Get Mystery Box with random crypto!

ቻይና የህክምና ባሉሙያዎችን ወደ ኢትዮጵያ ልትልክ ነው አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 7፣ 2012 (ኤፍ. | Ethio Anti Corona

ቻይና የህክምና ባሉሙያዎችን ወደ ኢትዮጵያ ልትልክ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የምታደርገው ጥረት የሚደግፉ የህክምና ባለሙያዎችን ቻይና ወደ ኢትዮጵያ ልትልክ ነው።

ቻይና ከኢትዮጵያ በተጨማሪም የህክምና ባለሙያዎችን ወደ ቡርኪና ፋሶ እንደምትልክ ነው የተገለፀው።

እነዚህ የህክምና ባለሙያዎች ልምዳቸውን ያጋራሉ እንዲሁም የኮሮና ቫይረስን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የሚያስችሉ መመሪያዎችን እና ቴክኒካል ምክሮችን ለጤና ባለሙያዎች እና ለህክምና ተቋማት ያካፍላሉ ተብሏል።

ቻይና ከአፍሪካ ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንዳላት የገለፁት የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዝሆ ሊጂዓን በአፍሪካ ቫይረሱን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር እየተከናወነ ያለውን ስራ ሀገራቸው እንደምትደግፍ ገልፀዋል።

በአፍሪካ ሀገራት ያለውን ሁኔታ በትኩረት እየተከታተለች መሆኑን ያስታወቀችው ቻይና ቫይረሱን ለመቆጣጠርና ለመከላከል የሚያስችሉ መሳሪያዎችን ማቅረቧን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።