Get Mystery Box with random crypto!

ethio andromeda with nahom💫

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioandromedawithnahom — ethio andromeda with nahom💫 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioandromedawithnahom — ethio andromeda with nahom💫
የሰርጥ አድራሻ: @ethioandromedawithnahom
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 643
የሰርጥ መግለጫ

ethio ethio with nahom
በዚህ ቻናል
ስለ አስትሮኖሚ
ስለ አስትሮሎጂ
ስለ ቴክኖሎጂ
አዳዲስ መረጃ
አነቃቂ ንግግሮች(inspire)
@ethioandromedawithnahom
@ethioandromedawithnahom
👇
ለአስተያየት
//
@nahom213 //
በዩቱብ
https://youtube.com/channel/UCWwutRK77dZkaz6_ARrO2jA

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-10 17:20:53 https://t.me/sport4_3_3
668 viewsናሆም የኪድዬ ልጅ, 14:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 12:24:05 ​ጨረቃ ኤልያኖች ጠልፈዋት ቢሄዱ ምን ይፈጠራል? ጨረቃ በኤልያኖች ብትወሰድ የዓለም መጨረሻ ሊሆን ይችላል ?

ወደ ፊት የሰው ልጅ የሚጠብቀው አይቀሬ ውጊያ ከኤልያኖች ጋር ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል ኤልያኖቹም ምድርን ለብቻቸው ለመቆጣጠር እኛን ማጥፋት ሊመርጡ ይችላሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት ናሳ ከፍተኛ ክትትል እያደረገባቸው ሲሆን ስቴፈን ሐውኪንግ ደግሞ በተቻለ መጠን የሰው ልጅ ከባዕዳን ፍጡራን ጋር ፊት ለፊት ባይገጥም ይመረጣል ብለው ነበር፡፡

አሁን እየተፈራ ያለው ነገር እነዚህ ባዕድ ፍጡራን ወደ ፊት ከሰው ልጅ ጋር በቀጥታ ጦርነት ውስጥ ከሚገቡ ጨረቃን በቀላሉ መገንጠልን ቀላሉ ስልታቸው ሊያደርጉ ይችላል ተብሎ ይታመናል፡፡

ለመሆኑ ላለማስገንጠል እንችል ይሆን? ኤልያኖች ጨረቃን ገንጥለው ቢወስዷት ምን ይፈጠራል?

ጨረቃን ላለማስገንጠል መሰዋዕትነት መክፍል እንዳለብንና እንደሌለብን የምናውቀው ታዲያ ጥቅምና ጉዳቷን ስንረዳ ነውና እነሆ ብለናል፡፡

ምድራችንን ከሌሎች ክዋክብት፣ ዐለታማ አካላት፣ በራሪ አካላት፣ ግዙፍ ፕላኔቶች፣ ጨረቃዎችና ሌሎች የግዙፉ ህዋ ፍጡራን ጋር አንድም ሆነ ሌላ የሚያስተሳስር ጉዳይ አይጠፋም፡፡ በተለይ የአንደኛው መኖር ለሌላኛው ወሳኝ የሚሆንበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡

አንዳድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ጨረቃ በከፊል ከምድር በፈረሰ አካል እንደተሰራች ነው በምድራችን እና በጨረቃ መካከል ያለው ርቀት ደግሞ 384.400 ነው።

ጨረቃ በዚህ ርቀት መሆኗም
ለምድራችን ህልውና ትልቅ አስተዋጽዖ እንዲኖራት የታሰበ ይመስላል፡፡ ተፈጥሮ በዚህ መልኩ ያስተሳሰረቻቸው ሁለቱ ግዙፍ አካላት አንደኛው ለአንደኛው መኖር ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ የጨረቃና የምድር ትስስር ከሁሉ ነገር አስቀድሞ የሚጠበቀውና የመጀመሪያ የሚሆነው የጨረቃ አለመኖር የሚያስከትለው ከባድ የሆነ የባህር ወጀብ ለውጥ ነው፡፡ ባህሮች በጨረቃ ስበት ሥር ወጀቦቻቸው ተወጥረው ይገኛሉ፡፡

