ " አኳሪየስ ዛሬ የሚያስበውን ቀሪው አለም ከ50 አመት በኅላ ያስበዋል " ይለናል።
»» አኳሪየሶች የጂኒየስነት ምልክት ነቸው፣ ከስመጥር ሰዎች 70% የሚሆኑት እነሱ ናቸው።

»» የአእምሮ መረበሽ ለደረሰባቸው አዘኔታን ያሳያሉ፣ ትከሻቸውም ይነገራችዋል፣ እነሱን በማናገር ብቻ ያረጋጉታል፣ ለራሳቸው ግን የማይረጋጉበት ጊዜ ይበዛል።

»» አመለካከታቸው ሰፊ ነው ፣ ፍርድ ገምድልነት የለባቸውም፣ ሁሉም ሰው ወይ እህቱ ወይ ደግሞ ወንድሙ ነው፣ በነዳያንና በሀብታሞች መንደር ይዞራሉ።

»» ብቸኝነቱን አይገዳደሩበት ፣ ብቻውን መሆን ይፈልጋል፣ አንድአንዴ ቁዘማ ውስጥ ይጠፋል ብዙ ግን አይቆይም ወዲያዎ ይወጣል።

»» ቁርጥ ባለ ጌዜና ተግባር ውስጥ መታሰርን ይፈራሉ ሆኖም አንዴ ልበቸውን ከገኟቸው በተባለው ቦታ ይገኛሉ፣ አንዴ ከመኖት አመኖት ነው ማንም ምንም ቢል ይሰማ ይሆናል እንጂ አያምንም፣ እስኪያምኖት ግን ግዜ ይፈልጋል።

»» የአኳሪየሶች ፍልስፍና ሁሉም እንደፍጥርጥሩ ይኑር ነው፣ ግለሰባዊነት በሱ ዘንድ መከበር አለበት።

»» አኳሪየሶች በቂ እንቅልፍና ንፁ አየር ማግኘት አለባቸው።
»» ልቦናው በጣም ስሱ ነው ፣ የውሸት እና የማጭበርበር ቀንደኛ ጠላቶችም ናቸው።

»» አኳሪየሶች በሚያስቡት ነገር ውስጥ የነገ ፍንጭ አለበት፣ ወዳልታሰበው አለም ተጉዘው ትንግርታዊ ምስጢሮችን ይቀስማሉ፣ ይህም ኢንቲዪሽን እና ሳይኪክነትን ያላብሳችዋል፣ለምሳሌ አብርሃም ሊንከን ስለሞቱ ከነአስገራሚ ዝርዝሩ አስቀድሞ አውቆ እንደነበር በታሪክ ተመዝግቧል።

»» አኳሪየስ ማበደርንም ሆነ መበደርን አይወድም፣ በስጦታ መልክ ደጋግሞ ሊሰጥህ ይችላል በድር ግን አጠይቀው፣ ወይ ደግሞ ቶሎ መልስ።

»» ከ12 ዞዳየኮች በውበትና ቁንጅና ተቀዳሚ ናቸው ሚባሉት ቶረሶች፣ ጄሚኒዎች፣ ሊብራዎችና አኳሪየሶች ናቸው፣ ከአራቱ አንደኞቹ የትኞቹ ናቸው በሚለው ላይ የአስትሮሎጂ ሊቃውንት አንድ አይነት አቋም ይዘው ባይታዩም ፣ በዛ ያሉት ግን አኳሪየሶችን ያስቀድማሉ።

»» ሳጁታሪየሶች መጪውን ጊዜ በህልም እና በራእይ መያት ይቻላቸዋል፣ አኳሪየሶች ግን መጪውን ጊዜ በእውኑ ያቁታል፣ እዚያው ነበሩ፣ ከዚያ መተው ነው የሚነግሩን፣ እንደ ነብይ ናቸው ፣ ነብይ ደግሞ ባገሩና በዘመኑ አይከበርም ይሰደዳል፣ እንዲሁም ይሰየፋል፣ ህብረተሰቡ አኳሪየሶችን ራሱ ያጠፋችዋል ራሱ ደግሞ ቆይቶ ይዘምርላችዋል።

