Get Mystery Box with random crypto!

ደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ 'STEM Synergy ከተባለ' አለም አቀፍ ድርጅት ጋር በመተባበር ለሁለተ | Ethio Students Books(Grade 9-12 )

ደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ "STEM Synergy ከተባለ" አለም አቀፍ ድርጅት ጋር በመተባበር ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በ "Coding and website development" ዙሪያ ስልጠና  በመሰጠት ላይ ነው።

ዩኒቨርስቲው ከSTEM Synergy ከተባለ አለም አቀፍ ድርጅት ጋር በመተባበር ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከሚያዚያ 04/2015 ጀምሮ ለተከታታይ አምስት (5) ሳምንታት በፕሮግራሚንግ እና ድህረ ገጽ አሰራር ዙሪያ  በደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ በሳይንስ፣ቴክኖሎጂ፣ምህንድስና እና ሒሳብ ማበልፀጊያ ማዕከል አስተባባሪነት ስልጠናው እየተሰጠ ይገኛል፡፡ስልጠናውን የሚሰጡት የማዕከሉ የቨርችዋል ላብራቶሪ ኤክስፐርት መ/ር አበበ ክንዴ እንዳሉት እንዲህ አይነት ስልጠናዎች መሰጠቱ ለተማሪዎቹ አሁን ባሉበት የክፍል ደረጃ ከወዲሁ ተሰጦዎቻቸውን እንዲለዩና እንዲያጎለብቱ እንደሚያግዝ ገልፀው ዩኒቨርሲቲው ተቋማዊ ዲጂታል አቅምን (Digital Capacity) የሚያሳድጉ መሰረተ ልማቶችን በመመስረት አበረታች ውጤት ማስመዝገቡን አስታውሰው በአገር አቀፍ ደረጃ ለመስኩ የተሰጠውን ትኩረት ታሳቢ በማድረግ ዩኒቨርሲቲው የሚገኝበትን የደቡብ ጎንደር ዞን የሁለተኛ ደረጃ ተማሪወችን የዲጂታል እውቀት እና ክህሎት የሚያሳድጉ በርካታ ስራወችን እያከናወነ እንደሆነ ገልፀዋል።                                                መረጃው የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ  ነው
@Ethio_Students_only
@Ethio_Students_only
@Elshio_ACADEMY