ጨረቃ ባትኖር የባህር ወጀቦቹ
መጠናቸው አሁን ካሉበት መጠን ሦስት እጥፍ ይጨምሩ ነበር
በሌላ በኩል ደግሞ ጨረቃ የሃይቆችን አልቲትዩድ ላይ ተፅዕኖ አላት፡፡

ጨረቃ በስበት ኃይል ወጥራ መያዝዋም በምድር ወገብ አካባቢ ከፍተኛ የውሃ መጠን እንዲኖርና በምድር ዋልታዎች ዝቅተኛ የውሃ መጠን እንዲኖር መንስዔም ነው፡፡

ጨረቃ ባትኖርም ይህ ውሃ ወደ ሰሜናዊ አልያም ደቡባዊ ዋልታ መፍሰሱና መከማቸቱ የማይቀር ነው፡፡

ጨረቃ የምድርን ሽክርክሪት በማዘግየት ትልቅ ሚና አላት በእርግጥ አብዛኞቹ ቀናቶች ላይ መዛባት ሊከሰትም ይችላል በተለይም ቀደም ሲል እንደነበረው ምድር ከቢልዮን ዓመታት በፊት ጨረቃ ሳትኖር፣ አማካኝ የቀን ሰዓታት ከ8 እስከ 10 ነበበር ይህ ሁኔታም ዛሬ ላይ ጨረቃ ባትኖረን ሊከሰት ይችላል ማለት ነው፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም አያሌ እንግዳ የሆኑ ክስተቶች ይከሰታሉ፡፡ በከፍተኛ ሁኔታ የንፋስና የአውሎ ንፋስ መጠንና ዐቅም ይጨምራል፡፡ በተያያዥም በምድር ላይ የሚኖረው የሰው ልጅም ሆነ አጠቃላይ ሕይወት ያለው ነገር ሁሉ፣ በኢቮሊሽን የሚከሰቱ ነገሮች ለይ ተፅእኖ መፍጠሩ የማይቀር ይሆናል፡፡

ሌላኛው እና ዋነኛው ጉዳይ፣ ምድር 23 ዲግሪ አጋድላ እንድትቀጥል የጨረቃ የስበት ኃይል ዋነኛ ሥራ ነው እናም ይህ የምድር 23 ዲግሪ ማጋደል መዛባቱ የማይቀር ነው ምድርም በራሷ ዛቢያ የምትሽከረከርበት ሁኔታ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሊገባ ይችላል፡፡ እንደ አንዳንዶች ሳይንሳዊ ግምት ደግሞ የመሬት ማጋደል ወደ 0 ዲግሪ ሊወርድ ይችላል ይህ ክስተት ደግሞ አብዛኞቹ የመሬት ክፍል ፀሐይን በቀን ለተወሰነች ደቂቃ ብቻ እንዲያገኟት ያደርጋል፡፡

ስለዚህም የጨረቃችን አለመኖር ከቀን እስከ ማታ በሚኖረን የዘልማድ ሕይወት ላይ ተፅዕኖ ማሳረፉ አይቀሬ ነው ጨረቃችን ብትጠፋ ከዚህ የበለጠ ጉዳቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ይታመናል፡፡

SHARE AND JOIN TELEGRAM CHANNEL
-----------------------------
@ethioandromedawithnahom
@ethioandromedawithnahom
@ethioandromedawithnahom
JOIN DISCCUS
-------------------------------
@ethio_andromeda_info
@ethio_andromeda_info @ethio_andromeda_info
SUBSCRIBE BEST YOUTUBE CHANNEL
---------------------------------
https://youtube.com/channel/UCWwutRK77dZkaz6_ARrO2jA
112 viewsናሆም የኪድዬ ልጅ, 09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 07:24:41 ሰለ ጠፈር ሊያውቋቸው የሚገቡ አስደናቂ እውነታዎች