በ1473 እስከ 1543 የኖረው ፓላንዳዊው ኒኮላስ ኮፐርኒካስ መሬት እና ሌሎች ፕላኔቶች ፀሃይን ይዞራሉ ስላል ብቻ በድንጋይ ተቀጥቅጦ ተገደለ፣ እሱ ከሞተ ከብዙ አመት ቧላ ግን መሬት እና ሌሎች ፕላኔቶች አለምን እንደሚዞሩ አለም የሚያቀው እውነት ሆነ።

Share Share

@ethiokokeb @ethiokokeb
@ethiokokeb @ethiokokeb
284 viewsedited  08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 10:58:24 ከየካቲት 13 እስከ መጋቢት 11 ለተወለዳቹ በሙሉ

»» ዞዳይካቹ ፓይሰስ ይባላል።
የፓይሰስ ኮኮብ ያለው ሰው በአንድ ስፍራ ተወስኖ ለረጅም ግዜ መቀመጥ አይችልም፣ በብዛት የሚገኙት በመንፈሳዊ ቦታዎች፣ በአርት ጋለሪዎች፣ ገዳማት ውስጥ ፣ በምሽት ክበቦች ውስጥ፣በትያትር ቤቶች ውስጥ፣ በባህር ዳርቻዎችና በጀልባ ላይ ሽርሽሮች ፓይሰሶችን ማግኘት ቀላል ነው።

»» ለአለማዊ ነገር ብዙም ናቸዉ፣ ለሹመት፣ ለሽልማትነ፣ ለማእረግ ፣ ለመሪነት ፣ ለስልጣንና ለሀብት አይጓጉም።

»» "እንደ ሚሊየነር መኖር እንጂ ሚሊየነር መሆን አልፈልግም " የተሰኘው ብሂል የፓይሰስን የገንዘብ ፍልስፍና ማለፊያ አድርጎ ይገልፀዋል፣ በአይነተኛ የፓይሰስ ልጆች ልብ ውስጥ ስስትና ስግብግብናት ቦታ የላቸውም።
»» ስለነገ ብዙም አይጨነቁም ፣ ትላንትን በትውስታ ዛሬን ደግሞ በትግስት ይኖራሉ፣ ቀለል ያለን የህይወት መስመር መንገድ ይመርጣሉ፣ በግዜያዊ ደስታም ይታለላሉ።

»» በተፍጥሯቸው የረጋና የሰከነ ምስኪን ሲሆኑ ፀባያቸውም ወላንሳ ነው፣ የሌሎች ስድብና ወቀሳ ግድ አይሰጣቸውም፣ ገፍተው ከመጡባቸው ግን እጃቸው አፍንጫን ከመስበር አይመለሱም።
»» ማንኛውንም አይነት የሀይል እርምጃና ጥቃት ደስ አይላቸውም ሰላማዊ ናቸው፣ በማንም ላይም የመፍረድ ዝንባሌ የላቸውም ።

ተስፋ አስቆራጭ ነገር ከገጠማቸው ችግሮችን ከመጋፈጥ ይልቅ ራሳቸው በፈጠሯት ውብ አለም ውስጥ መደበቅን ይመርጣሉ። ያልማሉ።
»» አንድን ፓይሰስ አለም ልትጠፋ ነው፣ ኦዞን ሳስቷል፣ ምናምን እያላቹ ብታወሩት ወይ ያዛጋል፣ ወይም ፈገግ ብቻ ይላል። ብዙም ግድ አይሰጣቸውም።

»» የፓይሰስ እግሮች ወይ ትላልቅ እና ዘርፋፋ ይሆናሉ፣ ወይ ደግሞ ትንንሾች እና ያማሩ ይሆናሉ ፣ የፓይሰሶች አይን ከብለል ከብለል የሚሉና እንግዳ በሆኑ ብርሃኖች የተሞሉ ናቸው፣ የአንድንዶቹ ወጣ ወጣ ያሉ ሆነው ማራኪ ናቸው፣ አይኖቻቸው በጣም ውብ ናቸው፣ ሲራመዱም ፈሰስ የሚሉ ይመስላሉ።

