Get Mystery Box with random crypto!

ሳተላይት ምንድን ነው? ሳተላይት ማለት Space ላይ የሚሽከረከር እቃ ሆኖ ከመሬት Signal | ethio andromeda with nahom💫

ሳተላይት ምንድን ነው?

ሳተላይት ማለት Space ላይ የሚሽከረከር እቃ ሆኖ ከመሬት Signal ተቀብሎ የመጣለትን Signal Amplify አርጎ ወደ መሬት መልሶ የሚልክልን መሳሪያ ነው።

ሁለት የሳተላይት አይነቶች ሲኖሩ እነዚህም Passive እና Active ይባላሉ። Passive የምንለው ከአንድ የመሬት መአዘን ወደ ሌላኛው የምድር ክፍል Microwave Signal ተቀብሎ የሚልክ ሲሆን ለምሳሌ በተፈጥሮ ጨርቃ Passive ነው።

Active የሚባለው በአለም ላይ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን Microwave Signal ወደ Space ልኮ የተላከውን Signal ሳተላይቱ Amplify አርጎ መልሶ ወደ መሬት የሚልክልን ነው። Active ሳተላይት ላይ Antenna System, Transmitter, Power Supply, Receiver እና የመሳሰሉት ኮምፖነንቶችን ይይዛል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ሳተላይትን ሀገር Soviet union (Russia) ስትሆን ይሄም የሆነው በ1957 ነው። ስሙም Sputnik 1 ተብሎ ይጠራ ነበር። ይህ ሳተላይት 58cm Diameter ሲኖረው 4 antenna እንዲሁም አነስተኛ ሞገድ (low frequency) የሆነ Signal ነበረው። Signal ያስተላለፈው ለ22 ቀን ሲሆን ከዛ በሃላ ባትሪው አልቆ ከጥቅም ውጪ ሊሆን ችላል።

በቀጣዩ አመት አሜሪካ ያስወነጨፈችው ሳተላይት ከመጀመሪው አንጻር ስኬታማ የሆነ ነበር። ይህች ሳተላይት የድምጽ ሞገድ ያስተላለፈች ሲሆን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የ አሜሪካ ፕሬዝደንት የነበሩት Dwight D. Eisenhower ለአለም ህዝብ "Peace on earth and good will toward men everywhere." የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ችለው ነበር።

ከዚህ በሃላ የተለያዩ ሀገራት የተለያዩ አይነት ሳተላይቶችን ሰርተው ማስመንጠቅ እና ማምጠቅ ችለዋል። በአሁኑ ሰአት በአለማችን ላይ ከ 2000 በላይ ሳተላይቶች በጠፈር ላይ ይገኛሉ። በ ኢኮኖሚ ደካማ የሆኑ ሀገራት ሳተላይትን ከበለጸጉ ሀገራት እየተከራዩ ይጠቀማሉ። ለምሳሌ ሀገራችን ኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ በኪራይ የምትጠቀም ሲሆን ከጥቂት አመታት በሃላ የራሳን ለመስራት እየታተረች ትገኛለች።

በነገራችን ላይ ሳተላይትን መስራት ብቻውን ዋጋ የለውም የተሰራውን ሳተላይት የማመንጠቂያ መዐከል ያስፈልገዋል። ይሄ የመንኮራኮር ማመንጠቂያ ማእከል ያላቸው ሀገራት በጣት የሚቆጠሩ ሲሆን አብዛኛው የአለም ሀገራት የ ሩሲያ እና የአሜሪካንን ማመንጠቂያ ስፍራ ይጠቀማሉ። ከቅርብ ጊዜያት ጀምሮ ከመንግስት አልፎ የግል ኩባንያዎችም በዚህ ዘርፍ ላይ በስፋት ተሰማርተዋል።

እንዴት ትርፋማ ይሆናሉ ብሎ የሚያስብ ይኖራል። እንዴት መሰላቹ የተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያውች በየአመቱ የሚከፍሉት ገንዘብ አለ ለሳተላይቱ ባለቤቶች።

ለምሳሌ EBS Nile sat ላይ ይጠቀማል በዚህ ምክንያት በየአመቱ ከ500000 ብር በላይ ይከፍላል። አብዛኞቹ የ አፍሪካ ሀገራት የተቃዋሚዎቻቸውን ቻናል Jam አድርጎ ማጥፋት ሲያቅታቸው በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላሮችን ለ ሳተላይት ባለንብረቶች እየከፈሉ ከአየር ላይ ያስወርዳሉ።

በሀገራችን ሁኔታም ይሄ በስፋት የተለመደ ነው። በፊት ESATን የመሰሉ የመንግስት ተቃዋሚ ቻናሎችን ለማውረድ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን እያወጡ
ነበር::
JOIN AND SHARE BEST CHANNEL
@ethioandromedawithnahom
@ethioandromedawithnahom
@ethioandromedawithnahom
JOIN DISCCUS
@ethio_andromeda_info
@ethio_andromeda_info
@ethio_andromeda_info
SUBSCRIBE YOUTUBECHANNEL
https://youtube.com/channel/UCWwutRK77dZkaz6_ARrO2jA