1. ጠፈረ ሙሉ ለሙሉ ፀጥ ያለ ነው።

ጠፈር ሙሉ ለሙሉ ፀጠ ያለ ነገረ የሆነው ምንም አይነት አየር ባለመኖሩ ነው አየር ከሌለ ደግሞ የድምፅ ሞገድ ከቦታ ወደ ቦታ ሊንቀሳቀስ አይችልም ሰለዚህ ጠፈረ ፀጠ ያለ ነው ጠፈርተኞችም በአንድ ሜትር እርቀት ላይ ቢሆኑ እንኳን የሚግባቡት በስልክ ወይም የራዲዮ ሲግናልን በመጠቀም ነው ።

2. ፕላኔት ማርስ ላይ ሕይወት ያለው ነገረ ይኖር ይሆን።

በ1986 የናሳ ተቋም ከማርስ ፕላኔት ላይ የወሰደው ናሙና የትናንሽ ፍጡሮች (microorganisms) የሰውነት ስብርባሪ የሚመስል ነገረ አግኝቶ ነበር።

3. በዚህ ግዙፍ ዩንቨርስ ውስጥ ምን ያክል ከዋክብቶች እና ፕላኔቶች እንዳሉ አይታወቅም።

በዚህ ዩንቨረስ ውስጥ እጅግ ብዙ ከዋክብቶች በመኖራቸው ምክንያት በቁጥር እንዲ ነው ብሎ መገመት ይከብዳል ይሁን እንጂ በኛ ጋላክሲ ውስጥ ብቻ ከ 200 እስከ 400 ቢልዬን ክዋክብቶች እንዳሉ ይገመታል በተመሳሳይ በቢልዬን የሚቆጠሩ ፕላኔቶች እንዳሉ ይገመታል።

4. የኒውትሮን ክዋክብቶች በራሳቸው ዙሪያ በሰከንድ 600 ጊዜ ይዞራሉ።

እጅግ ግዙፎቹ ክዋክብቶች ሲያረጁ ወደ ኒውቶሮን ወደ ሚባል የክዋክብት ዝርያ ይቀየራሉ የኛን ፀሐይ በማጨማደደ መሬትን ብናሳክላት ወደ ኒውትሮን ኮከብ መቀየር ትችላለች።

5. ጨረቃ ላይ የሚገኘው የሰው ልጆች የጫማ አሻራ ለ 100 ሚልዬን ዓመታት ያክል ምንም ሳይሆን ሊቀመጥ ይችላል።

ጨረቃ ላይ ምንም አይነት አየር ባለመኖሩ ምክንያት የጫማው አሻራ አይጠፍም።

6. የቬኑስ አንድ ቀን ከመሬት አንድ ዓመት ጋር እኩል ነው።

ፕላኔት ቬኑስ በራሷ ዛቢያ ስትሽከረከር እጅግ ቀርፍፍ በመሆኗ ምክንያት ቬኑስ ላይ የምንኖር ቢሆን ኑሮ አንድ ቀን የምንለው የመሬትን አንድ ዓመት ነበር።

7. ሁለት ብረቶችን ጠፈር ላይ ሁነን ብናነካካቸው ተጣብቀው ይቀራሉ

ይሄም የሆነው ጠፈረ ላይ ምንም አይነት ጋዝ ወይም አየር ባለመኖሩ ነው

8. ከኛ ምድር 10 ቢልዬን የብርሃን ዓመት የሚርቅ ቦታ ላይ ሳይንቲስቶች እጅግ ግዙፍ ውሃ ጠፈር ላይ ተንሳፎ አግኝተዋል።

ጠፈረ ላይ የድንጋይ ስብርባሪ ወይም የውሃ በረዶ በቀላሉ ሊገኝ ይችላል ነገረ ግን ፈሳሽ ውሃ ጠፈረ ላይ ሲገኝ ለመጀመሪ ጊዜ ነበር ይሄ ውሃ የኛ አለም ላይ የሚገኘውን ውሃ 140 ትሪሊዮን ጊዜ ይበልጣል::
JOIN AND SHARE BEST CHANNEL
@ethioandromedawithnahom
@ethioandromedawithnahom
@ethioandromedawithnahom
JOIN DISCCUS
@ethio_andromeda_info
@ethio_andromeda_info
@ethio_andromeda_info
SUBSCRIBE YOUTUBE CHANNEL
https://youtube.com/channel/UCWwutRK77dZkaz6_ARrO2jA
211 viewsናሆም የኪድዬ ልጅ, 04:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 11:17:40 የውሃው አለም (the water world)