»» ፓይሰሶች በፈሳሽ ነገር ይሳባሉ ፣ በሻይ፣ በቡና እና በመጠጥ፣ ነገር ግን እንደ ካንሰር እና ስኮርፒዮ ከመጠጥ ቢርቁ ይሻላችዋል።

»» አይንአፋር ናቸው፣ ግን አይናፋርነታቸውን መቋቋም ከቻሉ አሪፍ የመድረክ ሰው መሆን ይችላሉ፣ ግን ተስፋ መቁረጥ የለባቸውም።

»» ስለመጪው ግዜ በህልማቸው ያያሉ ወይም ትከሻቸው ይነግራቸዋል ።

»» ሁነኛ በህሪዎቻቸውን ለማዋቅ ይከብዳል፣ መልሶቻቻውም ቁርጥ ያለ አይደለም ፣ ምንአልባት ሚለውን ቃል ያዘወትራሉ።

»» ለደስታም ሆነ ለሃዘን እንባቸው ቅርብ ነው፣ የሰላም እና የፀትታን ኑሮ ይናፍቃሉ።

»» አመጋገባቸው እንደ አከሄዳቸው ቀስ ያለ ነው።

Share Share

@ethiokokeb @ethiokokeb
@ethiokokeb @ethiokokeb
213 viewsedited  07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 10:56:49 ከታህሳስ 13 እስከ ጥር 12 ለተወለዱ በሙሉ

»» ዞዳይካቹ ወይም ኮኮባቹ ካብሪኮርን ይባላል
»» ካብሪኮርን በትግስትና በእርጋታ አድብቶ ነገር ግን በእርግጠኛነት በመንቀሳቀስ ግርግርና ሁካታን ሳይፈጥር ከግቡ ይደርሳል።

»» ካብሪኮርኖች ኑሮቸውን ማሻሻልና ራሳቸውን ማሳደግ ከሚችሉበት ስፍራ ሁሉ አይጠፉም፣ ወደፊት ማደግን እና መቀጠልን ከልባቸው ይናፍቁታል፣ ከሁሉም በላይ የመሆን ድብቅ ፍላጎት ኣላቸው።

»» ካብሪኮርን ቸበር ቻቻን የሚወድ ዝንጉ የጭፈራ ፓርቲ ወዳጅ አይደለም፣ ሆኖም ግን ከማህበራዊ ስብሰባዎች አይጠፋም።

»» ካብሪኮርንን ረታለው ማለት ያስቸግራል፣ ወደ ሰዎች የሚቀላቀለው ማንም ሳያስተውለው ነው፣ ሆን ብሎም ባይሆን ተፈጥሮ ከአከባቢው ጋ ወዲያው ይላመዳል፣ ጎልቶ አይታይም።

»» አካላዊ አቋሙ ምንም ይሁን ምን አቋሙ አንድ ነው ፣ ካለበት ስፍራ በፅናት ይቆማል፣ በራሱ እስኪወስን ድረስ ከቆመበት አይነቃነቅም።

»» የካብሪኮርን ስብእና የትካዜ ብርሃን ሁሌም ያረብብበታል፣ ብዙ ግዜ ይደብረዋል፣ ኮስታራና ቁምነገራም ነው ፣ ራሱን በስነ ስርአት ይመራል፣ ሌሎችን ስርአት ያስይዛል፣ የራሱን ተፈጥሮ ላማሸነፍ ይጥራል፣ አይታክትም።

»» እህል ሳይቀምሱ ውሎ ማደር ይችላል፣ የመፆም ውድድር ቢኖር ካፕሪኮርንን የሚረታው አይኖርም፣ ራሱን መጨቆን ይችላል፣ ይወደዋልም።

»» እጆቹ እና እግሮቹ በጣም ጠንካራ ናቸው፣ የካብሪኮርን ድምፆ እንደ ጅረት በፀትታና በእርጋታ የሚፈስ አይነት ሆኖ የማግባባትና የማባባል ቅላፄ አላው፣ በትህትናም የበለፀገ ነው።

