Get Mystery Box with random crypto!

ማንኛውም የግል ትምህርት ቤት መፅሃፍም ሆነ ደብተር መሸጥ እንደማይችል ማሳሰቢያ ተሰጠ አንድ የ | ኢትዮ Students News

ማንኛውም የግል ትምህርት ቤት መፅሃፍም ሆነ ደብተር መሸጥ እንደማይችል ማሳሰቢያ ተሰጠ

አንድ የትምህርት ተቋም ፍቃድ የተሰጠው ለማስተማር እንጂ፤ መጽሐፍም ሆነ ደብተር ለመሸጥ አይደለም ሲል የ #አዲስአበባ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል።

የባለስልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ፍቅርተ አበራ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ማንኛውም የግል ትምህርት ቤቶች ከመመሪያ ውጪ ያልተገባ ክፍያ አስከፍለው በተገኙ ተቋማት ላይ ርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል።።

በመመሪያ አተገባበሩ ላይ የተለያዩ ጥቆማዎች እየደረሱ እንደሚገኝም ኃላፊዋ አክለዋል። በመመሪያ አተገባበሩ ላይ ከመጡት ጥቆማዎች ውስጥ አንዳንድ ተቋማት የምዝገባ ክፍያ መጨመር፣ በዓይነት መቀበል ለአብነት እሽግ ወረቀት እና የመፀዳጃ ቤት የንፅህና እቃዎችን የሚጠይቁ እንዳሉበት ገልፀዋል።

በተጨማሪም ባልተፈቀደ ክፍያ ጭማሪ እያደረጉ ያሉ የትምህር ተቋማት እንደሚገኙ ጥቆማ ደርሶናል ወርደን እናስተካከልን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ማንኛውም የግል ትምህርት ቤቶች ከመደበኛ ክፍያ ውጪ በየትኛውም መልኩ ክፍያ ማስከፈል አይቻሉም፤ አንድ የትምህርት ተቋም ፍቃድ የተሰጠው ለማስተማር እንጂ መጽሐፍም ሆነ ደብተር ለመሸጥ አይደለም ብለዋል።ከተሰጠው ፍቃድ ውጪ ሲንቀሳቀስ በሚገኝ ተቋም ላይ ርምጃ ይወሰድበታል፤ የሰበሰበውን ገንዘብም ሆነ ማንኛውንም አይነት ቁሳቁስ እንዲመልስ ይደረጋል ሲሉ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ፍቅርተ አበራ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።