"The water world" ወይም ሙሉ በሙሉ በውሃ የተሸፈነው ፕላኔት ወይም በሳይንትፊክ ስሙ Gj 1214B ይባላል።

የኛ ፕላኔት(ፈለከ) ወይም የኛ አለም 75% ፕርሰነተ በውሃ የተሸፈነ ሲሆን 25% ደግሞ በውሃ ያልተሸፈነ ምድር ነው ይሄም ማለት ሰባቱ አህጉሮች አፍሪካን ጨምሮ የመሬትን 25% ብቻ ነው የሚሸፍኑት እንደማለት ሲሆን ቀሪው 75% በዊቂያኖሶች እና በተለያዩ የውሃ አካላቶች የተሸፈነ ነው ይሄ በእራሱ የኛን መሬት አስደናቂ እና በውሃ ያሸበረቀች አለም ሊያስብላት ይችላል ነገረ ግን ይሄ Gj1214B የተሰኘው ፕላኔት ደግሞ ይበልጡን ያስደምመናል ከስሙ እንደምነረዳው ይሄ የውሃው አለም 100% በውሃ የተሸፈነ ሲሆን እዚህ አለም ላይ መኖር የሚችሉት መዋኘት የሚችሉ ፍጡሮች ብቻ ናቸው ተብሎ ይታሰባል የውሃው አለም ላይ የሚገኘውን ውሃ ብንመዝነው 10% የሚሆነውን የፕላኔቱን ክብደት መሸፈን ይችላል ነገረ ግን መሬት ላይ የሚገኘውን ውሃ ብንመዝነው 0.05% ብቻ የመሬትን ክብደት ቢሸፍን ነው

የውሃው አለም ከኛ ፕላኔት 40 የብርሃን አመታትን ይርቃል ይሄም ማለት በብርሃን ፍጥነት ብንጓዝ እንኳን ወደዚህ አለም ለመድርስ 40 አመት ይፈጅብናል እንደማለት ነው ብርሃን 40 የሚፈጅበት በሰከንድ 300,000km እየተጓዘ ነው በአሁኑ ዘመን እጅግ ፈጣን በሚባለው "NASA solar probe" እስፔስ ክራፍት ብንጓዝ ደግሞ ወደዚህ አለም ለመድረስ ያለማቋረጠ 700,000 አመታትን መጓዝ አለብን አስተውሉ ይሄ እስፔስ ክራፍት በሰሀት እስከ 394,000km ይጓዛል ይሄ በራሱ አስደናቂ ፍጥነት ነው

ይሄ አለም የተገኘው እንደ ኢትዮፒያኑ አቆጣጠር በ2001 ሲሆን በክብደት ከመሬት 6 እጥፍ የሚተልቅ ፕላኔት ነው ኔፕቱን ከተሰኘቹ ፕላኔት ግን እንደሚያንስ ይገመታል የውሃው አለም የሚዞረው ኮከብ ደግሞ "Gliese 1214" ተብሎ ይጠራል ይሄ ኮከብ "red dwarf " ተብለው ከሚጠሩ ኮከቦች ስር ይመደባል ይሄ ኮከብ ከፀሐይ አንፃር ትንሽዬ ሲሆን የፀሐይን 16 በ 100 ክብደት ብቻ ነው መሸፈን የሚችለው