»» ከተሰማራበት ጉደይ ፍንክች አይልም፣ አይዘናጋም፣ ለአላማው ጨካኝ ነው፣ ዘለፋን፣ ወቀሳን ፣ ውድቀትንና ጫናን ሁሉ ውጦ ዝም ይላል፣ ጉልበቱንም አያባክንም።

»» ከቀደሙት ይማራሉ ፣ ከእነርሱ ቀድመው ወደ ተራራው ጫፍ ለደረሱት ጥልቅ አድናቆት አላቸው፣ ከእነርሱ የጉዞውን ህግ ያጠናሉ።
»» የባህል እና ወግ ጠበቃዎች ናቸው፣ ባህልን ወግን ያከብራሉ፣ ስድነትን፣ አጉል ስድብን ይጠየፋሉ።

»» ከፊቱ የሚገረጡትን መሰናክሎች በጥንቃቄ ያስወግዳል።

»» በልጅነት ወራት ታማሚና ልንቁስቁስ ሊሆኑ ይችላሉ፣ እድሜ በጨመሩ ቁጥር ግን ብርቱዎች ለህመም የማይበገሩ ይሆናሉ፣ የሰከነ ተፈጥሯቸው ረዥም እድሜን ያጎናፅፋችዋል።

»» ከህመም በላይ ፍርሃት ፣ ስጋት፣ ጭንቀትና ትካዜ ከጀርሞች በላይ የከፉ የጤና ጠንቆች ናቸው ለካቤዎች፣ ብዙ አይጨነቁ። ትካዜ እና ሃዘን ካበዙ ፅኑ ራስምታት እና የኩላሊት ህመም ይጎበኛችዋል።

»» ወንዶቹም ሆኑ ሴቶቹ ቆዳቸው ቶሎ ይቆጣል ሰበበኛ ነው ።

»» ብዙ ግዜ የመነጠልና የብቸኝነት አባዜ አለባቸው።

»» አኳሪያሶች ያለፈውን የሚጠሉ ያሁኑን የሚንቁና መጪውን የሚያደንቁ ናቸው ፣ ካብሪኮርኖች ግን የጥንት የጠዋቱን ናፋቂዎች ናቸው።

»» ስለትዎልዱ ቀጣይነት እንደነሱ ሚጨነቅ የለም ፣ የአበትነት ተመሳሌት ናቸው።

Share Share

@ethiokokeb @ethiokokeb
@ethiokokeb @ethiokokeb
185 viewsedited  07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 10:54:45 ከ ህዳር 14 እስከ ታህሳስ 12 ለተወለዱ በሙሉ

»» ዞዳይካቹ ወይም ኮኮባቹ ሳጁታሪያስ ይባላል
»» ሳጁታሪየስ አመሰገንኩ ሲል ይሳደባል አሞገስኩ ሲል ያዋርዳል አስደሰትኩ ሲል ያሳዝናል እርሱ ግን ያጠፋውን ነገር አይታየውም ፣ በነሱ ቤት ለሰው አሪፍ ነገር ማረጋቸው ነው፣ ምን ክፉ ቃል ወጣኝ ብሎ ይገረማል፣ ጥፋቱ ቶሎ አይገባውም።

»» የሳጁታሪየስ ተፈጥሮ ከመሰሪነት እና ከተንኮል ሙሉ ለሙሉ የፀዳ ነው። ብዙዋቹ ፈጣን፣ ችኩልና ደንባራ ናቸው ፣ ነገር ስራቸው ሁሉ ሞቅና ደብለቅ ያለ ሆኖ ለዛና እርጋታ ግን ሊጎለው ይችላል።

»» ሳጁታሪየስ ሲናገር እጆቹን የማወናጨፍ ልማድ አለው።

»» ሁሌም ይደናፈቃሉ፣ ተደናፍቆም በወደቀ ጊዜ ያንጠለጠለው ወይም ያዘለው ሻንጣ ይወድቃል፣ ወድቆም ይበረገዳል።

»» የሳጁታሪየስ አይኖች እንደ ክዋክብት የሚያበሩና በደስታ የሚቁለጨለጩ ናቸው፣ የሰከነ ተፍጠሮ የላቸውም ፣ ይቁነጠነጣሉ ፣ ከአንድ ስፍራ ዘለግ ላለ ጊዜ አይቀመጡም፣ የሌላ ዞዳይክ የጎላ ተፅኖ ከሌለባቸው በስተቀር።

