Get Mystery Box with random crypto!

ከ 140 ሺህ በላይ የአማሮ ልዩ ወረዳ ዜጎች ለከፍተኛ የርሃብ አደጋ መጋለጣቸው ተነገረ። የአማ | ኢትዮ Students News

ከ 140 ሺህ በላይ የአማሮ ልዩ ወረዳ ዜጎች ለከፍተኛ የርሃብ አደጋ መጋለጣቸው ተነገረ።

የአማሮ ልዩ ወረዳን ከሚያዋስነዉ ከምዕራብ ጉጂ ይመጣሉ የተባሉ ታጣቂዎች ባለፉት ስድስት ዓመታት በፈጠሩት ግጭት ከ 140 ሺህ በላይ ዜጎች ለከፍተኛ ርሃብ መጋለጣቸዉ ተነግሯል።

የልዩ ወረዳዉ የኬሌ ምርጫ ክልል የኢዜማ ጽ/ቤት ባወጣዉ መግለጫ በግጭቱ ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ የሚያስፈልገው ቢሆንም፣ መረጃው ለኢፌዴሪ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እንዳልደረሰ አረጋግጫሁ ብሏል።

ባለፉት ስድስት ዓመታት በአማሮ ልዩ ወረዳ በሚገኙ ከ 20 በላይ ቀበሌዎች ውስጥ በተከሰተው ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ 44,202 ዜጎች እንዲሁም በድርቅ አደጋ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው 96,440 -በአጠቃላይ 140,642 ሕዝብ አደጋ መሆናቸዉ ተሰምቷል።

በአማሮ የኢዜማ ጽ/ቤት በግጭቶች ሰላባ ሆነዉ ለተፈናቀሉት እንዲሁም በልዩ ወረዳዉ በተከሰተዉ የድርቅ አደጋ ተጠቂ የሆኑትን ዜጎች በተመለከተ ለብሔራዊ አደጋ ስጋት እና ሥራ አመራር ኮሚሽን መረጃ አለመድረሱን ገልጿል።