ሙቀቱ ከፍተኛ ቢሆንም ልዩ ፍጡሮች ሊኖሩበት እንደሚችሉ ይገመታል የውሃው አለም ላይ የሚኖሩ ፍጡሮች ደግሞ መሬት ላይ ከሚኖሩ ፍጡሮች ፍፅሙ የተለዩ ሊሆኑ ይችላሉ ምክንያቱም የውሃው አለም ላይ ከፍተኛ ሙቀት እና ከፍተኛ የውሃ መጠን አለ ሌላኛው ነገረ ደግሞ ከፍተኛ አትሞስፐሪክ ፕሬዠር መኖሩ ነው ሰለዚህ እዚህ አለም ላይ የሚኖሩ ፍጡሮች ሙቀቱን እና አትሞስፔሪክ ፕሬዠሩን መቋቋም የሚችሉ መሆን አለባቸው በተመሳሳይ ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ ደግሞ ጥሩ ዋናተኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል የሰው ልጆች ግን በዚህ አለም ላይ መኖር አይችሉም ተብሎ ይታሰባል ምክንያቱም የሰው ልጆችም ሆን የኛ አለም ላይ የሚኖሩ ፉጡሮች planet earth ላይ ብቻ መኖር እንዲችሉ ተደርገው ነው የተፈጠሩት ሰለዚህ የውሃው አለም በሙቀት በከባቢ አየር እንዲውም በሌሎች ነገሮች የኛን አለም እስካልመሰለ ድረስ መኖር አይቻልም እዚህ አለም ላይ ወይም የተለይ ቴክኖሎጂን መጠቀም አለብን የሆነው ሁን የውሃው አለም 120 ድግሪ እስከ 280 ድግሪ ይሞቃል ተብሎ ይገመታል በተመሳሳይ ጠጣር ወይም ከፍ ያለ ከባቢ አየረ አለው

ይሄ ሙሉ በሙሉ በውሃ የተሸፈነው ፕላኔቱ የዊቂያኖሱ ጥልቀተ እስከ 15,000 km እንደሚሆን ይገመታል ይሄም ማለት ከአዲስ አበባ እስከ አስመራ ያለውን እርቀት 12 እጥፍ መሆኑ ይችላል የኛ አለም ላይ የሚገኙት ዊቃኖሶች ደግሞ እስከ 11km ጥልቀት ቢኖራቸው ነው ይሄም ከውሃው አለም ጋር ሲነፃፀር እጅግ በጣም ትንሽ ነው ሌላው ይሄንን ፕላኔት ለየት ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ ደግሞ ፕላኔቱ በጣም ከፍተኛ የሆነ ሙቀት ኑሮት ፈሳሽ ውሃን መያዙ ነው እደሚታወቀዎ ወሃ ከ 100 ዲግሪ ሴሊሴሽ በላይ በፈሳሽ መልክ አይገኝም ወይም መትነነ ነበረበት ግን አልሆንም

ምክንያቱም ውሃ በኛምድር ላይ ብቻ ነው 100° ሴልሴሽ የሚፈላው ወይም ውሃ ለመፍላቲ ሙቀት ብቻ በቂ አደለም ከባቢ አየርም ይወስነዋል ከፍ ያለ "atmospheric pressure " የሚኖር ከሆነ ውሃ የሚፈላበት የሙቀት መጥን ከፍ ያለ ይሆና በተመሳሳይ ዝቅተኛ "atmospheric pressure " የሚኖር ከሆነ ዝቅ ባለ ሙቀት ነው ውሃ የሚፈላው ለምሳሌ የአለማችን ትልቁ ተራራ የሆነው ኤቨረስት ላይ ውሃ የሚፈለው 70°ማ ሴልሴሽ አከባቢ ነው ምክንያቱም ዝቅተኛ የሆነ ከባቢ አየር ስላለው ነው ባጠቃላይ ውሃ 100° የሚፈላው 1 ATM ላይ ወይም 101000 Pascal pressure ላይ ነው ቅድም እንደገለፅነው ፕላኔቱ ከፍተኛ የሆነ ከባቢ አየር አለው ሰለዚህ ውሃ በዚህ ምድር ላይ በቀላሉ አይፈላም ማለት ነው

ሰለ ውሃው አለም ቪድዮ ለማየት ይሄንን ሊንክ ተጠቀሙ





194 viewsናሆም የኪድዬ ልጅ, 08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 19:27:54 እውነት..በፍልስፍና እይታ