»» ለእንስሳት ልዩ ፍቅር አላቸው በተለይ ደግሞ ለፈረስ እና ለውሻ

»» ንግግራቸው ፍርጥ ያለ ነው። ብዙ ግዜ መድረክን ያፈቅሩታል

»» ወንዶቹም ሆኑ ሴቶቹ በልጅነታቸው ወደ ሀይማኖት ይሳባሉ፣ በእድሜ ከፍ ካሉ ጊዜ ግን የሃይማኖትን ቀኖና ጥያቄ ውስጥ ማስገባት ይጀምራሉ።

»» ሳጁታሪየሶች ሁሌም ተጓዦች ናቸው ፣ ውርርድ እና ቁማር ይወዳሉ እድለኞችም ናቸው ።
»» የማስታዎስ ችሎታቸው ድንቅ የሚባል ነው፣ በነፃነት ለመኖር የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፣ በጠባብ ክፍል፣ በትንሽ ገንዘብ፣ በአነስተኛ እውቀት ሲገደቡ ይጨንቃችዋል።

»» እድገት እንጂ ውድቀት አይታያቸውም፣ ሁሉም ነገር ይቻላል ብለው ነው ሚያስቡት።

»» የወደፊቱንም ነገር የመተንበይ ልዩ ችሎታ አላቸው ።

Share Share

@ethiokokeb @ethiokokeb
@ethiokokeb @ethiokokeb
162 viewsedited  07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 10:53:14 ከጥቅምት 14 እስከ ህዳር 13 ለተወለደ በሙሉ።

ዞዳይካቹ ስኮርፒዮ ይባላል
የስኮርፒዮ ዞዳይክ ያላቸው ሰዎች በሶስት አይነት ይታያሉ፣ ጊንጡ ስኮርፒዮ፣ ንስሩ ስኮርፒዮ እና እንሽላሊቱ ስኮርፒዮ። የጋራ ባህርያችው ግን ከልዩነታቸው በልጦ ይገኛል።

»» ብዙ ሰዎች የአንድ ሰው ኮኮብ ስኮርፒዮ መሆኑን በሚሰሙ ጊዜ በፍርሀት ወይም በአክብሮት የታጀበ ግልፅ ድንጋጤን ያሳያሉ፣ ይህም ስኮርፒዮ ሴክስን የማይጠግብ ሰው ነው ስለሚባል ነው፣ ሌላው ደግሞ ስለ ስኮርፒዮዎች የሚወራ ነገር አለ፣ አደገኛ እና ርህራዬ አልባ ናቸው ይባላል። ይህ ግን በአብዛኛው ትክክል ቢሆንም ስተትም ሊሆን ይችላል።

»» ስኮርፒዮን ማዋቅ ሆነ ትንሽ መለየት ይከብዳል ይህም የሆነው ተፈጥሮውን እና ባህርይውን አውጥቶ ከመግለጥ በብዙው ይታቀባል፣ የማይቻል ግን አይደለም።

»» ስኮርፒዮዎች በንቀት መመልከት እንደማያዋጣ ሁሉም የአስትሮሎጂ ባለሙያዎች ይስማሙበታል፣ ወዳጁን የማይጠቅምና ጠላቱን የማይጎዳ ስኮርፒዮ ማግኘት ይከብዳል ።
»» የስኮርፒዮ ኮኮብ ያለው ሰው ንግግሩ ፍርጥ ያለ ነው፣ ነገርን መሸፋፋንና ማሽሞንሞን እርሱ ዘንድ የለም።

»» ስኮርፒዮ ለማሞገስ አልያም ድግሞ ወዳጅ ለማፍራት ሲል አይዋሽም ፣ እርሱ አዛኝ ቅቤ አንጓች አይደለም፣ እድርባይም አይሆንም።

»» ስኮርፒዮ መልካም ነገር ከተናገርዎ ዋጋ ይስጡት ፣ ከምሩ ነው፣ መረዋ ድምፅ አልዋት ካለ ወደ ድምፃዊነት ሙያ ማምራት ይችላሉ።

»» ስኮርፒዮን ጠላቶቹ እንኳን ያከብሩታል፣ አክብሮቱ ግን በቅናት የታጀለ ይሆናል።

»» አወዛጋቢ ዞዳይክ ነው ፣ አንድአንዱ መልአክ ይለዋል አንዱ ደግሞ ጋኔል ነው ይለዋል ፣ ይህን የሚሉት የአስትሮሎጂ ሊቃውንት ናቸው፣ መልሱን ለናንተ ትተናል።

»» ስኮርፒዎዋች የሚያስፈሩትን ያህል በደግነትም የተሞሉ ናቸው ፣ ቃላቸው ያፅናናል፣ በእጃቸው የሚነኩት እና የሚዳስሱት ታማሚን የመፈወስ እና የእፎይታን ስሜት ይቀዳጃል።

»» የስኮርፒዎች ቆራጥነት አስደማሚ ነው ፣ህመምንም ይሁን ድህነትን ውርደትንም ይሁን ውድቀትንም በማይታመን ቆራጥነት ይቋቋሙታል።

»» ስኮርፒዮ የተዋለለትን ደግነትና ውለታ እስከወዲያኛው አይረሰም፣ ውለታውንም እጥፍ ድርብ አድርጎ ይመልሳል፣ በደል እና ክፋትንም ቢሆን እስከ እለተሞቱ ድረስ አይረሳትም

»» ስኮርፒዎች የሚታመሙት ከስንት አንዴ ነው ፣ ሲታመሙ ግን በጣም ይታመማሉ ።

»» ከሚፈልገው ቦታ ለመድረስ አድበቶ ይጠብቅና ጊዜው ሲደርስ ይንቀሳቀሳል፣ አንድን ነገር ከልቡ ከፈለገው ያገኘዋል፣ ተቀናቃኞቹን ሁሉ ያሸንፋል።

# አንድ ስኮርፒዮ ከመወለዱ አንድ አመት በፊት ወይም ደገሞ ከተወለደ አንድ አመት በዋላ ከቤተሰቡ ውስጥ አንዱ ዘመዱ ይሞታል

»» ዝምታንና ብቸኝነትን ያበዛሉ ፣ የያዙትን ከዳር ሳያደርሱ አይተውም፣ ሁሉንም በጥልቀት ይመረምራሉ ።

»» ነካክቶ መተው እነሱ ጋ የለም፣ ከወደዱ በጣም ይወዱሃል ከጠሉክም እንደዛው ናቸው
»» ከላይ ከላይ ሲታዩ ምስኪን እና ማንንም ሊጎዱ የማይችሉ ፍጡሮች ሆነው ይታያሉ፣ ግን አይደሉም።

»» የስኮርፒዮ ሴቶች ውበት ምትሃታዊ እና መግነጢሳዊ ነው፣ ስኮርፒዮ ሴት ጋ የሰነበተ ወንድ ሴቶች ይሻሙበታል፣ አንዳች መስተፋቅር ትቀባዋለች፣ የፍቅር እስከ መቃብሯ ሰብለ ወንጌል የስኮርፒዮ ሴት ምሳሌ ነች።

Share Share

@ethiokokeb @ethiokokeb
@ethiokokeb @ethiokokeb
153 viewsedited  07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 10:51:19 ከመስከረም 14 እስከ ጥቅምት 13 ለተወለዱ በሙሉ

ዞዳይካቹ ሊብራ ይባላል ትሁት እና ጨዋ አለመሆንን ከልባቸው ይጠሉታል አፍቅሬሰብ ቢሆኑም ታላቅ ጉባኤ የመፍራት አባዜ አለባቸው።

»» ሊብራዎች በተፍጠሯቸው የዋህ ሆነው የደስደስ ያላቸው ናቸው ፣ እንዲያም ሆኖ ግን አኩራፊነት እና እንቢተኝነትም የተፈጥሯቸው አንዱ አካል ነው።