ሱፊስቶች ስለ እውነት ይህንን እይታ ያስቀምጣሉ
<< እውነት የሚመጣው ከስሜት ነው። ስለዚህም የእውነት ጥያቄ ምላሹ ስሜትህ ነው።...ስለዚህም እውነት ማለት የምትቀምሰው፣ የምታሸተው፣ የምትነካው፣ የምትሰማውና የምታየው ነገር ነው። >> ይላሉ
ይህንን እይታ ካልተቀበሉት ፈላስፎች ግንባር ቀደሙ ፕሌቶ ነበር እሱም እንዲህ አለ...
<< እውነት ማለት ሱፊስቶች እንደሚሉት ስሜትህ ከሆነ እውነት የለም ማለት ነው። ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰው አንድን ነገር የሚያሸተው፣ የሚነካው፣ የሚቀምሰው፣ ወዘተ...በተለያየ መንገድ ነውና። >>

፨ አንድን ነገር ሁለት ሰዎች በሁለት መንገድ ከሰማው ወይም ካየው ነገሩ አንድ መሆኑ አብቅቷል፤ ስለዚህ ነገሩ በራሱ እውነት አይደለም! እያለን ነው እንግዲህ ፕሎቶ...!

<< ስለሆነም የእውነት ጥያቄ የሚመለሰው በምክንያታዊ ማሰብ(Reasoning) እንጂ በስሜት አይደለም።...አንድን ነገር ለማየት ማሰብ ያስፈልጋል። አስቀድመህ የምታስበው ነገር ወደ አይንህ መልእክት አስተላልፎ የምታየውን ማየት ቻልክ፤ በሌላ አባባል የምታየው እውነት መሆኑን በማሰብህ ነው፤ ስለዚህ እውነት ማለት 'ማሰብ' ነው ። >> ይላል ፕሉቶ

የጠርጣሪነት ፍልስፍና መስራች የሆነው #ፊሮ ደግሞ የሱፊንም ሆነ የፕሌቶን አስተሳሰብ አይቀበልም ያንንም አስመልክቶ ይህንን ይለናል...
ስለ ሱፊዎች እምነት...
<< የምታየውን እንዴት ማመን ትችላለህ?...ፀሐይ ከመሬት እጅግ ብዙ እጥፍ ግዙፍ እንደሆነች እናውቃለን። ነገር ግን መሬት ላይ ቆመን ፀሐይን ስናያት ትንሽዬ ነች። ስለዚህ የምናየው ነገር ሁሉ እውነት አይደለም ማለት ነው። >>
ስለ ፕሎቶ እና አርስቶትል እይታ...
<< እንግዲህ አንድን ነገር እውነት የሚያደርገው ማሰብ ስለቻልን ከሆነ፦ ሰው የሚያስብ ፍጡር ነው፤ ሶቅራጥስ ደግሞ ሰው ነው፤ ስለዚህም ሶቅራጥስ ሰው ስለሆነ ማሰብ ይችላል ማለት ነው። ይኽ ደግሞ ሁልጊዜ አይሠራም ምክንያቱም ሰው ሁሉ ማሰብ ይችላል ማለት ሞኝነት ነውና። >> ይለናል ፊሮ

፧

ከሁሉም በተለየ መልኩ የሱፊ እምነት ተከታይ የነበረው ጎርጂያስ ደግሞ እውነትን በተናጋሪው የንግግር እና የማሳመን ችሎታ ይመነዋል ያንንም አስመልክቶ ይህንን ይለናል...
<< እውነት የሚባል ነገር የለም፤ ቢኖር እንኳን ነገሩን ነገሩን እውነት የሚያደርገው የአንተ ተናግሮ የማሳመን ችሎታ እንጂ የነገሩ እውነትነት አይደለም >> ይላል ሲያብራራው ደግሞ ይህንን ያክልበታል...
<< ምንም ነገር የለም፤ አንድ ነገር ቢኖር እንኳን መኖሩን ማወቅ አንችልም፤ ማወቅ ብንችል እንኳን ስለዚያ ነገር ማስረዳት አንችልም፤ ምክንያቱም አለ ብለን የምናስበው ነገር የለምና፤ ስለዚህም አለ ብለን ነገሩን ስላሰብን ብቻ እንዴት በድፍረት አለ ብለን እንፈርዳለን>> ይለናል...
በምሳሌ ሲያብራራው ደግሞ ይህንን ያክላል...
<< ለምሳሌ አንድን ነገር ሁለት ሰዎች እንዴት እንደሚያዩት ብትጠይቅ በጣም የተለያየ መልስ ታገኛለህ፤ ስለነገሩ አስረዱኝ ብትላቸው ደግሞ ከሁለቱ ሰዎች የአንዱ ንግግር ስለነገሩ የበለጠ ሊያሳምንህ ይችላል። ለዚህም ነው ነገሮች እውነት ናቸው ብለን እንድናምን የተሻለ ተናጋሪ ሰው መፍጠር አለብን የምንለው...>>

፨ መቼም በፍልስፍናው ዓለም እውነትን በተመለከተ ዛሬም ድረስ የሚያስማማ እይታ ማግኘት አልተቻለም...በርግጥም የፍልስፍና አላማው መስማማት አይደለምና...ዛሬ ላይ #እውነትን በተመለከተ ያሉት እይታዎችም በዚህ ዙርያ የሚሽከረከሩ ይመስለኛል...
፩, እውነት አለ #ፍጹማዊም ነው
፪, እውነት አለ ግን #አንፃራዊ ነው
፫, እውነት ብሎ ነገር #የለም...!!
፧
ምንጭ ፦ ጥበብ ከጲላጦስ ቅጽ ፩
JOIN AND SHARE BEST CHANNEL
@ethioandromedawithnahom
@ethioandromedawithnahom
@ethioandromedawithnahom
JOIN DISCCUS
@ethio_andromeda_info
@ethio_andromeda_info
@ethio_andromeda_info
SUBSCRIBE YOUTUBE CHANNEL
https://youtube.com/channel/UCWwutRK77dZkaz6_ARrO2jA
298 viewsናሆም የኪድዬ ልጅ, 16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 17:40:51 ሳተላይት ምንድን ነው?

ሳተላይት ማለት Space ላይ የሚሽከረከር እቃ ሆኖ ከመሬት Signal ተቀብሎ የመጣለትን Signal Amplify አርጎ ወደ መሬት መልሶ የሚልክልን መሳሪያ ነው።

ሁለት የሳተላይት አይነቶች ሲኖሩ እነዚህም Passive እና Active ይባላሉ። Passive የምንለው ከአንድ የመሬት መአዘን ወደ ሌላኛው የምድር ክፍል Microwave Signal ተቀብሎ የሚልክ ሲሆን ለምሳሌ በተፈጥሮ ጨርቃ Passive ነው።

Active የሚባለው በአለም ላይ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን Microwave Signal ወደ Space ልኮ የተላከውን Signal ሳተላይቱ Amplify አርጎ መልሶ ወደ መሬት የሚልክልን ነው። Active ሳተላይት ላይ Antenna System, Transmitter, Power Supply, Receiver እና የመሳሰሉት ኮምፖነንቶችን ይይዛል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ሳተላይትን ሀገር Soviet union (Russia) ስትሆን ይሄም የሆነው በ1957 ነው። ስሙም Sputnik 1 ተብሎ ይጠራ ነበር። ይህ ሳተላይት 58cm Diameter ሲኖረው 4 antenna እንዲሁም አነስተኛ ሞገድ (low frequency) የሆነ Signal ነበረው። Signal ያስተላለፈው ለ22 ቀን ሲሆን ከዛ በሃላ ባትሪው አልቆ ከጥቅም ውጪ ሊሆን ችላል።

በቀጣዩ አመት አሜሪካ ያስወነጨፈችው ሳተላይት ከመጀመሪው አንጻር ስኬታማ የሆነ ነበር። ይህች ሳተላይት የድምጽ ሞገድ ያስተላለፈች ሲሆን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የ አሜሪካ ፕሬዝደንት የነበሩት Dwight D. Eisenhower ለአለም ህዝብ "Peace on earth and good will toward men everywhere." የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ችለው ነበር።