»» የሊብራ ኮኮብ በወርቃማ የፍትሕ ሚዛን ትእምርት ይመሰላል፣ የሊብራም ባህሪ ልክ እንደ ሚዛን ነው አንዴ ይወርዳል አንዴ ይወጣል፣ የተመጣጠነ ሚሆነው አልፎ አልፎ ነው፣ የሊብረም ኑሮ ከፍ እና ዝቅ ነው።

»» እንደ ስብናቸው ሁሉ ፣የሊብራዎች መልክና ቁመና በቀላሉ ሊገለፅ የሚችል አይደለም፣ ሆኖም ብዙ ግዜ ፈገግ ሲሉ የሚገለጥ ስርጉድ ይታያል፣ በአገጫቸውም ላይም እንደዛው ፣ በፊታቸው ላይ እንኳን ከጠፋ ከእግራቸው ከሎሚው አጠገብ ዲምፕል አይጠፋም።

»» ሊብራዎች በድምፃቸው ቅላፄም ይላያሉ ድምፀ መረዋ ናቸው፣ ድምፃቸው ኩልል ያለ ነው

»» ሴቶቹ ሊብራዋች ውቦች ናቸው የደስ ደስ አላቸው ። ሊብራዎች ማራኪ ናቸው ፣ ተፍጥሯቸው አመዛዛኝ እና ፍታዊ ነው፣ ቢሆንም ግን ባህሪያቸው ወጥ አይደለም።

»» ሊብራዋች ክርክር ውስጣቸው ነው፣ ክርክር ይሁን እንጂ ከየትም ሆነው ይከራከራሉ።

»» የሆነ ግዜ ላይ በጣም ይሰሩ ይሰሩና ከሆነ ግዜ ቧላ ደግሞ ደክም ብሏቸው ከመሬትም የተሰበረ ብርጭቆ አያነሱም።

»» የአምሯውን የስሜት ሚዛን በመጠበቅ ረገድ ግን ሊብራዎች ደከም ይላሉ ፣ ሀዛን ይሰብራችዋል፣ ጤናቸው እስኪናጋ ድረስ በእንባ ይታጠባሉ።

»» የአምሯቸውን አና የአካላቸውን ጤና የሚጠብቁበት ብርቱ ደመነፍስ አላቸው ።

»» እነሱ ሚጠሉት ፍርድ ገምድልነት ፣ ኢፍታዊነትና ጭፍን እምነትን ነው።

»» ከውሳኔ ላይ ፈጥኖ ያለመድረስ ችግር ከሊብራዎች ላይ ባስ ሲል ይታያል፣ መዋከብ እና መቻኮልን አምርረው ይጠላሉ።

»» የሊብራ ልብ በፀዳና ባማረ ነገር ሁሉ ሃሴትን ታደርጋላች፣ የሊብራ ነፍስ አርቲስት ነች።

»» ሊብራ ሚለው ቃል መመጣጠንን፣ አቻ፣ እኩል መሆንን ያመለክታል። በተለይ ደግሞ ሚዛን የተሰኘው የአመርኛ ስያሜ ማመዛዘንን እና ማመጣጠንን የበለጠ ይግልፀዋል።

»» ታፍነው ፣ ተሸፍነውና ተዳፍነው ለመቆየት አይቻላቸውም።

»» የሊብራዎች ተፈጥሮ ቀለል ያለ እና ያልተወሳሰበ ነው። አመላቸው አይጎረብጥም፣ ዘና ያሉ ናቸው።
»» ጓደኝነትን ለመመስረት ይፈጥናሉ፣ በችኮላቸውም ሳቢያ በመጃመሪያ ሙከራቸው ላይ የሚገጥማቸው ሁነኛ ሰው አይደለም፣ ጋብቻም ላይ እንደዛው።

»» ሊብራዎች ሆደ ሰፊ ናቸው ፣ የሀይማኖት፣ የፖሎቲካና የአመላካካት ልዩነትን ያከብራሉ፣ በልዩነት ውስጥ ውበትና አንድነትን ማለምን ይችላሉ፣ ሊብራ የእኩልነትና ፍትህ ኮኮብ ነው።

Share Share

@ethiokokeb @ethiokokeb
@ethiokokeb @ethiokokeb
143 viewsedited  07:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