ከዚህ በሃላ የተለያዩ ሀገራት የተለያዩ አይነት ሳተላይቶችን ሰርተው ማስመንጠቅ እና ማምጠቅ ችለዋል። በአሁኑ ሰአት በአለማችን ላይ ከ 2000 በላይ ሳተላይቶች በጠፈር ላይ ይገኛሉ። በ ኢኮኖሚ ደካማ የሆኑ ሀገራት ሳተላይትን ከበለጸጉ ሀገራት እየተከራዩ ይጠቀማሉ። ለምሳሌ ሀገራችን ኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ በኪራይ የምትጠቀም ሲሆን ከጥቂት አመታት በሃላ የራሳን ለመስራት እየታተረች ትገኛለች።

በነገራችን ላይ ሳተላይትን መስራት ብቻውን ዋጋ የለውም የተሰራውን ሳተላይት የማመንጠቂያ መዐከል ያስፈልገዋል። ይሄ የመንኮራኮር ማመንጠቂያ ማእከል ያላቸው ሀገራት በጣት የሚቆጠሩ ሲሆን አብዛኛው የአለም ሀገራት የ ሩሲያ እና የአሜሪካንን ማመንጠቂያ ስፍራ ይጠቀማሉ። ከቅርብ ጊዜያት ጀምሮ ከመንግስት አልፎ የግል ኩባንያዎችም በዚህ ዘርፍ ላይ በስፋት ተሰማርተዋል።

እንዴት ትርፋማ ይሆናሉ ብሎ የሚያስብ ይኖራል። እንዴት መሰላቹ የተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያውች በየአመቱ የሚከፍሉት ገንዘብ አለ ለሳተላይቱ ባለቤቶች።

ለምሳሌ EBS Nile sat ላይ ይጠቀማል በዚህ ምክንያት በየአመቱ ከ500000 ብር በላይ ይከፍላል። አብዛኞቹ የ አፍሪካ ሀገራት የተቃዋሚዎቻቸውን ቻናል Jam አድርጎ ማጥፋት ሲያቅታቸው በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላሮችን ለ ሳተላይት ባለንብረቶች እየከፈሉ ከአየር ላይ ያስወርዳሉ።

በሀገራችን ሁኔታም ይሄ በስፋት የተለመደ ነው። በፊት ESATን የመሰሉ የመንግስት ተቃዋሚ ቻናሎችን ለማውረድ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን እያወጡ
ነበር::
JOIN AND SHARE BEST CHANNEL
@ethioandromedawithnahom
@ethioandromedawithnahom
@ethioandromedawithnahom
JOIN DISCCUS
@ethio_andromeda_info
@ethio_andromeda_info
@ethio_andromeda_info
SUBSCRIBE YOUTUBECHANNEL
https://youtube.com/channel/UCWwutRK77dZkaz6_ARrO2jA
231 viewsናሆም የኪድዬ ልጅ, 14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 21:59:03 ሰሞኑን በአንዳንድ የግል ምክንያቶቾ አልተገናኘንም ነበር ከነገ ጀምሮ እንቀጥላለን በዩቱብ በቲክቶክ እና በዚሁ በቴሌገራም እንጀምራለን እናንተም በቲክቶክ ፎሎው ያላረጋችሁን እና በዩቱብ subscribe ያላረጋችሁን ከታች ባለው ሊንክ እንድታሩጉን በአክብሮት እንጠይቃለን::
THE BEST TELRGRAM CHANNEL
@ethioandromedawithnahom
@ethioandromedawithnahom
@ethioandromedawithnahom
DISCCUS
@ethio_andromeda_info
@ethio_andromeda_info
@ethio_andromeda_info
THE BEST TIKTOK CHNNEL
http://tiktok.com/@ethioandromedawithnahom
http://tiktok.com/@ethioandromedawithnahom
http://tiktok.com/@ethioandromedawithnahom
THE BEST YOUTUBE CHANNEL
https://youtube.com/channel/UCWwutRK77dZkaz6_ARrO2jA
216 viewsATEREF AYALEW, 18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 19:26:14 http://t.me/amharicmotivation2
325 viewsATEREF AYALEW, 16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 07:18:14

1.1K viewsናሆም የኪድዬ ልጅ, 04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 09:32:28

2.6K viewsናሆም የኪድዬ ልጅ, 06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